| 1 |
ሰማይ በተቀደደች ጊዜ፤ |
/content/ayah/audio/hudhaify/084001.mp3
|
إِذَا السَّمَاء انشَقَّتْ |
| 2 |
ለጌታዋም (ትዕዛዝ) በሰማች ጊዜ፤ (ልትሰማ) ተገባትም፤ |
/content/ayah/audio/hudhaify/084002.mp3
|
وَأَذِنَتْ لِرَبِّهَا وَحُقَّتْ |
| 3 |
ምድርም በተለጠጠች ጊዜ፤ |
/content/ayah/audio/hudhaify/084003.mp3
|
وَإِذَا الْأَرْضُ مُدَّتْ |
| 4 |
በውስጧ ያለውንም ሁሉ በጣለችና ባዶ በኾነች ጊዜ፤ |
/content/ayah/audio/hudhaify/084004.mp3
|
وَأَلْقَتْ مَا فِيهَا وَتَخَلَّتْ |
| 5 |
ለጌታዋም በሰማች ጊዜ፤ (መስማት) ተገባትም፤ (ሰው ሁሉ ሥራውን ይገናኛል)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/084005.mp3
|
وَأَذِنَتْ لِرَبِّهَا وَحُقَّتْ |
| 6 |
አንተ ሰው ሆይ! አንተ ጌታህን (በሞት) እስከምትገናኝ ድረስ ልፋትን ለፊ ነህ፤ ተገናኚውም ነህ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/084006.mp3
|
يَا أَيُّهَا الْإِنسَانُ إِنَّكَ كَادِحٌ إِلَى رَبِّكَ كَدْحًا فَمُلَاقِيهِ |
| 7 |
መጽሐፉን በቀኙ የተሰጠ ሰውማ፤ |
/content/ayah/audio/hudhaify/084007.mp3
|
فَأَمَّا مَنْ أُوتِيَ كِتَابَهُ بِيَمِينِهِ |
| 8 |
በእርግጥ ቀላልን ምርመራ ይመረመራል፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/084008.mp3
|
فَسَوْفَ يُحَاسَبُ حِسَابًا يَسِيرًا |
| 9 |
ወደ ቤተሰቦቹም ተደሳች ኾኖ ይመለሳል፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/084009.mp3
|
وَيَنقَلِبُ إِلَى أَهْلِهِ مَسْرُورًا |
| 10 |
መጽሐፉን በጀርባው ኋላ የተሰጠ ሰውማ፤ |
/content/ayah/audio/hudhaify/084010.mp3
|
وَأَمَّا مَنْ أُوتِيَ كِتَابَهُ وَرَاء ظَهْرِهِ |
| 11 |
(ዋ! ጥፋቴ በማለት) ጥፋትን በእርግጥ ይጠራል፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/084011.mp3
|
فَسَوْفَ يَدْعُو ثُبُورًا |
| 12 |
የተጋጋመች እሳትንም ይገባል፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/084012.mp3
|
وَيَصْلَى سَعِيرًا |
| 13 |
እርሱ በቤተሰቡ ውስጥ ተደሳች ነበርና፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/084013.mp3
|
إِنَّهُ كَانَ فِي أَهْلِهِ مَسْرُورًا |
| 14 |
እርሱ (ወደ አላህ) የማይመለስ መኾኑን አስቧልና፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/084014.mp3
|
إِنَّهُ ظَنَّ أَن لَّن يَحُورَ |
| 15 |
አይደለም (ይመለሳል)፡፡ ጌታው በእርሱ (መመለስ) ዐዋቂ ነበር፤ (ነውም)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/084015.mp3
|
بَلَى إِنَّ رَبَّهُ كَانَ بِهِ بَصِيرًا |
| 16 |
አትካዱ፤ በወጋገኑ እምላለሁ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/084016.mp3
|
فَلَا أُقْسِمُ بِالشَّفَقِ |
| 17 |
በሌሊቱም በሰበሰውም ሁሉ፤ |
/content/ayah/audio/hudhaify/084017.mp3
|
وَاللَّيْلِ وَمَا وَسَقَ |
| 18 |
በጨረቃውም በሞላ ጊዜ (እምላለሁ)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/084018.mp3
|
وَالْقَمَرِ إِذَا اتَّسَقَ |
| 19 |
ከኹነታ በኋላ ወደ ሌላ ኹነታ ትለዋወጣላችሁ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/084019.mp3
|
لَتَرْكَبُنَّ طَبَقًا عَن طَبَقٍ |
| 20 |
የማያምኑት ለእነርሱ ምን አላቸው? |
/content/ayah/audio/hudhaify/084020.mp3
|
فَمَا لَهُمْ لَا يُؤْمِنُونَ |
| 21 |
በእነርሱም ላይ ቁርኣን በተነበበ ጊዜ የማይሰግዱት፤ (ምንአላቸው?) |
/content/ayah/audio/hudhaify/084021.mp3
|
وَإِذَا قُرِئَ عَلَيْهِمُ الْقُرْآنُ لَا يَسْجُدُونَ |
| 22 |
በእርግጡ እነዚያ የካዱት (በትንሣኤ) ያስተባብላሉ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/084022.mp3
|
بَلِ الَّذِينَ كَفَرُواْ يُكَذِّبُونَ |
| 23 |
አላህም (በልቦቻቸው) የሚቆጥሩትን ዐዋቂ ነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/084023.mp3
|
وَاللَّهُ أَعْلَمُ بِمَا يُوعُونَ |
| 24 |
በአሳማሚ ቅጣትም አብስራቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/084024.mp3
|
فَبَشِّرْهُم بِعَذَابٍ أَلِيمٍ |
| 25 |
ግን እነዚያ ያመኑና መልካሞችን የሠሩ ለእነርሱ የማይቆረጥ ምንዳ አልላቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/084025.mp3
|
إِلَّا الَّذِينَ آمَنُواْ وَعَمِلُواْ الصَّالِحَاتِ لَهُمْ أَجْرٌ غَيْرُ مَمْنُونٍ |