Adh-Dhuha

Change Language
Change Surah
Change Recitation

Amharic: Muhammed Sadiq and Muhammed Sani Habib

Play All
# Translation Ayah
1 በረፋዱ እምላለሁ፡፡ وَالضُّحَى
2 በሌሊቱም ጸጥ ባለ ጊዜ፤ وَاللَّيْلِ إِذَا سَجَى
3 ጌታህ አላሰናበተህም፤ አልጠላህምም፡፡ مَا وَدَّعَكَ رَبُّكَ وَمَا قَلَى
4 መጨረሻይቱም (ዓለም) ከመጀመሪያይቱ ይልቅ ላንተ በላጭ ናት፡፡ وَلَلْآخِرَةُ خَيْرٌ لَّكَ مِنَ الْأُولَى
5 ጌታህም ወደ ፊት (ብዙን ስጦታ) በእርግጥ ይሰጥሃል፡፡ ትደሰታለህም፡፡ وَلَسَوْفَ يُعْطِيكَ رَبُّكَ فَتَرْضَى
6 የቲም ኾነህ አላገኘህምና አላስጠጋህምን? (አስጠግቶሃል)፡፡ أَلَمْ يَجِدْكَ يَتِيمًا فَآوَى
7 የሳትክም ኾነህ አገኘህ መራህም፡፡ وَوَجَدَكَ ضَالًّا فَهَدَى
8 ድኻም ኾነህ አገኘህ፤ አከበረህም፡፡ وَوَجَدَكَ عَائِلًا فَأَغْنَى
9 የቲምንማ አትጨቁን፡፡ فَأَمَّا الْيَتِيمَ فَلَا تَقْهَرْ
10 ለማኝንም አትገላምጥ፡፡ وَأَمَّا السَّائِلَ فَلَا تَنْهَرْ
11 በጌታህም ጸጋ አውራ፤ (ግለጻት)፡፡ وَأَمَّا بِنِعْمَةِ رَبِّكَ فَحَدِّثْ
;