At-Tariq

Change Language
Change Surah
Change Recitation

Amharic: Muhammed Sadiq and Muhammed Sani Habib

Play All
# Translation Ayah
1 በሰማዩ በሌሊት መጪውም እምላለሁ፡፡ وَالسَّمَاء وَالطَّارِقِ
2 የሌሊት መጪውም ምን እንደ ኾነ ምን አሳወቀህ? وَمَا أَدْرَاكَ مَا الطَّارِقُ
3 ጨለማን ቀዳጁ ኮከብ ነው፡፡ النَّجْمُ الثَّاقِبُ
4 ነፍስ ሁሉ በእርሷ ላይ ጠባቂ ያለባት እንጅ ሌላ አይደለችም፡፡ إِن كُلُّ نَفْسٍ لَّمَّا عَلَيْهَا حَافِظٌ
5 ሰውም ከምን እንደተፈጠረ ይመልከት፡፡ فَلْيَنظُرِ الْإِنسَانُ مِمَّ خُلِقَ
6 ከተስፈንጣሪ ውሃ ተፈጠረ፡፡ خُلِقَ مِن مَّاء دَافِقٍ
7 ከጀርባና ከእርግብግብቶች መካከል የሚወጣ ከኾነ (ውሃ)፡፡ يَخْرُجُ مِن بَيْنِ الصُّلْبِ وَالتَّرَائِبِ
8 እርሱ (አላህ) በመመለሱ ላይ በእርግጥ ቻይ ነው፡፡ إِنَّهُ عَلَى رَجْعِهِ لَقَادِرٌ
9 ምስጢሮች በሚገለጡበት ቀን፡፡ يَوْمَ تُبْلَى السَّرَائِرُ
10 ለእርሱም (ለሰው) ኀይልና ረዳት ምንም የለውም፡፡ فَمَا لَهُ مِن قُوَّةٍ وَلَا نَاصِرٍ
11 የመመለስ ባለቤት በኾነችው ሰማይም እምላለሁ፡፡ وَالسَّمَاء ذَاتِ الرَّجْعِ
12 (በበቃይ) የመሰንጠቅ ባለቤት በኾነችው ምድርም፤ وَالْأَرْضِ ذَاتِ الصَّدْعِ
13 እርሱ (እውነትን ከውሸት) የሚለይ ቃል ነው፡፡ إِنَّهُ لَقَوْلٌ فَصْلٌ
14 እርሱም ቀልድ አይደለም፡፡ وَمَا هُوَ بِالْهَزْلِ
15 እነርሱ በእርግጥ ተንኮልን ይሠራሉ፡፡ إِنَّهُمْ يَكِيدُونَ كَيْدًا
16 (እኔ) ተንኮልንም እመልሳለሁ፡፡ وَأَكِيدُ كَيْدًا
17 ከሓዲዎችንም ቀን ስጣቸው፡፡ ጥቂትን ጊዜ አቆያቸው፡፡ فَمَهِّلِ الْكَافِرِينَ أَمْهِلْهُمْ رُوَيْدًا
;