Ash-Shams

Change Language
Change Surah
Change Recitation

Amharic: Muhammed Sadiq and Muhammed Sani Habib

Play All
# Translation Ayah
1 በፀሐይና በብርሃኗ እምላለሁ፡፡ وَالشَّمْسِ وَضُحَاهَا
2 በጨረቃም በተከተላት ጊዜ፤ وَالْقَمَرِ إِذَا تَلَاهَا
3 በቀኑም (ፀሐይን) በገለጻት ጊዜ፤ وَالنَّهَارِ إِذَا جَلَّاهَا
4 በሌሊቱም በሸፈናት ጊዜ፤ وَاللَّيْلِ إِذَا يَغْشَاهَا
5 በሰማይቱም በገነባትም (ጌታ)፤ وَالسَّمَاء وَمَا بَنَاهَا
6 በምድሪቱም በዘረጋትም፤ وَالْأَرْضِ وَمَا طَحَاهَا
7 በነፍስም ባስተካከላትም፤ وَنَفْسٍ وَمَا سَوَّاهَا
8 አመጽዋንና ፍርሃትዋንም ባሳወቃት (አምላክ እምላለሁ)፡፡ فَأَلْهَمَهَا فُجُورَهَا وَتَقْوَاهَا
9 (ከኀጢኣት) ያጠራት ሰው ፍላጎቱን በእርግጥ አገኘ፡፡ قَدْ أَفْلَحَ مَن زَكَّاهَا
10 (በኀጢኣት) የሸፈናትም ሰው በእውነት አፈረ፡፡ وَقَدْ خَابَ مَن دَسَّاهَا
11 ሠሙድ ወሰን በማለፍዋ አስተባበለች፡፡ كَذَّبَتْ ثَمُودُ بِطَغْوَاهَا
12 ጠማማዋ በተንቀሳቀሰ ጊዜ፡፡ إِذِ انبَعَثَ أَشْقَاهَا
13 ለእነርሱም የአላህ መልክተኛ (ሷሊህ) «የአላህን ግመል የመጠጥ ተራዋንም (ተጠንቀቁ)» አላቸው፡፡ فَقَالَ لَهُمْ رَسُولُ اللَّهِ نَاقَةَ اللَّهِ وَسُقْيَاهَا
14 አስተባበሉትም፡፡ (ቋንጃዋን) ወጓትም፡፡ በኀጢኣታቸውም ምክንያት ጌታቸው (ቅጣትን) በእነርሱ ላይ ደመደመባቸው፤ አስተካከላትም፡፡ فَكَذَّبُوهُ فَعَقَرُوهَا فَدَمْدَمَ عَلَيْهِمْ رَبُّهُم بِذَنبِهِمْ فَسَوَّاهَا
15 ፍጻሜዋንም (የምታስከትለውን) አያፈራም፡፡ وَلَا يَخَافُ عُقْبَاهَا
;