| 1 |
ሰዓቲቱ (የትንሣኤ ቀን) ተቃረበች፤ ጨረቃም ተገመሰ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/054001.mp3
|
اقْتَرَبَتِ السَّاعَةُ وَانشَقَّ الْقَمَرُ |
| 2 |
ተዓምርንም ቢያዩ (ከእምነት) ይዞራሉ፡፡ (ይህ) «ዘውታሪ ድግምት ነውም» ይላሉ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/054002.mp3
|
وَإِن يَرَوْا آيَةً يُعْرِضُوا وَيَقُولُوا سِحْرٌ مُّسْتَمِرٌّ |
| 3 |
አስተባበሉም፡፡ ዝንባሌዎቻቸውንም ተከተሉ፡፡ ነገርም ሁሉ (ወሰን አለው)፤ ረጊ ነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/054003.mp3
|
وَكَذَّبُوا وَاتَّبَعُوا أَهْوَاءهُمْ وَكُلُّ أَمْرٍ مُّسْتَقِرٌّ |
| 4 |
ከዜናዎችም በእርሱ ውስጥ መገሰጥ ያለበት ነገር በእርግጥ መጣላቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/054004.mp3
|
وَلَقَدْ جَاءهُم مِّنَ الْأَنبَاء مَا فِيهِ مُزْدَجَرٌ |
| 5 |
ሙሉ የኾነች ጥበብ (መጣቻቸው) ግን አስፈራሪዎቹ አያብቃቁም፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/054005.mp3
|
حِكْمَةٌ بَالِغَةٌ فَمَا تُغْنِ النُّذُرُ |
| 6 |
ከነርሱም ዙር፡፡ ጠሪው (መልአክ) ወደ አስደንጋጭ ነገር የሚጠራበትን ቀን (አስታውስ)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/054006.mp3
|
فَتَوَلَّ عَنْهُمْ يَوْمَ يَدْعُ الدَّاعِ إِلَى شَيْءٍ نُّكُرٍ |
| 7 |
ዓይኖቻቸው ያቀረቀሩ ኾነው፤ ፍጹም የተበተነ አንበጣ መስለው ከመቃብሮቹ ይወጣሉ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/054007.mp3
|
خُشَّعًا أَبْصَارُهُمْ يَخْرُجُونَ مِنَ الْأَجْدَاثِ كَأَنَّهُمْ جَرَادٌ مُّنتَشِرٌ |
| 8 |
ወደ ጠሪው አንገቶቻቸውን ሳቢዎች ቸኳዮች ኾነው (ይወጣሉ)፡፡ ከሓዲዎቹ (ያን ጊዜ ምን ይላሉ?) «ይህ ብርቱ ቀን ነው» ይላሉ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/054008.mp3
|
مُّهْطِعِينَ إِلَى الدَّاعِ يَقُولُ الْكَافِرُونَ هَذَا يَوْمٌ عَسِرٌ |
| 9 |
ከእነርሱ በፊት የኑሕ ነገድ አስተባበለች፡፡ ባሪያችንንም (ኑሕን) አስተባበሉ፡፡ «ዕብድ ነውም» አሉ፡፡ ተገላመጠም፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/054009.mp3
|
كَذَّبَتْ قَبْلَهُمْ قَوْمُ نُوحٍ فَكَذَّبُوا عَبْدَنَا وَقَالُوا مَجْنُونٌ وَازْدُجِرَ |
| 10 |
ጌታውንም «እኔ የተሸነፍኩ ነኝና እርዳኝ» ሲል ጠራ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/054010.mp3
|
فَدَعَا رَبَّهُ أَنِّي مَغْلُوبٌ فَانتَصِرْ |
| 11 |
ወዲያውም የሰማይን ደጃፎች በሚንቧቧ ውሃ ከፈትን፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/054011.mp3
|
فَفَتَحْنَا أَبْوَابَ السَّمَاء بِمَاء مُّنْهَمِرٍ |
| 12 |
የምድርንም ምንጮች አፈነዳን፡፡ ውሃውም (የሰማዩና የምድሩ) በእርግጥ በተወሰነ ኹነታ ላይ ተገናኘ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/054012.mp3
|
وَفَجَّرْنَا الْأَرْضَ عُيُونًا فَالْتَقَى الْمَاء عَلَى أَمْرٍ قَدْ قُدِرَ |
| 13 |
ባለ ሳንቃዎችና ባለሚስማሮች በኾነችም ታንኳ ላይ ጫንነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/054013.mp3
|
وَحَمَلْنَاهُ عَلَى ذَاتِ أَلْوَاحٍ وَدُسُرٍ |
