1 |
እኛ ኑሕን «ሕዝቦችህን አሳማሚ ቅጣት ሳይመጣባቸው በፊት አስጠንቅቅ በማለት ወደ ሕዝቦቹ ላክነው፡፡» |
/content/ayah/audio/hudhaify/071001.mp3
|
إِنَّا أَرْسَلْنَا نُوحًا إِلَى قَوْمِهِ أَنْ أَنذِرْ قَوْمَكَ مِن قَبْلِ أَن يَأْتِيَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ |
2 |
(እርሱም) አለ «ሕዝቦቼ ሆይ! እኔ ለእናንተ ገላጭ የኾንኩ አስጠንቃቂ ነኝ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/071002.mp3
|
قَالَ يَا قَوْمِ إِنِّي لَكُمْ نَذِيرٌ مُّبِينٌ |
3 |
«አላህን ተገዙት፣ ፍሩትም፣ ታዘዙኝም በማለት፤ (አስጠንቃቂ ነኝ)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/071003.mp3
|
أَنِ اعْبُدُوا اللَّهَ وَاتَّقُوهُ وَأَطِيعُونِ |
4 |
«ለእናንተ ከኀጢኣቶቻችሁ ይምራልና፡፡ ወደተወሰነው ጊዜም ያቆያችኋል፡፡ የአላህ (የወሰነው) ጊዜ በመጣ ወቅት አይቆይም፡፡ የምታውቁት ብትኾኑ ኖሮ (በታዘዛችሁ ነበር)፡፡» |
/content/ayah/audio/hudhaify/071004.mp3
|
يَغْفِرْ لَكُم مِّن ذُنُوبِكُمْ وَيُؤَخِّرْكُمْ إِلَى أَجَلٍ مُّسَمًّى إِنَّ أَجَلَ اللَّهِ إِذَا جَاء لَا يُؤَخَّرُ لَوْ كُنتُمْ تَعْلَمُونَ |
5 |
(ስለ ተቃወሙትም) «አለ ጌታዬ ሆይ! እኔ ሌሊትም ቀንም ሕዝቦቼን ጠራሁ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/071005.mp3
|
قَالَ رَبِّ إِنِّي دَعَوْتُ قَوْمِي لَيْلًا وَنَهَارًا |
6 |
«ጥሪየም መሸሽን እንጅ ሌላ አልጨመረላቸውም፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/071006.mp3
|
فَلَمْ يَزِدْهُمْ دُعَائِي إِلَّا فِرَارًا |
7 |
«እኔም ለእነርሱ ትምር ዘንድ (ወደ እምነት) በጠራኋቸው ቁጥር ጣቶቻቸውን በጆሮዎቻቸው ውስጥ አደረጉ፡፡ ልብሶቻቸውንም ተከናነቡ፡፡ (በመጥፎ ሥራቸው ላይ) ዘወተሩም፡፡ (ያለ ልክ) መኩራትንም ኮሩ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/071007.mp3
|
وَإِنِّي كُلَّمَا دَعَوْتُهُمْ لِتَغْفِرَ لَهُمْ جَعَلُوا أَصَابِعَهُمْ فِي آذَانِهِمْ وَاسْتَغْشَوْا ثِيَابَهُمْ وَأَصَرُّوا وَاسْتَكْبَرُوا اسْتِكْبَارًا |
8 |
«ከዚያም እኔ በጩኸት ጠራኋቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/071008.mp3
|
ثُمَّ إِنِّي دَعَوْتُهُمْ جِهَارًا |
9 |
«ከዚያም እኔ ለእነርሱ ገለጽኩ፡፡ ለእነርሱም መመስጠርን መሰጠርኩ |
/content/ayah/audio/hudhaify/071009.mp3
|
ثُمَّ إِنِّي أَعْلَنتُ لَهُمْ وَأَسْرَرْتُ لَهُمْ إِسْرَارًا |
10 |
«አልኳቸውም፡- ጌታችሁን ምሕረትን ለምኑት፡፡ እርሱ በጣም መሐሪ ነውና፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/071010.mp3
|
فَقُلْتُ اسْتَغْفِرُوا رَبَّكُمْ إِنَّهُ كَانَ غَفَّارًا |
11 |
«በእናንተ ላይ ዝናምን ተከታታይ አድርጎ ይልካል፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/071011.mp3
|
يُرْسِلِ السَّمَاء عَلَيْكُم مِّدْرَارًا |
12 |
«በገንዘቦችና በልጆችም ይለግሰላችኋል፡፡ ለእናንተም አትክልቶችን ያደርግላችኋል፡፡ ለእናንተም ወንዞችን ያደርግላችኋል፡፡» |
/content/ayah/audio/hudhaify/071012.mp3
|
وَيُمْدِدْكُمْ بِأَمْوَالٍ وَبَنِينَ وَيَجْعَل لَّكُمْ جَنَّاتٍ وَيَجْعَل لَّكُمْ أَنْهَارًا |
13 |
ለአላህ ልቅናን የማትሹት ለእናንተ ምን አላችሁ? |
/content/ayah/audio/hudhaify/071013.mp3
|
مَّا لَكُمْ لَا تَرْجُونَ لِلَّهِ وَقَارًا |
14 |
በልዩ ልዩ ኹኔታዎች በእርግጥ የፈጠራችሁ ሲኾን፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/071014.mp3
|
وَقَدْ خَلَقَكُمْ أَطْوَارًا |
15 |
አላህ ሰባትን ሰማያት አንዱ ካንዱ በላይ ሲኾን እንዴት እንደፈጠረ አታዩምን? |
