1 |
መበተንን በታኞች በኾኑት (ነፋሶች)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051001.mp3
|
وَالذَّارِيَاتِ ذَرْوًا |
2 |
ከባድ (ዝናምን) ተሸካሚዎች በኾኑትም (ደመናዎች)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051002.mp3
|
فَالْحَامِلَاتِ وِقْرًا |
3 |
ገር (መንሻለልን) ተንሻላዮች በኾኑትም (መርከቦች)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051003.mp3
|
فَالْجَارِيَاتِ يُسْرًا |
4 |
ነገርን ሁሉ አከፋፋዮች በኾኑትም (መላእክት) እምላለሁ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051004.mp3
|
فَالْمُقَسِّمَاتِ أَمْرًا |
5 |
የምትቀጠሩት (ትንሣኤ) እውነት ነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051005.mp3
|
إِنَّمَا تُوعَدُونَ لَصَادِقٌ |
6 |
(እንደየሥራው) ዋጋን ማግኘትም፤ ኋኝ ነው፤ (የማይቀር ነው)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051006.mp3
|
وَإِنَّ الدِّينَ لَوَاقِعٌ |
7 |
የ(ከዋክብት) መንገዶች ባለቤት በኾነችው ሰማይ እምላለሁ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051007.mp3
|
وَالسَّمَاء ذَاتِ الْحُبُكِ |
8 |
እናንተ (የመካ ሰዎች) በተለያየ ቃል ውስጥ ናችሁ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051008.mp3
|
إِنَّكُمْ لَفِي قَوْلٍ مُّخْتَلِفٍ |
9 |
ከርሱ የሚዝዞር ሰው ይዝዞራል፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051009.mp3
|
يُؤْفَكُ عَنْهُ مَنْ أُفِكَ |
10 |
በግምት የሚናገሩ ውሸታሞች ተረገሙ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051010.mp3
|
قُتِلَ الْخَرَّاصُونَ |
11 |
እነዚያ እነርሱ በሚሸፍን ስሕተተ ውስጥ ዘንጊዎች የኾኑት፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051011.mp3
|
الَّذِينَ هُمْ فِي غَمْرَةٍ سَاهُونَ |
12 |
የዋጋ መስጫው ቀን መቼ እንደ ኾነ ይጠይቃሉ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051012.mp3
|
يَسْأَلُونَ أَيَّانَ يَوْمُ الدِّينِ |
13 |
(እነርሱ) በእሳት ላይ በሚፈተኑበት ቀን ነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051013.mp3
|
يَوْمَ هُمْ عَلَى النَّارِ يُفْتَنُونَ |
14 |
«መከራችሁን ቅመሱ፤ ይህ ያ በእርሱ ትቻኮሉበት የነበራችሁት ነው» (ይባላሉ)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051014.mp3
|
ذُوقُوا فِتْنَتَكُمْ هَذَا الَّذِي كُنتُم بِهِ تَسْتَعْجِلُونَ |
15 |
አላህን ፈሪዎቹ በአትክልቶችና በምንጮች ውስጥ ናቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051015.mp3
|
إِنَّ الْمُتَّقِينَ فِي جَنَّاتٍ وَعُيُونٍ |
16 |
ያንን ጌታቸው የሰጣቸውን ተቀባዮች ኾነው፤ (በገነት ውስጥ ይኾናሉ)፡፡ እነርሱ ከዚህ በፊት መልካም ሰሪዎች ነበሩና፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051016.mp3
|
آخِذِينَ مَا آتَاهُمْ رَبُّهُمْ إِنَّهُمْ كَانُوا قَبْلَ ذَلِكَ مُحْسِنِينَ |
17 |
