An-Nabaa

Change Language
Change Surah
Change Recitation

Amharic: Muhammed Sadiq and Muhammed Sani Habib

Play All
# Translation Ayah
1 ከምን ነገር ይጠያየቃሉ? عَمَّ يَتَسَاءلُونَ
2 ከታላቁ ዜና (ከቁርኣን ይጠያየቃሉ)፡፡ عَنِ النَّبَإِ الْعَظِيمِ
3 ከዚያ እነርሱ በእርሱ የተለያዩበት ከኾነው፡፡ الَّذِي هُمْ فِيهِ مُخْتَلِفُونَ
4 ይከልከሉ፤ ወደፊት (የሚደርስበቸውን) በእርግጥ ያውቃሉ፡፡ كَلَّا سَيَعْلَمُونَ
5 ከዚያም ይከልከሉ፤ ወደፊት ያውቃሉ፡፡ ثُمَّ كَلَّا سَيَعْلَمُونَ
6 ምድርን ምንጣፍ አላደረግንምን? أَلَمْ نَجْعَلِ الْأَرْضَ مِهَادًا
7 ጋራዎችንም ችካሎች አላደረግንምን? وَالْجِبَالَ أَوْتَادًا
8 ብዙ ዓይነቶችም አድርገን ፈጠርናችሁ፡፡ وَخَلَقْنَاكُمْ أَزْوَاجًا
9 እንቅልፋችሁንም ዕረፍት አደረግን፡፡ وَجَعَلْنَا نَوْمَكُمْ سُبَاتًا
10 ሌሊቱንም ልባስ አደረግን፡፡ وَجَعَلْنَا اللَّيْلَ لِبَاسًا
11 ቀኑንም (ለኑሮ) መስሪያ አደረግን፡፡ وَجَعَلْنَا النَّهَارَ مَعَاشًا
12 ከበላያችሁም ሰባትን ብርቱዎች (ሰማያት) ገነባን፡፡ وَبَنَيْنَا فَوْقَكُمْ سَبْعًا شِدَادًا
13 አንጸባራቂ ብርሃንንም አደረግን፡፡ وَجَعَلْنَا سِرَاجًا وَهَّاجًا
14 ከአረገዙት ደመናዎችም ተንቧቢ ውሃን አወረድን፡፡ وَأَنزَلْنَا مِنَ الْمُعْصِرَاتِ مَاء ثَجَّاجًا
15 በእርሱ እኽልንና ቅጠላ ቅጠልን እናወጣ ዘንድ (አወረድን)፡፡ لِنُخْرِجَ بِهِ حَبًّا وَنَبَاتًا
16 የተቆላለፉ አትክልቶችንም፡፡ وَجَنَّاتٍ أَلْفَافًا
17 የመለያው ቀን የተወሰነ ጊዜ ነው፡፡ إِنَّ يَوْمَ الْفَصْلِ كَانَ مِيقَاتًا
18 በቀንዱ በሚነፋና የተለያዩ ጭፍሮች ኾናችሁ በምትመጡ ቀን ነው፡፡ يَوْمَ يُنفَخُ فِي الصُّورِ فَتَأْتُونَ أَفْوَاجًا
19 ሰማይም በምትከፈትና (ባለ) ደጃፎችም በምትኾንበት፡፡ وَفُتِحَتِ السَّمَاء فَكَانَتْ أَبْوَابًا
20 ጋራዎችም በሚነዱበት (እንደ) ሲሪብዱም በሚኾኑበት (ቀን) ነው፡፡ وَسُيِّرَتِ الْجِبَالُ فَكَانَتْ سَرَابًا
21 ገሀነም መጠባበቂያ (ስፍራ) ናት፡፡ إِنَّ جَهَنَّمَ كَانَتْ مِرْصَادًا
22 ለሕግ ተላላፊዎች መመለሻ ስትኾን፡፡ لِلْطَّاغِينَ مَآبًا
23 በውስጧ ብዙን ዘመናት ነዋሪዎች ሲኾኑ፤ لَابِثِينَ فِيهَا أَحْقَابًا
