Al-Gashiya

Change Language
Change Surah
Change Recitation

Amharic: Muhammed Sadiq and Muhammed Sani Habib

Play All
# Translation Ayah
1 የሸፋኝቱ (ትንሣኤ) ወሬ መጣህን? هَلْ أَتَاكَ حَدِيثُ الْغَاشِيَةِ
2 ፊቶች በዚያ ቀን ተዋራጆች ናቸው፡፡ وُجُوهٌ يَوْمَئِذٍ خَاشِعَةٌ
3 ሠሪዎች ለፊዎች ናቸው፡፡ عَامِلَةٌ نَّاصِبَةٌ
4 ተኳሳን እሳት ይገባሉ፡፡ تَصْلَى نَارًا حَامِيَةً
5 በጣም ከፈላች ምንጭ ይጋታሉ፡፡ تُسْقَى مِنْ عَيْنٍ آنِيَةٍ
6 ለእነርሱ ዶሪዕ ከሚባል (እሾሃም) ዛፍ እንጅ ሌላ ምግብ የላቸውም፡፡ لَّيْسَ لَهُمْ طَعَامٌ إِلَّا مِن ضَرِيعٍ
7 የማያሰባ ከረኃብም የማያብቃቃ ከኾነው፡፡ لَا يُسْمِنُ وَلَا يُغْنِي مِن جُوعٍ
8 ፊቶች በዚያ ቀን ተቀማጣዮች ናቸው፡፡ وُجُوهٌ يَوْمَئِذٍ نَّاعِمَةٌ
9 ለሥራቸው ተደሳቾች ናቸው፡፡ لِسَعْيِهَا رَاضِيَةٌ
10 በከፍተኛ ገነት ውስጥ ናቸው፡፡ فِي جَنَّةٍ عَالِيَةٍ
11 በውስጧ ውድቅን ነገር አይሰሙም፡፡ لَّا تَسْمَعُ فِيهَا لَاغِيَةً
12 በውስጧ ፈሳሾች ምንጮች አልሉ፡፡ فِيهَا عَيْنٌ جَارِيَةٌ
13 በውስጧ ከፍ የተደረጉ አልጋዎች አልሉ፡፡ فِيهَا سُرُرٌ مَّرْفُوعَةٌ
14 በተርታ የተኖሩ ብርጭቆዎችም፡፡ وَأَكْوَابٌ مَّوْضُوعَةٌ
15 የተደረደሩ መከዳዎችም፡፡ وَنَمَارِقُ مَصْفُوفَةٌ
16 የተነጠፉ ስጋጃዎችም (አልሉ)፡፡ وَزَرَابِيُّ مَبْثُوثَةٌ
17 (ከሓዲዎች) አይመለከቱምን? ወደ ግመል እንዴት እነደተፈጠረች! أَفَلَا يَنظُرُونَ إِلَى الْإِبِلِ كَيْفَ خُلِقَتْ
18 ወደ ሰማይም እንዴት ከፍ እንደ ተደረገች! وَإِلَى السَّمَاء كَيْفَ رُفِعَتْ
19 ወደ ተራራዎችም እንዴት እንደ ተቸከሉ! وَإِلَى الْجِبَالِ كَيْفَ نُصِبَتْ
20 ወደ ምድርም እንዴ እንደተዘረጋች (አይመለከቱምን?) وَإِلَى الْأَرْضِ كَيْفَ سُطِحَتْ
21 አስታውስም፤ አንተ አስታዋሽ ብቻ ነህና፡፡ فَذَكِّرْ إِنَّمَا أَنتَ مُذَكِّرٌ
22 በእነርሱ ላይ ተሿሚ (አስገዳጅ) አይደለህም፡፡ لَّسْتَ عَلَيْهِم بِمُصَيْطِرٍ
23 ግን (ከእውነት) የዞረና የካደ ሰው፤ إِلَّا مَن تَوَلَّى وَكَفَرَ
24 አላህ ታላቁን ቅጣት ይቀጣዋል፡፡ فَيُعَذِّبُهُ اللَّهُ الْعَذَابَ الْأَكْبَرَ
25 መመለሻቸው ወደእኛ ብቻ ነው፡፡ إِنَّ إِلَيْنَا إِيَابَهُمْ
26 ከዚያም ምርመራቸው በእኛ ላይ ብቻ ነው፡፡ ثُمَّ إِنَّ عَلَيْنَا حِسَابَهُمْ
;