Abasa

Change Language
Change Surah
Change Recitation

Amharic: Muhammed Sadiq and Muhammed Sani Habib

Play All
# Translation Ayah
1 ፊቱን አጨፈገገ፤ ዞረም፡፡ عَبَسَ وَتَوَلَّى
2 ዕውሩ ስለ መጣው፡፡ أَن جَاءهُ الْأَعْمَى
3 ምን ያሳውቅሃል? (ከኀጢአቶቹ) ሊጥራራ ይከጀላል፡፡ وَمَا يُدْرِيكَ لَعَلَّهُ يَزَّكَّى
4 ወይም ሊገሠጽ ግሠጼይቱም ልትጠቅመው (ይከጀላል)፡፡ أَوْ يَذَّكَّرُ فَتَنفَعَهُ الذِّكْرَى
5 የተብቃቃው ሰውማ፤ أَمَّا مَنِ اسْتَغْنَى
6 አንተ ለእርሱ (ለእምነቱ በመጓጓት) በፈገግታ ትቀበለዋለህ፡፡ فَأَنتَ لَهُ تَصَدَّى
7 ባይጥራራ (ባያምን) ባንተ ላይ ምንም የሌለብህ ስትኾን፡፡ وَمَا عَلَيْكَ أَلَّا يَزَّكَّى
8 እየገሰገሰ የመጣህ ሰውማ፤ وَأَمَّا مَن جَاءكَ يَسْعَى
9 እርሱ (አላህን) የሚፈራ ሲኾን፤ وَهُوَ يَخْشَى
10 አንተ ከእርሱ ትዝዘናጋለህ፡፡ فَأَنتَ عَنْهُ تَلَهَّى
11 ተከልከል፡፡ እርሷ ማስገንዘቢያ ናት፡፡ كَلَّا إِنَّهَا تَذْكِرَةٌ
12 የሻም ሰው (ቁርኣኑን) ያስታውሰዋል፡፡ فَمَن شَاء ذَكَرَهُ
13 በተከበሩ ጽሑፎች ውስጥ ነው፡፡ فِي صُحُفٍ مُّكَرَّمَةٍ
14 ከፍ በተደረገች ንጹሕ በተደረገች (ጽሑፍ ውስጥ ነው)፡፡ مَّرْفُوعَةٍ مُّطَهَّرَةٍ
15 በጸሐፊዎቹ (መላእክት) እጆች (ንጹሕ የተደረገች)፡፡ بِأَيْدِي سَفَرَةٍ
16 የተከበሩና ታዛዦች በኾኑት (ጸሐፊዎች እጆች)፡፡ كِرَامٍ بَرَرَةٍ
17 ሰው ተረገመ፤ ምን ከሓዲ አደረገው? قُتِلَ الْإِنسَانُ مَا أَكْفَرَهُ
18 (ጌታው) በምን ነገር ፈጠረው? (አያስብምን?) مِنْ أَيِّ شَيْءٍ خَلَقَهُ
19 ከፍትወት ጠብታ ፈጠረው፤ መጠነውም፡፡ مِن نُّطْفَةٍ خَلَقَهُ فَقَدَّرَهُ
20 ከዚያም (መውጫ) መንገዱን አገራው፡፡ ثُمَّ السَّبِيلَ يَسَّرَهُ
21 ከዚያም ገደለው፤ እንዲቀበርም አደረገው፡፡ ثُمَّ أَمَاتَهُ فَأَقْبَرَهُ
22 ከዚያም (ማንሳቱን) በሻ ጊዜ ያስነሳዋል፡፡ ثُمَّ إِذَا شَاء أَنشَرَهُ
23 በእውነት ያንን (ጌታው) ያዘዘውን ገና አልፈጸመም፡፡ كَلَّا لَمَّا يَقْضِ مَا أَمَرَهُ
24 ሰውም ወደ ምግቡ ይመልከት፡፡ فَلْيَنظُرِ الْإِنسَانُ إِلَى طَعَامِهِ
25 እኛ ውሃን ማንቧቧትን ያንቧቧን መኾናችንን፡፡ أَنَّا صَبَبْنَا الْمَاء صَبًّا
26 ከዚያም ምድርን (በደካማ ቡቃያ) መሰንጠቅን የሰነጠቅን፤ ثُمَّ شَقَقْنَا الْأَرْضَ شَقًّا
27 በውስጧም እኽልን ያበቀልን፤ فَأَنبَتْنَا فِيهَا حَبًّا
28 ወይንንም፤ እርጥብ ያበቀልን፤ وَعِنَبًا وَقَضْبًا
29 የዘይት ወይራንም ዘንባባንም፤ وَزَيْتُونًا وَنَخْلًا
30 ጭፍቆች አትክልቶችንም፤ وَحَدَائِقَ غُلْبًا
31 ፍራፍሬንም ገለባንም፤ (ያበቀልን መኾናችንን ይመልከት)፡፡ وَفَاكِهَةً وَأَبًّا
32 ለእናንተም ለእንስሶቻችሁም መጠቀሚያ ይኾን ዘንድ (ይህን ሠራን)፡፡ مَّتَاعًا لَّكُمْ وَلِأَنْعَامِكُمْ
33 አደንቋሪይቱም (መከራ) በመጣች ጊዜ፤ فَإِذَا جَاءتِ الصَّاخَّةُ
34 ሰው ከወንድሙ በሚሸሽበት ቀን፤ يَوْمَ يَفِرُّ الْمَرْءُ مِنْ أَخِيهِ
35 ከናቱም ካባቱም፤ وَأُمِّهِ وَأَبِيهِ
36 ከሚስቱም ከልጁም፤ وَصَاحِبَتِهِ وَبَنِيهِ
37 ከእነርሱ ለየሰው ሁሉ በዚያ ቀን (ከሌላው) የሚያብቃቃው ኹነታ አልለው፡፡ لِكُلِّ امْرِئٍ مِّنْهُمْ يَوْمَئِذٍ شَأْنٌ يُغْنِيهِ
38 ፊቶች በዚያ ቀን አብሪዎች ናቸው፤ وُجُوهٌ يَوْمَئِذٍ مُّسْفِرَةٌ
39 ሳቂዎችም ተደሳቾችም ናቸው፡፡ ضَاحِكَةٌ مُّسْتَبْشِرَةٌ
40 ፊቶችም በዚያ ቀን በላያቸው ላይ ትቢያ አልለባቸው፤ وَوُجُوهٌ يَوْمَئِذٍ عَلَيْهَا غَبَرَةٌ
41 ጥቁረት ትሸፍናቸዋለች፤ تَرْهَقُهَا قَتَرَةٌ
42 እነዚያ እነሱ ከሓዲዎቹ አመጸኞቹ ናቸው፡፡ أُوْلَئِكَ هُمُ الْكَفَرَةُ الْفَجَرَةُ
;