At-Takwir

Change Language
Change Surah
Change Recitation

Amharic: Muhammed Sadiq and Muhammed Sani Habib

Play All
# Translation Ayah
1 ፀሐይ በተጠቀለለች ጊዜ፤ إِذَا الشَّمْسُ كُوِّرَتْ
2 ከዋክብትም በረገፉ ጊዜ፤ وَإِذَا النُّجُومُ انكَدَرَتْ
3 ተራራዎችም በተነዱ ጊዜ፤ وَإِذَا الْجِبَالُ سُيِّرَتْ
4 የዐሥር ወር እርጉዞች ግመሎችም (ያለጠባቂ) በተተዉ ጊዜ፤ وَإِذَا الْعِشَارُ عُطِّلَتْ
5 እንስሳትም ሁሉ በተሰበሰቡ ጊዜ፤ وَإِذَا الْوُحُوشُ حُشِرَتْ
6 ባሕሮችም በተቃጠሉ ጊዜ፤ وَإِذَا الْبِحَارُ سُجِّرَتْ
7 ነፍሶችም (በየአካሎቻቸው) በተቆራኙ ጊዜ፤ وَإِذَا النُّفُوسُ زُوِّجَتْ
8 በሕይወቷ የተቀበረችውም ሴት ልጅ በተጠየቀች ጊዜ፤ وَإِذَا الْمَوْؤُودَةُ سُئِلَتْ
9 በምን ወንጀል እንደ ተገደለች፤ بِأَيِّ ذَنبٍ قُتِلَتْ
10 ጽሑፎችም በተዘረጉ ጊዜ፤ وَإِذَا الصُّحُفُ نُشِرَتْ
11 ሰማይም በተገሸለጠች ጊዜ፤ وَإِذَا السَّمَاء كُشِطَتْ
12 ገሀነምም በተነደደች ጊዜ፤ وَإِذَا الْجَحِيمُ سُعِّرَتْ
13 ገነትም በተቀረበች ጊዜ፤ وَإِذَا الْجَنَّةُ أُزْلِفَتْ
14 ነፍስ ሁሉ (ከሥራ) ያቀረበችውን ታውቃለች፤ عَلِمَتْ نَفْسٌ مَّا أَحْضَرَتْ
15 ተመላሾችም በኾኑት (ዐዋድያት) እምላለሁ፡፡ فَلَا أُقْسِمُ بِالْخُنَّسِ
16 ኺያጆች ገቢዎች በኾኑት (ከዋክብት)፡፡ الْجَوَارِ الْكُنَّسِ
17 በሌሊቱም (ጨለማውን) በጠነሰሰ ጊዜ፤ وَاللَّيْلِ إِذَا عَسْعَسَ
18 በንጋቱም (በብርሃን) በተነፈሰ ጊዜ፤ (እምላለሁ)፡፡ وَالصُّبْحِ إِذَا تَنَفَّسَ
19 እርሱ (ቁርኣን) የክቡር መልክተኛ ቃል ነው፡፡ إِنَّهُ لَقَوْلُ رَسُولٍ كَرِيمٍ
20 የኀይል ባለቤት በዙፋኑ ባለ ቤት ዘንድ ባለሟል የኾነ፡፡ ذِي قُوَّةٍ عِندَ ذِي الْعَرْشِ مَكِينٍ
21 በዚያ ስፍራ ትእዛዙ ተሰሚ፤ ታማኝ የኾነ (መልክተኛ ቃል) ነው፡፡ مُطَاعٍ ثَمَّ أَمِينٍ
22 ነቢያችሁም በፍጹም ዕብድ አይደለም፡፡ وَمَا صَاحِبُكُم بِمَجْنُونٍ
23 በግልጹ አድማስም በእርግጥ አይቶታል፡፡ وَلَقَدْ رَآهُ بِالْأُفُقِ الْمُبِينِ
24 እርሱም በሩቁ ወሬ ላይ ሰሳች (ንፉግ) አይደለም፡፡ وَمَا هُوَ عَلَى الْغَيْبِ بِضَنِينٍ
25 እርሱም (ቁርኣን) የእርጉም ሰይጣን ቃል አይደለም፡፡ وَمَا هُوَ بِقَوْلِ شَيْطَانٍ رَجِيمٍ
26 ታዲያ ወዴት ትኼዳላችሁ? فَأَيْنَ تَذْهَبُونَ
27 እርሱ የዓለማት መገሠጫ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ إِنْ هُوَ إِلَّا ذِكْرٌ لِّلْعَالَمِينَ
28 ከናንተ ቀጥተኛ መኾንን ለሻ ሰው (መገሰጫ ነው)፡፡ لِمَن شَاء مِنكُمْ أَن يَسْتَقِيمَ
29 የዓለማት ጌታ አላህ ካልሻም አትሹም፡፡ وَمَا تَشَاؤُونَ إِلَّا أَن يَشَاء اللَّهُ رَبُّ الْعَالَمِينَ
;