| 14 |
በጥበቃችን ስር ኾና ትንሻለላለች፡፡ ተክዶ ለነበረው ሰው ምንዳ (ይህንን ሠራን)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/054014.mp3
|
تَجْرِي بِأَعْيُنِنَا جَزَاء لِّمَن كَانَ كُفِرَ |
| 15 |
ተዓምር አድርገንም በእርግጥ ተውናት፡፡ ከተገሳጭም አልለን? |
/content/ayah/audio/hudhaify/054015.mp3
|
وَلَقَد تَّرَكْنَاهَا آيَةً فَهَلْ مِن مُّدَّكِرٍ |
| 16 |
ቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼም እንዴት ነበሩ? |
/content/ayah/audio/hudhaify/054016.mp3
|
فَكَيْفَ كَانَ عَذَابِي وَنُذُرِ |
| 17 |
ቁርኣንንም ለመገንዘብ በእርግጥ አገራነው፡፡ ተገንዛቢም አልለን? |
/content/ayah/audio/hudhaify/054017.mp3
|
وَلَقَدْ يَسَّرْنَا الْقُرْآنَ لِلذِّكْرِ فَهَلْ مِن مُّدَّكِرٍ |
| 18 |
ዓድ አስተባበለች፡፡ ቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼም እንዴት ነበሩ! |
/content/ayah/audio/hudhaify/054018.mp3
|
كَذَّبَتْ عَادٌ فَكَيْفَ كَانَ عَذَابِي وَنُذُرِ |
| 19 |
እኛ በእነርሱ ላይ ዘወትር መናጢ በኾነ ቀን በኀይል የምትንሻሻ ነፋስን ላክንባቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/054019.mp3
|
إِنَّا أَرْسَلْنَا عَلَيْهِمْ رِيحًا صَرْصَرًا فِي يَوْمِ نَحْسٍ مُّسْتَمِرٍّ |
| 20 |
ሰዎቹን ልክ ከሥሮቻቸው የተጎለሰሱ የዘንባባ ግንዶች መስለው (ከተደበቁበት) ትነቅላቸዋለች፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/054020.mp3
|
تَنزِعُ النَّاسَ كَأَنَّهُمْ أَعْجَازُ نَخْلٍ مُّنقَعِرٍ |
| 21 |
ቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼም እንዴት ነበሩ? |
/content/ayah/audio/hudhaify/054021.mp3
|
فَكَيْفَ كَانَ عَذَابِي وَنُذُرِ |
| 22 |
ቁርኣንንም ለማስታወስ በእርግጥ አገራነው፡፡ ተገሳጭም አልለን? |
/content/ayah/audio/hudhaify/054022.mp3
|
وَلَقَدْ يَسَّرْنَا الْقُرْآنَ لِلذِّكْرِ فَهَلْ مِن مُّدَّكِرٍ |
| 23 |
ሰሙድ በአስፈራሪዎቹ አስተባበለች፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/054023.mp3
|
كَذَّبَتْ ثَمُودُ بِالنُّذُرِ |
| 24 |
«ከእኛ የኾነን አንድን ሰው እንከተለዋለን? እኛ ያን ጊዜ በስህተትና በዕብደት ውስጥ ነን» አሉ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/054024.mp3
|
فَقَالُوا أَبَشَرًا مِّنَّا وَاحِدًا نَّتَّبِعُهُ إِنَّا إِذًا لَّفِي ضَلَالٍ وَسُعُرٍ |
| 25 |
«ከኛ መካከል በእርሱ ላይ (ብቻ) ማስገንዘቢያ (ራእይ) ተጣለለትን? አይደለም እርሱ ውሸታም ኩሩ ነው» (አሉ)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/054025.mp3
|
أَأُلْقِيَ الذِّكْرُ عَلَيْهِ مِن بَيْنِنَا بَلْ هُوَ كَذَّابٌ أَشِرٌ |
| 26 |
ውሸታሙ ኩሩው ማን እንደኾነ ነገ በእርግጥ ያውቃሉ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/054026.mp3
|
سَيَعْلَمُونَ غَدًا مَّنِ الْكَذَّابُ الْأَشِرُ |
| 27 |
እኛ ሴት ግመልን ለእነርሱ መፈተኛ ትኾን ዘንድ ላኪዎች ነን፡፡ ተጠባበቃቸውም፡፡ ታገስም፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/054027.mp3
|