ከሌሊቱ ጥቂትን ብቻ ይተኙ ነበሩ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051017.mp3
|
كَانُوا قَلِيلًا مِّنَ اللَّيْلِ مَا يَهْجَعُونَ |
18 |
በሌሊቱ መጨረሻዎችም እነርሱ ምሕረትን ይለምናሉ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051018.mp3
|
وَبِالْأَسْحَارِ هُمْ يَسْتَغْفِرُونَ |
19 |
በገንዘቦቻቸውም ውስጥ ለለማኝና (ከልመና) ለተከለከለም (በችሮታቸው) መብት አልለ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051019.mp3
|
وَفِي أَمْوَالِهِمْ حَقٌّ لِّلسَّائِلِ وَالْمَحْرُومِ |
20 |
በምድርም ውስጥ ለሚያረጋግጡ ሰዎች ምልክቶች አልሉ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051020.mp3
|
وَفِي الْأَرْضِ آيَاتٌ لِّلْمُوقِنِينَ |
21 |
በነፍሶቻችሁም ውስጥ (ምልክቶች አልሉ)፤ ታዲያ አትመለከቱምን?› |
/content/ayah/audio/hudhaify/051021.mp3
|
وَفِي أَنفُسِكُمْ أَفَلَا تُبْصِرُونَ |
22 |
ሲሳያችሁም የምትቀጠሩትም (ፍዳና ምንዳ) በሰማይ ውስጥ ነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051022.mp3
|
وَفِي السَّمَاء رِزْقُكُمْ وَمَا تُوعَدُونَ |
23 |
በሰማይና በምድር ጌታም እምላለሁ፡፡ እርሱ እናንተ እንደምትናገሩት ብጤ እርግጠኛ ነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051023.mp3
|
فَوَرَبِّ السَّمَاء وَالْأَرْضِ إِنَّهُ لَحَقٌّ مِّثْلَ مَا أَنَّكُمْ تَنطِقُونَ |
24 |
የተከበሩት የኢብራሂም እንግዶች ወሬ መጥቶሃልን? |
/content/ayah/audio/hudhaify/051024.mp3
|
هَلْ أَتَاكَ حَدِيثُ ضَيْفِ إِبْرَاهِيمَ الْمُكْرَمِينَ |
25 |
በእርሱ ላይ በገቡና «ሰለም» ባሉ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ «ሰላም ያልታወቃችሁ ሕዝቦች ናችሁ፤» አላቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051025.mp3
|
إِذْ دَخَلُوا عَلَيْهِ فَقَالُوا سَلَامًا قَالَ سَلَامٌ قَوْمٌ مُّنكَرُونَ |
26 |
ወደ ቤተሰቡም ተዘነበለ፤» ወዲያውም የሰባ ወይፈንን አመጣ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051026.mp3
|
فَرَاغَ إِلَى أَهْلِهِ فَجَاء بِعِجْلٍ سَمِينٍ |
27 |
ወደእነርሱም (አርዶና ጠብሶ) አቀረበው፡፡ «አትበሉም ወይ?» አላቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051027.mp3
|
فَقَرَّبَهُ إِلَيْهِمْ قَالَ أَلَا تَأْكُلُونَ |
28 |
ከእነርሱ መፍራትንም በልቡ አሳደረ፡፡ «አትፍራ» አሉት፡፡ በዐዋቂ ወጣት ልጅም አበሰሩት፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051028.mp3
|
فَأَوْجَسَ مِنْهُمْ خِيفَةً قَالُوا لَا تَخَفْ وَبَشَّرُوهُ بِغُلَامٍ عَلِيمٍ |
29 |
ሚስቱም እየጮኸች መጣች፡፡ ፊቷንም መታች፡፡ «መካን አሮጊት ነኝ» አለችም፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051029.mp3
|
فَأَقْبَلَتِ امْرَأَتُهُ فِي صَرَّةٍ فَصَكَّتْ وَجْهَهَا وَقَالَتْ عَجُوزٌ عَقِيمٌ |
30 |
እንደዚህ ጌታሽ ብሏል፡፡ «እነሆ እርሱ ጥበባ ዐዋቂ ነውና» አሏት፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051030.mp3
|