24 በውስጧ ቅዝቃዜንም መጠጥንም አይቀምሱም፡፡ لَّا يَذُوقُونَ فِيهَا بَرْدًا وَلَا شَرَابًا
25 ግን ሙቅ ውሃንና እዥን (ይቀምሳሉ)፡፡ إِلَّا حَمِيمًا وَغَسَّاقًا
26 ተስማሚን ምንዳ ይምመነዳሉ፡፡ جَزَاء وِفَاقًا
27 እነርሱ ምርመራን የማይፈሩ ነበሩና፡፡ إِنَّهُمْ كَانُوا لَا يَرْجُونَ حِسَابًا
28 በአንቀጾቻችንም ማስተባበልን አስተባበሉና፡፡ وَكَذَّبُوا بِآيَاتِنَا كِذَّابًا
29 ነገሩንም ሁሉ የተጻፈ ሲኾን አጠቃለልነው፡፡ وَكُلَّ شَيْءٍ أَحْصَيْنَاهُ كِتَابًا
30 ቅመሱም ቅጣትንም እንጅ (ሌላን) አንጨምራችሁም (ይባላሉ)፡፡ فَذُوقُوا فَلَن نَّزِيدَكُمْ إِلَّا عَذَابًا
31 ለጥንቁቆቹ መዳኛ ስፍራ አልላቸው፡፡ إِنَّ لِلْمُتَّقِينَ مَفَازًا
32 አትክልቶችና ወይኖችም፡፡ حَدَائِقَ وَأَعْنَابًا
33 እኩያዎች የኾኑ ጡተ ጉቻማዎችም፡፡ وَكَوَاعِبَ أَتْرَابًا
34 የተሞሉ ብርጭቆዎችም፡፡ وَكَأْسًا دِهَاقًا
35 በውስጧ ትርፍ ቃልንም ማስዋሸትንም አይሰሙም፡፡ لَّا يَسْمَعُونَ فِيهَا لَغْوًا وَلَا كِذَّابًا
36 ከጌታህ የኾነን ምንዳ በቂ ስጦታን (ተሰጡ)፡፡ جَزَاء مِّن رَّبِّكَ عَطَاء حِسَابًا
37 የሰማያትና የምድር በመካከላቸውም ያለው ሁሉ ጌታ በጣም አዛኝ ከኾነው (ተመነዱ)፡፡ ከእርሱ ጋር መነጋገርን አይችሉም፡፡ رَبِّ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَمَا بَيْنَهُمَا الرحْمَنِ لَا يَمْلِكُونَ مِنْهُ خِطَابًا
38 መንፈሱ (ጂብሪል) መላእክቶቹም የተሰለፉ ኾነው በሚቆሙ ቀን አል-ረሕማን ለእርሱ የፈቀደለትና ትክክለኛን ቃል ያለ ሰው ቢኾን እንጅ (መነጋገርን አይችሉም)፡፡ يَوْمَ يَقُومُ الرُّوحُ وَالْمَلَائِكَةُ صَفًّا لَّا يَتَكَلَّمُونَ إِلَّا مَنْ أَذِنَ لَهُ الرحْمَنُ وَقَالَ صَوَابًا
39 ይህ የተረጋገጠው ቀን ነው፡፡ የሻም ሰው ወደ ጌታው መመለስን ይይዛል፡፡ ذَلِكَ الْيَوْمُ الْحَقُّ فَمَن شَاء اتَّخَذَ إِلَى رَبِّهِ مَآبًا
40 እኛ ሰው ሁሉ እጆቹ ያስቀደሙትን በሚያይበትና ከሓዲውም ዋ ምኞቴ! ምንነው ዐፈር በኾንኩ በሚልበት ቀን ቅርብ የኾነን ቅጣት አስጠነቀቅናችሁ፡፡ إِنَّا أَنذَرْنَاكُمْ عَذَابًا قَرِيبًا يَوْمَ يَنظُرُ الْمَرْءُ مَا قَدَّمَتْ يَدَاهُ وَيَقُولُ الْكَافِرُ يَا لَيْتَنِي كُنتُ تُرَابًا
;