Al-Infitar

Change Language
Change Surah
Change Recitation

Amharic: Muhammed Sadiq and Muhammed Sani Habib

Play All
# Translation Ayah
1 ሰማይ በተሰነጠቀች ጊዜ፤ إِذَا السَّمَاء انفَطَرَتْ
2 ከዋክብትም ተበታትነው በወደቁ ጊዜ፤ وَإِذَا الْكَوَاكِبُ انتَثَرَتْ
3 ባሕሮችም በተከፈቱና በተደበላለቁ ጊዜ፤ وَإِذَا الْبِحَارُ فُجِّرَتْ
4 መቃብሮችም በተገለባበጡና (ሙታን) በተነሱ ጊዜ፤ وَإِذَا الْقُبُورُ بُعْثِرَتْ
5 ማንኛይቱም ነፍስ ያስቀደመችውንና ያቆየችውን ታውቃለች፡፡ عَلِمَتْ نَفْسٌ مَّا قَدَّمَتْ وَأَخَّرَتْ
6 አንተ ሰው ሆይ! በቸሩ ጌታህ ምን አታለለህ? يَا أَيُّهَا الْإِنسَانُ مَا غَرَّكَ بِرَبِّكَ الْكَرِيمِ
7 በዚያ በፈጠረህ አካለ ሙሉም ባደረገህ ባስተካከለህም፡፡ الَّذِي خَلَقَكَ فَسَوَّاكَ فَعَدَلَكَ
8 በማንኛውም በሻው ቅርፅ በገጣጠመህ (ጌታህ ምን አታለለህ)፡፡ فِي أَيِّ صُورَةٍ مَّا شَاء رَكَّبَكَ
9 ተከልከሉ፤ በእውነቱ በፍርዱ ቀን ታስተባብላላችሁ፡፡ كَلَّا بَلْ تُكَذِّبُونَ بِالدِّينِ
10 በእናንተ ላይ ተጠባባቂዎች ያሉባችሁ፤ ስትኾኑ፤ وَإِنَّ عَلَيْكُمْ لَحَافِظِينَ
11 የተከበሩ ጸሐፊዎች የኾኑ፤ (ተጠባባቂዎች)፡፡ كِرَامًا كَاتِبِينَ
12 የምትሠሩትን ሁሉ የሚያውቁ፡፡ يَعْلَمُونَ مَا تَفْعَلُونَ
13 እውነተኞቹ ምእምናን በእርግጥ በገነት ውስጥ ናቸው፡፡ إِنَّ الْأَبْرَارَ لَفِي نَعِيمٍ
14 ከሓዲዎቹም በእርግጥ በገሀነም ውስጥ ናቸው፡፡ وَإِنَّ الْفُجَّارَ لَفِي جَحِيمٍ
15 በፍርዱ ቀን ይገቧታል፡፡ يَصْلَوْنَهَا يَوْمَ الدِّينِ
16 እነርሱም ከርሷ ራቂዎች አይደሉም፡፡ وَمَا هُمْ عَنْهَا بِغَائِبِينَ
17 የፍርድ ቀን ምን እንደኾነ ምን አሳወቀህ? وَمَا أَدْرَاكَ مَا يَوْمُ الدِّينِ
18 ከዚያም የፍርዱ ቀን ምን እንደኾነ ምን አሳወቀህ? ثُمَّ مَا أَدْرَاكَ مَا يَوْمُ الدِّينِ
19 (እርሱ) ማንኛይቱም ነፍስ ለሌላይቱ ነፍስ ምንም ማድረግን የማትችልበት ቀን ነው፡፡ ነገሩም ሁሉ በዚያ ቀን ለአላህ ብቻ ነው፡፡ يَوْمَ لَا تَمْلِكُ نَفْسٌ لِّنَفْسٍ شَيْئًا وَالْأَمْرُ يَوْمَئِذٍ لِلَّهِ
;