| 1 |
ለሰላቢዎች ወዮላቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/083001.mp3
|
وَيْلٌ لِّلْمُطَفِّفِينَ |
| 2 |
ለእነዚያ ከሰዎች ባስሰፈሩ ጊዜ የሚያስሞሉ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/083002.mp3
|
الَّذِينَ إِذَا اكْتَالُواْ عَلَى النَّاسِ يَسْتَوْفُونَ |
| 3 |
ለእነርሱም (ለሰዎቹ) በሰፈሩ ወይም በመዘኑላቸው ጊዜ የሚያጎድሉ (ለኾኑት)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/083003.mp3
|
وَإِذَا كَالُوهُمْ أَو وَّزَنُوهُمْ يُخْسِرُونَ |
| 4 |
እነዚያ እነርሱ ተቀስቃሾች መኾናቸውን አያውቁምን? |
/content/ayah/audio/hudhaify/083004.mp3
|
أَلَا يَظُنُّ أُولَئِكَ أَنَّهُم مَّبْعُوثُونَ |
| 5 |
በታላቁ ቀን፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/083005.mp3
|
لِيَوْمٍ عَظِيمٍ |
| 6 |
ሰዎች ሁሉ ለዓለማት ጌታ (ፍርድ)፤ በሚቆሙበት ቀን (ተቀስቃሾች መኾናቸውን)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/083006.mp3
|
يَوْمَ يَقُومُ النَّاسُ لِرَبِّ الْعَالَمِينَ |
| 7 |
በእውነት የከሓዲዎቹ (የሰላቢዎቹ) መጽሐፍ በእርግጥ በሲጂን ውስጥ ነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/083007.mp3
|
كَلَّا إِنَّ كِتَابَ الفُجَّارِ لَفِي سِجِّينٍ |
| 8 |
ሲጂንም ምን እንደ ኾነ ምን አሳወቀህ? |
/content/ayah/audio/hudhaify/083008.mp3
|
وَمَا أَدْرَاكَ مَا سِجِّينٌ |
| 9 |
የታተመ መጽሐፍ ነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/083009.mp3
|
كِتَابٌ مَّرْقُومٌ |
| 10 |
ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/083010.mp3
|
وَيْلٌ يَوْمَئِذٍ لِّلْمُكَذِّبِينَ |
| 11 |
ለእነዚያ በፍርዱ ቀን ለሚያስተባብሉት፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/083011.mp3
|
الَّذِينَ يُكَذِّبُونَ بِيَوْمِ الدِّينِ |
| 12 |
በእርሱም ወሰን አላፊ ኀጢአተኛ ሁሉ እንጅ ሌላ አያስተባብልም፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/083012.mp3
|
وَمَا يُكَذِّبُ بِهِ إِلَّا كُلُّ مُعْتَدٍ أَثِيمٍ |
| 13 |
አንቀጾቻችን በእርሱ ላይ በተነበቡ ጊዜ «የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች ናቸው» ይላል፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/083013.mp3
|
إِذَا تُتْلَى عَلَيْهِ آيَاتُنَا قَالَ أَسَاطِيرُ الْأَوَّلِينَ |
| 14 |
ይከልከል፤ ይልቁንም በልቦቻቸው ላይ ይሠሩት የነበሩት (ኀጢአት) ደገደገባቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/083014.mp3
|
كَلَّا بَلْ رَانَ عَلَى قُلُوبِهِم مَّا كَانُوا يَكْسِبُونَ |
| 15 |
ይከልከሉ፤ እነርሱ በዚያ ቀን ከጌታቸው (ማየት) ተጋራጆች ናቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/083015.mp3
|
كَلَّا إِنَّهُمْ عَن رَّبِّهِمْ يَوْمَئِذٍ لَّمَحْجُوبُونَ |
| 16 |
ከዚያም እነርሱ በእርግጥ ገሀነምን ገቢዎች ናቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/083016.mp3
|
ثُمَّ إِنَّهُمْ لَصَالُوا الْجَحِيمِ |
| 17 |
ከዚያም «ይህ ያ በእርሱ ታስተባብሉበት የነበራችሁት ነው» ይባላሉ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/083017.mp3
|
ثُمَّ يُقَالُ هَذَا الَّذِي كُنتُم بِهِ تُكَذِّبُونَ |
| 18 |
በእውነቱ የእውነተኞቹ ምእምናን መጽሐፍ በዒሊዮን ውስጥ ነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/083018.mp3
|