إِنَّا مُرْسِلُو النَّاقَةِ فِتْنَةً لَّهُمْ فَارْتَقِبْهُمْ وَاصْطَبِرْ |
| 28 |
ውሃውንም በመካከላቸው የተከፈለ መኾኑን ንገራቸው፡፡ ከውሃ የኾነ ፋንታ ሁሉ (ተረኞቹ) የሚጣዱት ነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/054028.mp3
|
وَنَبِّئْهُمْ أَنَّ الْمَاء قِسْمَةٌ بَيْنَهُمْ كُلُّ شِرْبٍ مُّحْتَضَرٌ |
| 29 |
ጓደኛቸውንም ጠሩ፡፡ ወዲያውም (ሰይፍን) ተቀበለ፡፡ ወጋትም፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/054029.mp3
|
فَنَادَوْا صَاحِبَهُمْ فَتَعَاطَى فَعَقَرَ |
| 30 |
ቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼም እንዴት ነበሩ? |
/content/ayah/audio/hudhaify/054030.mp3
|
فَكَيْفَ كَانَ عَذَابِي وَنُذُرِ |
| 31 |
እኛ በእነርሱ ላይ አንዲትን ጩኸት ላክንባቸው፡፡ ወዲያውም ከበረት አጣሪ (አጥር) እንደ ተሰባበረ ርግጋፊ ኾኑ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/054031.mp3
|
إِنَّا أَرْسَلْنَا عَلَيْهِمْ صَيْحَةً وَاحِدَةً فَكَانُوا كَهَشِيمِ الْمُحْتَظِرِ |
| 32 |
ቁርኣንንም ለመገንዘብ አገራነው፡፡ ተገሳጭም አልለን? |
/content/ayah/audio/hudhaify/054032.mp3
|
وَلَقَدْ يَسَّرْنَا الْقُرْآنَ لِلذِّكْرِ فَهَلْ مِن مُّدَّكِرٍ |
| 33 |
የሉጥ ሕዝብ በአስፈራሪዎቹ አስተባበለች፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/054033.mp3
|
كَذَّبَتْ قَوْمُ لُوطٍ بِالنُّذُرِ |
| 34 |
እኛ በእነርሱ ላይ ጠጠርን ያዘለች ነፋስን ላክን፡፡ የሉጥ ቤተሰቦች ብቻ ሲቀሩ (እነርሱንስ) በሌሊት መጨረሻ ላይ አዳንናቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/054034.mp3
|
إِنَّا أَرْسَلْنَا عَلَيْهِمْ حَاصِبًا إِلَّا آلَ لُوطٍ نَّجَّيْنَاهُم بِسَحَرٍ |
| 35 |
ከእኛ በኾነ ጸጋ (አዳንናቸው)፡፡ እንደዚሁ ያመሰገነን ሰው እንመነዳለን፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/054035.mp3
|
نِعْمَةً مِّنْ عِندِنَا كَذَلِكَ نَجْزِي مَن شَكَرَ |
| 36 |
ብርቱይቱን አያያዛችንንም በእርግጥ አስጠነቀቃቸው፡፡ በማስጠንቀቂያዎቹም ተከራከሩ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/054036.mp3
|
وَلَقَدْ أَنذَرَهُم بَطْشَتَنَا فَتَمَارَوْا بِالنُّذُرِ |
| 37 |
ከእንግዶቹም እንዲያስመቻቸው ደጋግመው ፈለጉት፡፡ ወዲያውም ዓይኖቻቸውን አበስን፡፡ «ቅጣቴንና ማስጠንቀቂያዎቼንም ቅመሱ» (አልናቸው)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/054037.mp3
|
وَلَقَدْ رَاوَدُوهُ عَن ضَيْفِهِ فَطَمَسْنَا أَعْيُنَهُمْ فَذُوقُوا عَذَابِي وَنُذُرِ |
| 38 |
በማለዳም ዘውታሪ የኾነ ቅጣት በእርግጥ ማለደባቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/054038.mp3
|
وَلَقَدْ صَبَّحَهُم بُكْرَةً عَذَابٌ مُّسْتَقِرٌّ |
| 39 |
«ቅጣቴንና ማስጠንቀቂያዎቼንም ቅመሱ» (ተባሉ)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/054039.mp3
|
فَذُوقُوا عَذَابِي وَنُذُرِ |
| 40 |
ቁርኣንንም ለመገንዘብ በእርግጥ አገራነው፡፡ ተገሳጭም አልለን? |
/content/ayah/audio/hudhaify/054040.mp3
|
وَلَقَدْ يَسَّرْنَا الْقُرْآنَ لِلذِّكْرِ فَهَلْ مِن مُّدَّكِرٍ |
| 41 |