/content/ayah/audio/hudhaify/071015.mp3
|
أَلَمْ تَرَوْا كَيْفَ خَلَقَ اللَّهُ سَبْعَ سَمَاوَاتٍ طِبَاقًا |
16 |
በውስጣቸውም ጨረቃን አብሪ አደረገ፡፡ ፀሐይንም ብርሃን አደረገ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/071016.mp3
|
وَجَعَلَ الْقَمَرَ فِيهِنَّ نُورًا وَجَعَلَ الشَّمْسَ سِرَاجًا |
17 |
አላህም ከምድር ማብቀልን አበቀላችሁ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/071017.mp3
|
وَاللَّهُ أَنبَتَكُم مِّنَ الْأَرْضِ نَبَاتًا |
18 |
ከዚያም በውስጧ ይመልሳችኋል፡፡ ማውጣትንም ያወጣችኋል፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/071018.mp3
|
ثُمَّ يُعِيدُكُمْ فِيهَا وَيُخْرِجُكُمْ إِخْرَاجًا |
19 |
አላህም ምድርን ለእናንተ ምንጣፍ አደረጋት፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/071019.mp3
|
وَاللَّهُ جَعَلَ لَكُمُ الْأَرْضَ بِسَاطًا |
20 |
ከእርሷ ሰፋፊዎችን መንገዶች ትገቡ ዘንድ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/071020.mp3
|
لِتَسْلُكُوا مِنْهَا سُبُلًا فِجَاجًا |
21 |
ኑሕ አለ፡- «ጌታዬ ሆይ! እነሱ አምመጹብኝ፡፡ ገንዘቡና ልጁም ከጥፋት በስተቀር ያልጨመረለትን ሰው ተከተሉ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/071021.mp3
|
قَالَ نُوحٌ رَّبِّ إِنَّهُمْ عَصَوْنِي وَاتَّبَعُوا مَن لَّمْ يَزِدْهُ مَالُهُ وَوَلَدُهُ إِلَّا خَسَارًا |
22 |
«ታላቅንም ተንኮል የመከሩትን ሰዎች» (ተከተሉ)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/071022.mp3
|
وَمَكَرُوا مَكْرًا كُبَّارًا |
23 |
አሉም «አምላኮቻችሁን አትተዉ፡፡ ወድንም፣ ሱዋዕንም፣ የጉሥንም፣ የዑቅንም ነስርንም አትተው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/071023.mp3
|
وَقَالُوا لَا تَذَرُنَّ آلِهَتَكُمْ وَلَا تَذَرُنَّ وَدًّا وَلَا سُوَاعًا وَلَا يَغُوثَ وَيَعُوقَ وَنَسْرًا |
24 |
«በእርግጥም ብዙዎችን አሳሳቱ፡፡ ከሓዲዎችንም ጥመትን እንጅ ሌላን አትጨምርላቸው» (አለ)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/071024.mp3
|
وَقَدْ أَضَلُّوا كَثِيراً وَلَا تَزِدِ الظَّالِمِينَ إِلَّا ضَلَالًا |
25 |
በኀጢኣቶቻቸው ምክንያት ተሰጠሙ፡፡ እሳትንም እንዲገቡ ተደረጉ፡፡ ለእነርሱም ከአላህ ሌላ የኾኑ ረዳቶችን አላገኙም፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/071025.mp3
|
مِمَّا خَطِيئَاتِهِمْ أُغْرِقُوا فَأُدْخِلُوا نَارًا فَلَمْ يَجِدُوا لَهُم مِّن دُونِ اللَّهِ أَنصَارًا |
26 |
ኑሕም አለ «ጌታዬ ሆይ! ከከሓዲዎቹ በምድር ላይ አንድንም አትተው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/071026.mp3
|
وَقَالَ نُوحٌ رَّبِّ لَا تَذَرْ عَلَى الْأَرْضِ مِنَ الْكَافِرِينَ دَيَّارًا |
27 |
«አንተ ብትተዋቸው ባሮችህን ያሳስታሉና፡፡ ኀጢኣተኛ ከሓዲንም እንጅ ሌላን አይወልዱም፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/071027.mp3
|
إِنَّكَ إِن تَذَرْهُمْ يُضِلُّوا عِبَادَكَ وَلَا يَلِدُوا إِلَّا فَاجِرًا كَفَّارًا |
28 |
«ጌታዬ ሆይ! ለእኔም ለወላጆቼም ምእመን ኾኖ በቤቴ ለገባም ሰው ሁሉ ለምእመናንና ለምእምናትም ምሕረት አድርግ፡፡ ከሓዲዎችንም ከጥፋት በቀር አትጨምርላቸው፤» (አለ)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/071028.mp3
|
رَبِّ اغْفِرْ لِي وَلِوَالِدَيَّ وَلِمَن دَخَلَ بَيْتِيَ مُؤْمِنًا وَلِلْمُؤْمِنِينَ وَالْمُؤْمِنَاتِ وَلَا تَزِدِ الظَّالِمِينَ إِلَّا تَبَارًا |