Al-Ma'arij

Change Language
Change Surah
Change Recitation

Amharic: Muhammed Sadiq and Muhammed Sani Habib

Play All
# Translation Ayah
1 ወዳቂ ከኾነው ቅጣት ጠያቂ ጠየቀ፡፡ سَأَلَ سَائِلٌ بِعَذَابٍ وَاقِعٍ
2 በከሓዲዎች ላይ (ወዳቂ ከኾነው) ለእርሱ መላሽ የለውም፡፡ لِّلْكَافِرينَ لَيْسَ لَهُ دَافِعٌ
3 የ(ሰማያት) መሰላሎች ባለቤት ከኾነው አላህ (መላሽ የለውም)፡፡ مِّنَ اللَّهِ ذِي الْمَعَارِجِ
4 መላእክቱና መንፈሱም ልኩ አምሳ ሺሕ ዓመት በኾነ ቀን ውስጥ ወደእርሱ ያርጋሉ፤ (ይወጣሉ)፡፡ تَعْرُجُ الْمَلَائِكَةُ وَالرُّوحُ إِلَيْهِ فِي يَوْمٍ كَانَ مِقْدَارُهُ خَمْسِينَ أَلْفَ سَنَةٍ
5 መልካምንም ትዕግስት ታገሥ፡፡ فَاصْبِرْ صَبْرًا جَمِيلًا
6 እነርሱ (ያንን ቀን) ሩቅ አድርገው ያዩታል፡፡ إِنَّهُمْ يَرَوْنَهُ بَعِيدًا
7 እኛም ቅርብ ኾኖ እናየዋለን፡፡ وَنَرَاهُ قَرِيبًا
8 ሰማይ እንደ ዘይት አተላ በምትኾንበት ቀን፡፡ يَوْمَ تَكُونُ السَّمَاء كَالْمُهْلِ
9 ጋራዎችም በተለያዩ ቀለማት እንደ ተነከረ ሱፍ (ነፋስ እንደሚያበረው) በሚኾኑበት ቀን፡፡ وَتَكُونُ الْجِبَالُ كَالْعِهْنِ
10 ዘመድም ዘመድን በማይጠይቅበት ቀን፤ (መላሽ የለውም)፡፡ وَلَا يَسْأَلُ حَمِيمٌ حَمِيمًا
11 (ዘመዶቻቸውን) ያዩዋቸዋል፡፡ አመጸኛው ከዚያ ቀን ስቃይ (ነፍሱን) በልጆቹ ሊበዥ ይመኛል፡፡ يُبَصَّرُونَهُمْ يَوَدُّ الْمُجْرِمُ لَوْ يَفْتَدِي مِنْ عَذَابِ يَوْمِئِذٍ بِبَنِيهِ
12 በሚስቱም በወንድሙም፡፡ وَصَاحِبَتِهِ وَأَخِيهِ
13 በዚያችም በምታስጠጋው ጎሳው፡፡ وَفَصِيلَتِهِ الَّتِي تُؤْويهِ
14 በምድርም ላይ ባለው ሁሉ (ሊበዥ) ከዚያም ሊያድነው (ይመኛል)፡፡ وَمَن فِي الْأَرْضِ جَمِيعًا ثُمَّ يُنجِيهِ
15 ይተው! እርሷ (እሳቲቱ) ለዟ ናት፡፡ كَلَّا إِنَّهَا لَظَى
16 የራስን ቅል ቆዳ የምትሞሽልቅ ስትኾን፡፡ نَزَّاعَةً لِّلشَّوَى
17 (ከእምነት) የዞረንና የሸሸን ሰው (ወደእርሷ) ትጠራለች፡፡ تَدْعُو مَنْ أَدْبَرَ وَتَوَلَّى
18 ገንዘብን የሰበሰበንና (ዘካውን ሳይሰጥ) የቆጠረንም፤ (ትጠራለች)፡፡ وَجَمَعَ فَأَوْعَى
19 ሰው ቅጠ ቢስ ኾኖ ተፈጠረ፡፡ إِنَّ الْإِنسَانَ خُلِقَ هَلُوعًا
20 ክፉ ነገር ባገኘው ጊዜ ብስጪተኛ፡፡ إِذَا مَسَّهُ الشَّرُّ جَزُوعًا
21 መልካምም ነገር (ድሎት) ባገኘ ጊዜ ከልካይ (ኾኖ ተፈጠረ)፡፡ وَإِذَا مَسَّهُ الْخَيْرُ مَنُوعًا
22 ሰጋጆቹ ብቻ ሲቀሩ፡፡ إِلَّا الْمُصَلِّينَ
23 እነዚያ እነርሱ በስግደታቸው ላይ ዘውታሪዎች የኾኑት፡፡ الَّذِينَ هُمْ عَلَى صَلَاتِهِمْ دَائِمُونَ
24 እነዚያም በገንዘቦቻቸው ላይ የታወቀ መብት ያለባቸው የኾኑት፡፡ وَالَّذِينَ فِي أَمْوَالِهِمْ حَقٌّ مَّعْلُومٌ
25 ለለማኝ ከልመና ለሚከለከልም (መብት ያለባቸው የኾኑት)፡፡ لِّلسَّائِلِ وَالْمَحْرُومِ
26 እነዚያም በፍርዱ ቀን እውነት የሚሉት (የሚያረጋግጡት)፡፡ وَالَّذِينَ يُصَدِّقُونَ بِيَوْمِ الدِّينِ
