An-Nazi'at

Change Language
Change Surah
Change Recitation

Amharic: Muhammed Sadiq and Muhammed Sani Habib

Play All
# Translation Ayah
1 በኃይል አውጪዎች በኾኑት፤ وَالنَّازِعَاتِ غَرْقًا
2 በቀስታ መምዘዝንም መዘዦች በኾኑት፤ وَالنَّاشِطَاتِ نَشْطًا
3 መዋኘትም ዋኚዎች በኾኑት፤ وَالسَّابِحَاتِ سَبْحًا
4 መቅደምንም ቀዳሚዎች በኾኑት፤ فَالسَّابِقَاتِ سَبْقًا
5 ነገርንም አስተናባሪዎች በኾኑት (መላእክት) እምላለሁ፡፡ (በእርግጥ ትቀሰቀሳላችሁ)፡፡ فَالْمُدَبِّرَاتِ أَمْرًا
6 ተርገፍጋፊይቱ (ምድር) በምትርገፈገፍበት ቀን፤ يَوْمَ تَرْجُفُ الرَّاجِفَةُ
7 ለጣቂይቱ የምትከተላት ስትኾን (ትቀሰቀሳላችሁ)፡፡ تَتْبَعُهَا الرَّادِفَةُ
8 በዚያ ቀን ልቦች ተሸባሪዎች ናቸው፡፡ قُلُوبٌ يَوْمَئِذٍ وَاجِفَةٌ
9 ዓይኖቻቸው ተዋራጆች (አቀርቃሪዎች) ናቸው፡፡ أَبْصَارُهَا خَاشِعَةٌ
10 «እኛ ወደ መጀመሪያይቱ ኹነታ ተመላሾች ነን?» ይላሉ፡፡ يَقُولُونَ أَئِنَّا لَمَرْدُودُونَ فِي الْحَافِرَةِ
11 «የበሰበሱ አጥንቶች በኾን ጊዜ (እንቀሰቀሳለን?)» أَئِذَا كُنَّا عِظَامًا نَّخِرَةً
12 «ይህቺ ያን ጊዜ ባለ ከሳራ መመለስ ናት» ይላሉ፡፡ قَالُوا تِلْكَ إِذًا كَرَّةٌ خَاسِرَةٌ
13 እርሷም አንዲት ጩኸት ብቻ ናት፡፡ فَإِنَّمَا هِيَ زَجْرَةٌ وَاحِدَةٌ
14 ወዲያውኑም እነርሱ እንቅልፍ በሌለባት (ምድር) ላይ ይኾናሉ፡፡ فَإِذَا هُم بِالسَّاهِرَةِ
15 የሙሳ ወሬ መጣልህን? هَلْ أتَاكَ حَدِيثُ مُوسَى
16 ጌታው በተቀደሰው ሸለቆ በጡዋ በጠራው ጊዜ፤ إِذْ نَادَاهُ رَبُّهُ بِالْوَادِ الْمُقَدَّسِ طُوًى
17 ወደ ፈርዖን ኺድ፡፡ እርሱ ወሰን አልፏልና፡፡ اذْهَبْ إِلَى فِرْعَوْنَ إِنَّهُ طَغَى
18 በለውም፡- «ወደ መጥራራትህ ላንተ (መንገድ) አለህን?» فَقُلْ هَل لَّكَ إِلَى أَن تَزَكَّى
19 «ወደ ጌታህም ልመራህ ትፈራውም ዘንድ፤ (መንገድ አለህን?)» አለው፡፡ وَأَهْدِيَكَ إِلَى رَبِّكَ فَتَخْشَى
20 ታላቂቱንም ተዓምር አሳየው፡፡ فَأَرَاهُ الْآيَةَ الْكُبْرَى
21 አስተባበለም፤ አመጸም፡፡ فَكَذَّبَ وَعَصَى
22 ከዚያም (ለማጥፋት) የሚተጋ ኾኖ ዞረ፡፡ ثُمَّ أَدْبَرَ يَسْعَى
23 (ሰራዊቶቹን) ሰበሰበም፤ ተጣራም፡፡ فَحَشَرَ فَنَادَى
24 አለም፡- «እኔ ታላቁ ጌታችሁ ነኝ፡፡» فَقَالَ أَنَا رَبُّكُمُ الْأَعْلَى
25 አላህም በኋለኛይቱና በፊተኛይቱ (ቃል) ቅጣት ያዘው፡፡ فَأَخَذَهُ اللَّهُ نَكَالَ الْآخِرَةِ وَالْأُولَى
