Al-Alaq

Change Language
Change Surah
Change Recitation

Amharic: Muhammed Sadiq and Muhammed Sani Habib

Play All
# Translation Ayah
1 አንብብ በዚያ (ሁሉን) በፈጠረው ጌታህ ስም፡፡ اقْرَأْ بِاسْمِ رَبِّكَ الَّذِي خَلَقَ
2 ሰውን ከረጋ ደም በፈጠረው (ጌታህ ስም)፡፡ خَلَقَ الْإِنسَانَ مِنْ عَلَقٍ
3 አንብብ፤ ጌታህ በጣም ቸር ሲኾን፤ اقْرَأْ وَرَبُّكَ الْأَكْرَمُ
4 ያ በብርዕ ያስተማረ፡፡ الَّذِي عَلَّمَ بِالْقَلَمِ
5 ሰውን ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቀ ሲኾን፡፡ عَلَّمَ الْإِنسَانَ مَا لَمْ يَعْلَمْ
6 በእውነቱ ሰው ወሰንን ያልፋል፡፡ كَلَّا إِنَّ الْإِنسَانَ لَيَطْغَى
7 ራሱን የተብቃቃ (ባለ ሀብት) ኾኖ ለማየቱ፡፡ أَن رَّآهُ اسْتَغْنَى
8 መመለሻው ወደ ጌታህ ብቻ ነው፡፡ إِنَّ إِلَى رَبِّكَ الرُّجْعَى
9 አየህን? ያንን የሚከለክለውን፡፡ أَرَأَيْتَ الَّذِي يَنْهَى
10 ባሪያን በሰገደ ጊዜ፤ عَبْدًا إِذَا صَلَّى
11 አየህን? ንገረኝ (ተከልካዩ) በትክክለኛ መንገድ ላይ ቢኾን፤ أَرَأَيْتَ إِن كَانَ عَلَى الْهُدَى
12 ወይም (ፈጣሪውን) በመፍራት ቢያዝ፤ أَوْ أَمَرَ بِالتَّقْوَى
13 አየህን? ንገረኝ (ከልካዩ) ቢያስተባብልና (ከእምነት) ቢሸሽ፤ أَرَأَيْتَ إِن كَذَّبَ وَتَوَلَّى
14 አላህ የሚያይ መኾኑን አያውቅምን? أَلَمْ يَعْلَمْ بِأَنَّ اللَّهَ يَرَى
15 ይተው ባይከለከል አናቱን ይዘን እንጎትተዋለን፡፡ كَلَّا لَئِن لَّمْ يَنتَهِ لَنَسْفَعًا بِالنَّاصِيَةِ
16 ውሸታም ስሕተተኛ የኾነችውን አናቱን፡፡ نَاصِيَةٍ كَاذِبَةٍ خَاطِئَةٍ
17 ሸንጎውንም ይጥራ፡፡ فَلْيَدْعُ نَادِيَه
18 (እኛም) ዘበኞቻችንን እንጠራለን፡፡ سَنَدْعُ الزَّبَانِيَةَ
19 ይከልከል አትታዘዘው፡፡ ስገድም፤ (ወደ አላህ) ተቃረብም፡፡ كَلَّا لَا تُطِعْهُ وَاسْجُدْ وَاقْتَرِبْ
;