27 እነዚያም እነርሱ ከጌታቸው ቅጣት ፈሪዎች የኾኑት፡፡ وَالَّذِينَ هُم مِّنْ عَذَابِ رَبِّهِم مُّشْفِقُونَ
28 የጌታቸው ቅጣት (መምጣቱ) የማያስተማምን ነውና፡፡ إِنَّ عَذَابَ رَبِّهِمْ غَيْرُ مَأْمُونٍ
29 እነዚያም እነርሱ ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች የኾኑት፡፡ وَالَّذِينَ هُمْ لِفُرُوجِهِمْ حَافِظُونَ
30 በሚስቶቻቸው ወይም እጆቻቸው በያዙዋቸው (ባሪያዎች) ላይ ሲቀር፡፡ እነርሱ (በእነዚህ) የማይወቀሱ ናቸውና፡፡ إِلَّا عَلَى أَزْوَاجِهِمْ أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُهُمْ فَإِنَّهُمْ غَيْرُ مَلُومِينَ
31 ከዚያም ወዲያ የፈለገ ሰው እነዚያ እነሱ ድንበር አላፊዎች ናቸው፡፡ فَمَنِ ابْتَغَى وَرَاء ذَلِكَ فَأُوْلَئِكَ هُمُ الْعَادُونَ
32 እነዚያም እነርሱ አደራዎቻቸውንና ቃል ኪዳናቸውን ጠባቂዎች የኾኑት፡፡ وَالَّذِينَ هُمْ لِأَمَانَاتِهِمْ وَعَهْدِهِمْ رَاعُونَ
33 እነዚያም እነርሱ በምስክርነታቸው ትክክለኞች የኾኑት፡፡ وَالَّذِينَ هُم بِشَهَادَاتِهِمْ قَائِمُونَ
34 እነዚያም እነርሱ በሶላቶቻቸው ላይ የሚጠባበቁት፡፡ وَالَّذِينَ هُمْ عَلَى صَلَاتِهِمْ يُحَافِظُونَ
35 እነዚህ (ከዚህ በላይ የተወሱት ሁሉ) በገነቶች ውስጥ የሚከበሩ ናቸው፡፡ أُوْلَئِكَ فِي جَنَّاتٍ مُّكْرَمُونَ
36 ለእነዚያም ለካዱት ወደ አንተ በኩል አንገቶቻቸውን መዝዘው የሚያተኩሩት ምን አላቸው? فَمَالِ الَّذِينَ كَفَرُوا قِبَلَكَ مُهْطِعِينَ
37 ከቀኝና ከግራ ክፍልፍል ጭፍሮች ሲኾኑ፡፡ عَنِ الْيَمِينِ وَعَنِ الشِّمَالِ عِزِينَ
38 ከእነርሱ እያንዳንዱ ሰው የጸጋይቱን ገነት መግባትን ይከጅላልን? أَيَطْمَعُ كُلُّ امْرِئٍ مِّنْهُمْ أَن يُدْخَلَ جَنَّةَ نَعِيمٍ
39 ይከልከል፤ እኛ ከሚያውቁት ነገር (ከፍቶት ጠብታ) ፈጠርናቸው፡፡ كَلَّا إِنَّا خَلَقْنَاهُم مِّمَّا يَعْلَمُونَ
40 በምሥራቆችና በምዕራቦችም ጌታ እምላለሁ፡፡ እኛ በእርግጥ ቻዮች ነን፡፡ فَلَا أُقْسِمُ بِرَبِّ الْمَشَارِقِ وَالْمَغَارِبِ إِنَّا لَقَادِرُونَ
41 ከእነርሱ የተሻለን በመለወጥ ላይ፡፡ እኛም ተሸናፊዎች አይደለንም፡፡ عَلَى أَن نُّبَدِّلَ خَيْرًا مِّنْهُمْ وَمَا نَحْنُ بِمَسْبُوقِينَ
42 ያንንም የሚስፈራሩበትን ቀናቸውን እስከሚገናኙ ድረስ ተዋቸው፡፡ ይዋኙ ይጫወቱም፡፡ فَذَرْهُمْ يَخُوضُوا وَيَلْعَبُوا حَتَّى يُلَاقُوا يَوْمَهُمُ الَّذِي يُوعَدُونَ
43 ወደ ጣዖቶች እንደሚሽቀዳደሙ ኾነው ከመቃብሮቻቸው ፈጥነው የሚወጡበትን ቀን (እስከሚገናኙ ድረስ ተዋቸው)፡፡ يَوْمَ يَخْرُجُونَ مِنَ الْأَجْدَاثِ سِرَاعًا كَأَنَّهُمْ إِلَى نُصُبٍ يُوفِضُونَ
44 ዓይኖቻቸው ያፈሩ ኾነው ውርደት ትሸፍናቸዋለች፡፡ ይህ ቀን ያ ይስፈራሩበት የነበሩት ነው፡፡ خَاشِعَةً أَبْصَارُهُمْ تَرْهَقُهُمْ ذِلَّةٌ ذَلِكَ الْيَوْمُ الَّذِي كَانُوا يُوعَدُونَ
;