26 በዚህ ውስጥ ለሚፈራ ሰው በእርግጥ መገምገሚያ አለበት፡፡ إِنَّ فِي ذَلِكَ لَعِبْرَةً لِّمَن يَخْشَى
27 ባፈጣጠር እናንተ ይበልጥ የበረታችሁ ናችሁን? ወይንስ ሰማይ? (አላህ) ገነባት፡፡ أَأَنتُمْ أَشَدُّ خَلْقًا أَمِ السَّمَاء بَنَاهَا
28 ከፍታዋን አጓነ፤ አስተካከላትም፡፡ رَفَعَ سَمْكَهَا فَسَوَّاهَا
29 ሌሊቷንም አጨለመ፡፡ ቀንዋንም ገለጸ፡፡ وَأَغْطَشَ لَيْلَهَا وَأَخْرَجَ ضُحَاهَا
30 ምድርንም ከዚህ በኋላ ዘረጋት፡፡ وَالْأَرْضَ بَعْدَ ذَلِكَ دَحَاهَا
31 ውሃዋንና ግጦሿን ከእርሷ አወጣ፡፡ أَخْرَجَ مِنْهَا مَاءهَا وَمَرْعَاهَا
32 ጋራዎችንም አደላደላቸው፡፡ وَالْجِبَالَ أَرْسَاهَا
33 ለእናንተና ለእንስሶቻችሁ መጣቀሚያ ይኾን ዘንድ (ይህን አደረገ)፡፡ مَتَاعًا لَّكُمْ وَلِأَنْعَامِكُمْ
34 ታላቂቱም መዐት በመጣች ጊዜ፣ فَإِذَا جَاءتِ الطَّامَّةُ الْكُبْرَى
35 ሰው ሁሉ የሠራውን በሚያስታውስበት ቀን፣ يَوْمَ يَتَذَكَّرُ الْإِنسَانُ مَا سَعَى
36 ገሀነምም ለሚያይ ሰው በተገለጠች ጊዜ፣ وَبُرِّزَتِ الْجَحِيمُ لِمَن يَرَى
37 የካደ ሰውማ፣ فَأَمَّا مَن طَغَى
38 ቅርቢቱንም ሕይወት የመረጠ፣ وَآثَرَ الْحَيَاةَ الدُّنْيَا
39 ገሀነም እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት፡፡ فَإِنَّ الْجَحِيمَ هِيَ الْمَأْوَى
40 በጌታው ፊት መቆምን የፈራ ሰውማ ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ وَأَمَّا مَنْ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِ وَنَهَى النَّفْسَ عَنِ الْهَوَى
41 ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት፡፡ فَإِنَّ الْجَنَّةَ هِيَ الْمَأْوَى
42 «ከሰዓቲቱ መቼ ነው መኾኛዋ?» ሲሉ ይጠይቁሃል፡፡ يَسْأَلُونَكَ عَنِ السَّاعَةِ أَيَّانَ مُرْسَاهَا
43 አንተ እርሷን ከማስታወስ በምን ውስጥ ነህ? فِيمَ أَنتَ مِن ذِكْرَاهَا
44 (የዕውቀት) መጨረሻዋ ወደ ጌታህ ብቻ ነው፡፡ إِلَى رَبِّكَ مُنتَهَاهَا
45 አንተ የሚፈራትን ሰው አስፈራሪ ብቻ ነህ፡፡ إِنَّمَا أَنتَ مُنذِرُ مَن يَخْشَاهَا
46 እነርሱ በሚያዩዋት ቀን ያንዲት ቀን ምሽትን ወይም ረፏዷን እንጅ ያልቆዩ ይመስላሉ፡፡ كَأَنَّهُمْ يَوْمَ يَرَوْنَهَا لَمْ يَلْبَثُوا إِلَّا عَشِيَّةً أَوْ ضُحَاهَا
;