Al-Buruj

Change Language
Change Surah
Change Recitation

Amharic: Muhammed Sadiq and Muhammed Sani Habib

Play All
# Translation Ayah
1 የቡርጆች ባለቤት በኾነችው ሰማይ እምላለሁ፡፡ وَالسَّمَاء ذَاتِ الْبُرُوجِ
2 በተቀጠረው ቀንም፤ وَالْيَوْمِ الْمَوْعُودِ
3 በተጣጅና በሚጣዱትም፤ (እምላለሁ)፡፡ وَشَاهِدٍ وَمَشْهُودٍ
4 የጉድቡ ባለቤቶች ተረገሙ፡፡ قُتِلَ أَصْحَابُ الْأُخْدُودِ
5 የማገዶ ባለቤት የኾነቺው እሳት (ባለቤቶች)፡፡ النَّارِ ذَاتِ الْوَقُودِ
6 እነርሱ በርሷ (አፋፍ) ላይ ተቀማጮች በኾኑ ጊዜ፤ (ተረገሙ)፡፡ إِذْ هُمْ عَلَيْهَا قُعُودٌ
7 እነርሱም በምእምናኖቹ በሚሠሩት (ማሰቃየት) ላይ መስካሪዎች ናቸው፡፡ وَهُمْ عَلَى مَا يَفْعَلُونَ بِالْمُؤْمِنِينَ شُهُودٌ
8 ከእነርሱም በአላህ አሸናፊው፣ ምስጉኑ በኾነው (ጌታ) ማመናቸውን እንጅ ሌላ ምንም አልጠሉም፡፡ وَمَا نَقَمُوا مِنْهُمْ إِلَّا أَن يُؤْمِنُوا بِاللَّهِ الْعَزِيزِ الْحَمِيدِ
9 በእዚያ የሰማያትና የምድር ንግሥና ለእርሱ ብቻ በኾነው (አላህ ማመናቸውን)፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ መስካሪ ነው፡፡ الَّذِي لَهُ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَاللَّهُ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ شَهِيدٌ
10 እነዚያ ምእምንንና ምእምናትን ያሰቃዩ፣ ከዚያም ያልተጸጸቱ ለእነርሱ የገሀነም ቅጣት አልላቸው፡፡ ለእነርሱም የመቃጠሉ ስቃይ አልላቸው፡፡ إِنَّ الَّذِينَ فَتَنُوا الْمُؤْمِنِينَ وَالْمُؤْمِنَاتِ ثُمَّ لَمْ يَتُوبُوا فَلَهُمْ عَذَابُ جَهَنَّمَ وَلَهُمْ
11 እነዚያ ያመኑና መልካም ሥራዎችንም የሠሩ ለእነርሱ ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች አሏቸው፡፡ ይህ ታላቅ ማግኘት ነው፡፡ إِنَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ لَهُمْ جَنَّاتٌ تَجْرِي مِن تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ ذَلِكَ الْفَوْزُ الْكَبِيرُ
12 የጌታህ በኀይል መያዝ ብርቱ ነው፡፡ إِنَّ بَطْشَ رَبِّكَ لَشَدِيدٌ
13 እነሆ እርሱ መፍጠርን ይጀምራል፤ ይመልሳልም፡፡ إِنَّهُ هُوَ يُبْدِئُ وَيُعِيدُ
14 እርሱም ምሕረተ ብዙ ወዳድ ነው፡፡ وَهُوَ الْغَفُورُ الْوَدُودُ
15 የዙፋኑ ባለቤት የላቀው ነው፡፡ ذُو الْعَرْشِ الْمَجِيدُ
16 የሚሻውን ሁሉ ሠሪ ነው፡፡ فَعَّالٌ لِّمَا يُرِيدُ
17 የሰራዊቶቹ ወሬ መጣልህን? هَلْ أَتَاكَ حَدِيثُ الْجُنُودِ
18 የፈርዖንና የሰሙድ፤ (ወሬ)፡፡ فِرْعَوْنَ وَثَمُودَ
19 በእውነቱ እነዚያ የካዱት በማስተባበል ውስጥ ናቸው፡፡ بَلِ الَّذِينَ كَفَرُوا فِي تَكْذِيبٍ
20 አላህም በዙሪያቸው (በዕውቀቱ) ከባቢ ነው፡፡ وَاللَّهُ مِن وَرَائِهِم مُّحِيطٌ
21 ይልቁንም እርሱ የከበረ ቁርኣን ነው፡፡ بَلْ هُوَ قُرْآنٌ مَّجِيدٌ
22 የተጠበቀ በኾነ ሰሌዳ ውስጥ ነው፡፡ فِي لَوْحٍ مَّحْفُوظٍ
;