Al-A'la

Change Language
Change Surah
Change Recitation

Amharic: Muhammed Sadiq and Muhammed Sani Habib

Play All
# Translation Ayah
1 ከሁሉ በላይ የኾነውን ጌታህን ስም አሞግሥ፡፡ سَبِّحِ اسْمَ رَبِّكَ الْأَعْلَى
2 የዚያን (ሁሉን ነገር) የፈጠረውን ያስተካከለውንም፡፡ الَّذِي خَلَقَ فَسَوَّى
3 የዚያንም የወሰነውን፡፡ (ለተፈጠረለት ነገር) የመራውንም፡፡ وَالَّذِي قَدَّرَ فَهَدَى
4 የዚያንም ግጦሽን (ለምለም አድርጎ) ያወጣውን፡፡ وَالَّذِي أَخْرَجَ الْمَرْعَى
5 (ከዚያ) ደረቅ ጥቁር ያደረገውንም (አምላክ ስም አሞግስ)፡፡ فَجَعَلَهُ غُثَاء أَحْوَى
6 (ቁርኣንን) በእርግጥ እናስነብብሃለን፤ አትረሳምም፡፡ سَنُقْرِؤُكَ فَلَا تَنسَى
7 አላህ ከሻው ነገር በስተቀር፡፡ እርሱ ግልጹን የሚሸሸገውንም ሁሉ ያውቃልና፡፡ إِلَّا مَا شَاء اللَّهُ إِنَّهُ يَعْلَمُ الْجَهْرَ وَمَا يَخْفَى
8 ለገሪቱም (ሕግጋት) እንገጥምሃለን፡፡ وَنُيَسِّرُكَ لِلْيُسْرَى
9 ግሣጼይቱ ብትጠቅም (ሰዎችን) ገሥጽም፡፡ فَذَكِّرْ إِن نَّفَعَتِ الذِّكْرَى
10 (አላህን) የሚፈራ ሰው በእርግጥ ይገሠጻል፡፡ سَيَذَّكَّرُ مَن يَخْشَى
11 መናጢውም ይርቃታል፡፡ وَيَتَجَنَّبُهَا الْأَشْقَى
12 ያ ታላቂቱን እሳት የሚገባው፡፡ الَّذِي يَصْلَى النَّارَ الْكُبْرَى
13 ከዚያም በእርሷ ውስጥ አይሞትም ሕያውም አይኾንም፡፡ ثُمَّ لَا يَمُوتُ فِيهَا وَلَا يَحْيَى
14 የተጥራራ ሰው በእርግጥ ዳነ፡፡ قَدْ أَفْلَحَ مَن تَزَكَّى
15 የጌታውንም ስም ያወሳና የሰገደ፡፡ وَذَكَرَ اسْمَ رَبِّهِ فَصَلَّى
16 ይልቁንም ቅርቢቱን ሕይወት ትመርጣላችሁ፡፡ بَلْ تُؤْثِرُونَ الْحَيَاةَ الدُّنْيَا
17 መጨረሻይቱ (ሕይወት) በላጭ ሁል ጊዜ ዘውታሪም ስትኾን፡፡ وَالْآخِرَةُ خَيْرٌ وَأَبْقَى
18 ይህ በፊተኞቹ መጻሕፍት ውስጥ ያልለ ነው፡፡ إِنَّ هَذَا لَفِي الصُّحُفِ الْأُولَى
19 በኢብራሂምና በሙሳ ጽሑፎች ውስጥ፡፡ صُحُفِ إِبْرَاهِيمَ وَمُوسَى
;