የፈርዖንንም ቤተሰቦች ማስጠንቀቂያዎች በእርግጥ መጡዋቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/054041.mp3
|
وَلَقَدْ جَاء آلَ فِرْعَوْنَ النُّذُرُ |
| 42 |
በተዓምራቶቻችን በሁሏም አስተባበሉ፡፡ የብርቱ ቻይንም አያያዝ ያዝናቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/054042.mp3
|
كَذَّبُوا بِآيَاتِنَا كُلِّهَا فَأَخَذْنَاهُمْ أَخْذَ عَزِيزٍ مُّقْتَدِرٍ |
| 43 |
ከሓዲዎቻችሁ ከእነዚህ በላጮች ናቸውን? ወይስ ለናንተ በመጽሐፎች ውስጥ (የተነገረ) ነፃነት አላችሁን? |
/content/ayah/audio/hudhaify/054043.mp3
|
أَكُفَّارُكُمْ خَيْرٌ مِّنْ أُوْلَئِكُمْ أَمْ لَكُم بَرَاءةٌ فِي الزُّبُرِ |
| 44 |
ወይስ «እኛ የተረዳን ክምቹዎች ነን» ይላሉን? |
/content/ayah/audio/hudhaify/054044.mp3
|
أَمْ يَقُولُونَ نَحْنُ جَمِيعٌ مُّنتَصِرٌ |
| 45 |
ክምቹዎቹ በእርግጥ ድል ይምመታሉ፡፡ ጀርባዎችንም ያዞራሉ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/054045.mp3
|
سَيُهْزَمُ الْجَمْعُ وَيُوَلُّونَ الدُّبُرَ |
| 46 |
ይልቁንም ሰዓቲቱ (ትንሣኤ) ቀጠሮዋቸው ናት፡፡ ሰዓቲቱም በጣም የከበደችና የመረረች ናት፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/054046.mp3
|
بَلِ السَّاعَةُ مَوْعِدُهُمْ وَالسَّاعَةُ أَدْهَى وَأَمَرُّ |
| 47 |
አመጸኞች በስህተትና በእሳቶች ውስጥ ናቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/054047.mp3
|
إِنَّ الْمُجْرِمِينَ فِي ضَلَالٍ وَسُعُرٍ |
| 48 |
በእሳት ውስጥ በፊቶቻቸው በሚጎተቱበት ቀን «የሰቀርን መንካት ቅመሱ» (ይባላሉ)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/054048.mp3
|
يَوْمَ يُسْحَبُونَ فِي النَّارِ عَلَى وُجُوهِهِمْ ذُوقُوا مَسَّ سَقَرَ |
| 49 |
እኛ ሁሉን ነገር በልክ ፈጠርነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/054049.mp3
|
إِنَّا كُلَّ شَيْءٍ خَلَقْنَاهُ بِقَدَرٍ |
| 50 |
ትእዛዛችንም እንደ ዓይን ቅጽበት አንዲት (ቃል) እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/054050.mp3
|
وَمَا أَمْرُنَا إِلَّا وَاحِدَةٌ كَلَمْحٍ بِالْبَصَرِ |
| 51 |
ብጤዎቻችሁንም በእርግጥ አጠፋን፡፡ ተገሳጭም አልለን? |
/content/ayah/audio/hudhaify/054051.mp3
|
وَلَقَدْ أَهْلَكْنَا أَشْيَاعَكُمْ فَهَلْ مِن مُّدَّكِرٍ |
| 52 |
የሠሩትም ነገር ሁሉ በመጽሐፎች ውስጥ ነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/054052.mp3
|
وَكُلُّ شَيْءٍ فَعَلُوهُ فِي الزُّبُرِ |
| 53 |
ትንሹም ትልቁም ሁሉ የተጻፈ ነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/054053.mp3
|
وَكُلُّ صَغِيرٍ وَكَبِيرٍ مُسْتَطَرٌ |
| 54 |
አላህን ፈሪዎቹ በአትክልቶችና በወንዞች ውስጥ ናቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/054054.mp3
|
إِنَّ الْمُتَّقِينَ فِي جَنَّاتٍ وَنَهَرٍ |
| 55 |
(እነርሱም ውድቅ ቃልና መውወንጀል በሌለበት) በእውነት መቀመጫ ውስጥ ቻይ የሆነው ንጉሥ ዘንድ ናቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/054055.mp3
|
فِي مَقْعَدِ صِدْقٍ عِندَ مَلِيكٍ مُّقْتَدِرٍ |