كَلَّا إِنَّ كِتَابَ الْأَبْرَارِ لَفِي عِلِّيِّينَ |
| 19 |
ዒሊዮንም ምን እንደ ኾነ ምን አሳወቀህ? |
/content/ayah/audio/hudhaify/083019.mp3
|
وَمَا أَدْرَاكَ مَا عِلِّيُّونَ |
| 20 |
የታተመ መጽሐፍ ነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/083020.mp3
|
كِتَابٌ مَّرْقُومٌ |
| 21 |
ባለሟልዎቹ ይጣዱታል፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/083021.mp3
|
يَشْهَدُهُ الْمُقَرَّبُونَ |
| 22 |
እውነተኞቹ ምእምናን በእርግጥ በድሎት (ገነት) ውስጥ ናቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/083022.mp3
|
إِنَّ الْأَبْرَارَ لَفِي نَعِيمٍ |
| 23 |
በባለ አጎበር አልጋዎች ላይ ኾነው ይመለከታሉ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/083023.mp3
|
عَلَى الْأَرَائِكِ يَنظُرُونَ |
| 24 |
በፊቶቻቸው ላይ የድሎትን ውበት ታውቃለህ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/083024.mp3
|
تَعْرِفُ فِي وُجُوهِهِمْ نَضْرَةَ النَّعِيمِ |
| 25 |
ተጣርቶ ከታተመ ጠጅ ይጠጣሉ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/083025.mp3
|
يُسْقَوْنَ مِن رَّحِيقٍ مَّخْتُومٍ |
| 26 |
ማተሚያው ምስክ ከኾነ፤ በዚህም ተሽቀዳዳሚዎች ይሽቀዳደሙ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/083026.mp3
|
خِتَامُهُ مِسْكٌ وَفِي ذَلِكَ فَلْيَتَنَافَسِ الْمُتَنَافِسُونَ |
| 27 |
መበረዣውም ከተስኒም ነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/083027.mp3
|
وَمِزَاجُهُ مِن تَسْنِيمٍ |
| 28 |
ባለሟሎቹ ከእርሷ የሚጠጡላት ምንጭ ናት፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/083028.mp3
|
عَيْنًا يَشْرَبُ بِهَا الْمُقَرَّبُونَ |
| 29 |
እነዚያ ያምመጹት በእነዚያ ባመኑት በእርግጥ ይስቁ ነበሩ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/083029.mp3
|
إِنَّ الَّذِينَ أَجْرَمُوا كَانُواْ مِنَ الَّذِينَ آمَنُوا يَضْحَكُونَ |
| 30 |
በእነርሱም ላይ ባለፉ ጊዜ ይጠቃቀሱ ነበር፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/083030.mp3
|
وَإِذَا مَرُّواْ بِهِمْ يَتَغَامَزُونَ |
| 31 |
ወደ ቤተሰቦቻቸውም በተመለሱ ጊዜ (በመሳለቃቸው) ተደሳቾች ኾነው ይመለሱ ነበር፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/083031.mp3
|
وَإِذَا انقَلَبُواْ إِلَى أَهْلِهِمُ انقَلَبُواْ فَكِهِينَ |
| 32 |
ባዩዋቸውም ጊዜ «እነዚህ በእርግጥ ተሳሳቾች ናቸው» ይሉ ነበር፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/083032.mp3
|
وَإِذَا رَأَوْهُمْ قَالُوا إِنَّ هَؤُلَاء لَضَالُّونَ |
| 33 |
በነርሱ ላይ ተጠባባቂዎች ተደርገው ያልተላኩ ሲኾኑ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/083033.mp3
|
وَمَا أُرْسِلُوا عَلَيْهِمْ حَافِظِينَ |
| 34 |
ዛሬ (በትንሣኤ ቀን) እነዚያ ያመኑት በከሓዲዎቹ ይስቃሉ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/083034.mp3
|
فَالْيَوْمَ الَّذِينَ آمَنُواْ مِنَ الْكُفَّارِ يَضْحَكُونَ |
| 35 |
በባለ አጎበር አልጋዎች ላይ ኾነው የሚመለከቱ ሲኾኑ (ይስቃሉ)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/083035.mp3
|
عَلَى الْأَرَائِكِ يَنظُرُونَ |
| 36 |
ከሓዲዎች ይሠሩት የነበሩትን (ዋጋ) ተመነዱን? (ይላሉ)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/083036.mp3
|
هَلْ ثُوِّبَ الْكُفَّارُ مَا كَانُوا يَفْعَلُونَ |