Al-Baiyina

Change Language
Change Surah
Change Recitation

Amharic: Muhammed Sadiq and Muhammed Sani Habib

Play All
# Translation Ayah
1 እነዚያ ከመጽሐፉ ባለቤቶች ከአጋሪዎቹም የካዱት ግልጹ አስረጅ እስከ መጣላቸው ድረስ (ከነበሩበት ላይ) ተወጋጆች አልነበሩም፡፡ لَمْ يَكُنِ الَّذِينَ كَفَرُوا مِنْ أَهْلِ الْكِتَابِ وَالْمُشْرِكِينَ مُنفَكِّينَ حَتَّى تَأْتِيَهُمُ الْبَيِّنَةُ
2 (አስረጁም) ከአላህ የኾነ መልክተኛ የተጥራሩን መጽሐፎች የሚያነብ ነው፡፡ رَسُولٌ مِّنَ اللَّهِ يَتْلُو صُحُفًا مُّطَهَّرَةً
3 በውስጧ ቀጥተኛ የኾኑ ጽሑፎች ያሉባት የኾነችን፡፡ فِيهَا كُتُبٌ قَيِّمَةٌ
4 እነዚያም መጽሐፉን የተሰጡት ሰዎች ግልጽ አስረጅ ከመጣላቸው በኋላ እንጅ አልተለያዩም፡፡ وَمَا تَفَرَّقَ الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ إِلَّا مِن بَعْدِ مَا جَاءتْهُمُ الْبَيِّنَةُ
5 አላህን ሃይማኖትን ለእርሱ ብቻ አጥሪዎች፣ ቀጥተኞች ኾነው ሊግገዙት፣ ሶላትንም አስተካክለው ሊሰግዱ ዘካንም ሊሰጡ እንጅ ያልታዘዙ ሲኾኑ (ተለያዩ)፡፡ ይህም የቀጥተኛይቱ (ሃይማኖት) ድንጋጌ ነው፡፡ وَمَا أُمِرُوا إِلَّا لِيَعْبُدُوا اللَّهَ مُخْلِصِينَ لَهُ الدِّينَ حُنَفَاء وَيُقِيمُوا الصَّلَاةَ وَيُؤْتُوا الزَّكَاةَ وَذَلِكَ دِينُ الْقَيِّمَةِ
6 እነዚያ ከመጽሐፉ ሰዎች የካዱት፣ አጋሪዎቹም በገሀነም እሳት ውስጥ ናቸው፤ በውስጧ ዘውታሪዎች ሲኾኑ እነዚያ እነርሱ ከፍጥረት ሁሉ ክፉ ናቸው፡፡ إِنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا مِنْ أَهْلِ الْكِتَابِ وَالْمُشْرِكِينَ فِي نَارِ جَهَنَّمَ خَالِدِينَ فِيهَا أُوْلَئِكَ هُمْ شَرُّ الْبَرِيَّةِ
7 እነዚያ ያመኑትና መልካሞችንም የሠሩት፣ እነዚያ እነርሱ ከፍጥረት ሁሉ በላጭ ናቸው፡፡ إِنَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ أُوْلَئِكَ هُمْ خَيْرُ الْبَرِيَّةِ
8 በጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው የመኖሪያ ገነቶች ነው፡፡ በውስጣቸው ዘለዓለም ዘውታሪዎች ሲኾኑ (ይገቡባቸወል)፡፡ አላህ ከእነርሱ ወደደ፡፡ ከእርሱም ወደዱ፡፡ ይህ ጌታውን ለፈራ ሰው ነው፡፡ جَزَاؤُهُمْ عِندَ رَبِّهِمْ جَنَّاتُ عَدْنٍ تَجْرِي مِن تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا أَبَدًا رَّضِيَ اللَّهُ عَنْهُمْ وَرَضُوا عَنْهُ ذَلِكَ لِمَنْ خَشِيَ رَبَّهُ
;