Al-Fajr

Change Language
Change Surah
Change Recitation

Amharic: Muhammed Sadiq and Muhammed Sani Habib

Play All
# Translation Ayah
1 በጎህ እምላለሁ፡፡ وَالْفَجْرِ
2 በዐሥር ሌሊቶችም፡፡ وَلَيَالٍ عَشْرٍ
3 በጥንዱም በነጠላውም፡፡ وَالشَّفْعِ وَالْوَتْرِ
4 በሌሊቱም በሚኼድ ጊዜ፡፡ وَاللَّيْلِ إِذَا يَسْرِ
5 በዚህ (መሓላ) ለባለ አእምሮ ታላቅ መሓላ አለበትን? هَلْ فِي ذَلِكَ قَسَمٌ لِّذِي حِجْرٍ
6 ጌታህ በዓድ እንዴት እንደ ሠራ አታውቅምን? أَلَمْ تَرَ كَيْفَ فَعَلَ رَبُّكَ بِعَادٍ
7 በኢረም በባለ ረዣዢሚቱ አዕማድ፡፡ إِرَمَ ذَاتِ الْعِمَادِ
8 በዚያች ብጤዋ በአገሮች ውስጥ ያልተፈጠረ በኾነችው፡፡ الَّتِي لَمْ يُخْلَقْ مِثْلُهَا فِي الْبِلَادِ
9 በሰሙድም በእነዚያ በሸለቆው ቋጥኝን የቆረጡ በኾኑት፡፡ وَثَمُودَ الَّذِينَ جَابُوا الصَّخْرَ بِالْوَادِ
10 በፈርዖንም ባለ ችካሎች በኾነው፡፡ وَفِرْعَوْنَ ذِي الْأَوْتَادِ
11 በእነዚያ በአገሮች ላይ ግፍ የሠሩ፡፡ الَّذِينَ طَغَوْا فِي الْبِلَادِ
12 በእርሷም ውስጥ ጥፋትን ያበዙ በኾኑት (እንዴት እንደሠራ አታውቅምን?) فَأَكْثَرُوا فِيهَا الْفَسَادَ
13 በእነርሱ ላይም ጌታህ የቅጣትን አለንጋ አወረደባቸው፡፡ فَصَبَّ عَلَيْهِمْ رَبُّكَ سَوْطَ عَذَابٍ
14 ጌታህ በመጠባበቂያ ላይ ነውና፡፡ إِنَّ رَبَّكَ لَبِالْمِرْصَادِ
15 ሰውማ ጌታው በሞከረው ጊዜ፣ ባከበረውና ባጣቀመውም (ጊዜ) «ጌታዬ አከበረኝ (አበለጠኝ)» ይላል፡፡ فَأَمَّا الْإِنسَانُ إِذَا مَا ابْتَلَاهُ رَبُّهُ فَأَكْرَمَهُ وَنَعَّمَهُ فَيَقُولُ رَبِّي أَكْرَمَنِ
16 በሞከረውና በእርሱ ላይ ሲሳዩን ባጠበበ ጊዜማ «ጌታዬ አሳነሰኝ» ይላል፡፡ وَأَمَّا إِذَا مَا ابْتَلَاهُ فَقَدَرَ عَلَيْهِ رِزْقَهُ فَيَقُولُ رَبِّي أَهَانَنِ
17 ይከልከል፤ ይልቁንም የቲምን አታከብሩም፡፡ كَلَّا بَل لَّا تُكْرِمُونَ الْيَتِيمَ
18 ድኻንም በማብላት ላይ አትታዘዙም፡፡ وَلَا تَحَاضُّونَ عَلَى طَعَامِ الْمِسْكِينِ
19 የውርስንም ገንዘብ የመሰብሰብን አበላል ትበላላችሁ፡፡ وَتَأْكُلُونَ التُّرَاثَ أَكْلًا لَّمًّا
20 ገንዘብንም ብዙን መውደድ ትወዳላችሁ፡፡ وَتُحِبُّونَ الْمَالَ حُبًّا جَمًّا
21 ተዉ፤ ምድር ደጋግማ በተሰባበረች ጊዜ፤ كَلَّا إِذَا دُكَّتِ الْأَرْضُ دَكًّا دَكًّا
22 መላእክትም ሰልፍ ሰልፍ ኾነው ጌታህ (ትዕዛዙ) በመጣ ጊዜ፤ وَجَاء رَبُّكَ وَالْمَلَكُ صَفًّا صَفًّا
23 ገሀነምም በዚያ ቀን በተመጣች ጊዜ በዚያ ቀን ሰው (ጥፋቱን) ይገነዘባል፡፡ መገንዘብም ለእርሱ ከየቱ? وَجِيءَ يَوْمَئِذٍ بِجَهَنَّمَ يَوْمَئِذٍ يَتَذَكَّرُ الْإِنسَانُ وَأَنَّى لَهُ الذِّكْرَى
24 «ዋ እኔ! ምነው በሕይወቴ (መልካምን ሥራ) ባስቀደምኩ ኖሮ» ይላል፡፡ يَقُولُ يَا لَيْتَنِي قَدَّمْتُ لِحَيَاتِي
25 በዚያ ቀንም የርሱን አቀጣጥ አንድም አይቀጣም፡፡ فَيَوْمَئِذٍ لَّا يُعَذِّبُ عَذَابَهُ أَحَدٌ
26 የእርሱንም አስተሳሰር አንድም አያስርም፡፡ وَلَا يُوثِقُ وَثَاقَهُ أَحَدٌ
27 (ለአመነች ነፍስም) «አንቺ የረካሺው ነፍስ ሆይ! يَا أَيَّتُهَا النَّفْسُ الْمُطْمَئِنَّةُ
28 «ወዳጅ ተወዳጅ ኾነሽ ወደ ጌታሽ ተመለሺ፡፡ ارْجِعِي إِلَى رَبِّكِ رَاضِيَةً مَّرْضِيَّةً
29 «በባሮቼም ውስጥ ግቢ፡፡ فَادْخُلِي فِي عِبَادِي
30 ገነቴንም ግቢ፤» (ትባላለች)፡፡ وَادْخُلِي جَنَّتِي
;