قَالُوا كَذَلِكَ قَالَ رَبُّكِ إِنَّهُ هُوَ الْحَكِيمُ الْعَلِيمُ |
31 |
«እናንተ መልክተኞች ሆይ! ታዲያ ነገራችሁ ምንድን ነው?» አላቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051031.mp3
|
قَالَ فَمَا خَطْبُكُمْ أَيُّهَا الْمُرْسَلُونَ |
32 |
(እነርሱም) አሉ፡- «እኛ ወደ አመጸኞች ሕዝቦች ተልከናል፡፡» |
/content/ayah/audio/hudhaify/051032.mp3
|
قَالُوا إِنَّا أُرْسِلْنَا إِلَى قَوْمٍ مُّجْرِمِينَ |
33 |
በእነርሱ ላይ ከጭቃ የኾኑን ድንጋዮች ልንለቅባቸው (ተላክን)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051033.mp3
|
لِنُرْسِلَ عَلَيْهِمْ حِجَارَةً مِّن طِينٍ |
34 |
በጌታህ ዘንድ ለድንበር አላፊዎቹ (በየስማቸው) ምልክት የተደረገባት ስትኾን፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051034.mp3
|
مُسَوَّمَةً عِندَ رَبِّكَ لِلْمُسْرِفِينَ |
35 |
ከምእምናንም፤ በእርሷ (በከተማቸው) ውስጥ የነበሩትን አወጣን፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051035.mp3
|
فَأَخْرَجْنَا مَن كَانَ فِيهَا مِنَ الْمُؤْمِنِينَ |
36 |
በውስጧም ከሙስሊሞች ከአንድ ቤት (ቤተሰቦች) በስተቀር አላገኘንም፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051036.mp3
|
فَمَا وَجَدْنَا فِيهَا غَيْرَ بَيْتٍ مِّنَ الْمُسْلِمِينَ |
37 |
በውስጧም ለእነዚያ አሳማሚውን ቅጣት ለሚፈሩት ምልክትን አስቀረን፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051037.mp3
|
وَتَرَكْنَا فِيهَا آيَةً لِّلَّذِينَ يَخَافُونَ الْعَذَابَ الْأَلِيمَ |
38 |
በሙሳም (ወሬ) ውስጥ ወደ ፈርዖን በግልጽ ማስረጃ በላክነው ጊዜ (ምልክትን አደረግን)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051038.mp3
|
وَفِي مُوسَى إِذْ أَرْسَلْنَاهُ إِلَى فِرْعَوْنَ بِسُلْطَانٍ مُّبِينٍ |
39 |
ከድጋፉ (ከሰራዊቱ) ጋርም (ከእምነት) ዞረ፡፡ (እርሱ) «ድግምተኛ ወይም ዕብድ ነው» አለም፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051039.mp3
|
فَتَوَلَّى بِرُكْنِهِ وَقَالَ سَاحِرٌ أَوْ مَجْنُونٌ |
40 |
እርሱንም ሰራዊቱንም ያዝናቸው፡፡ እርሱ ተወቃሽ ሲኾን በባሕር ውስጥም ጣልናቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051040.mp3
|
فَأَخَذْنَاهُ وَجُنُودَهُ فَنَبَذْنَاهُمْ فِي الْيَمِّ وَهُوَ مُلِيمٌ |
41 |
በዓድም በእነርሱ ላይ መካንን ነፋስ በላክን ጊዜ (ምልክት አልለ)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051041.mp3
|
وَفِي عَادٍ إِذْ أَرْسَلْنَا عَلَيْهِمُ الرِّيحَ الْعَقِيمَ |
42 |
በላዩ ላይ የመጣችበትን ማንኛውንም ነገር እንደ በሰበሰ አጥንት ያደረገችው ብትኾን እንጂ አትተወውም፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051042.mp3
|
مَا تَذَرُ مِن شَيْءٍ أَتَتْ عَلَيْهِ إِلَّا جَعَلَتْهُ كَالرَّمِيمِ |
43 |
በሰሙድም ለእነርሱ «እስከ ጊዜ (ሞታችሁ) ድረስ ተጣቀሙ» በተባሉ ጊዜ (ምልክት አልለ)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051043.mp3
|
وَفِي ثَمُودَ إِذْ قِيلَ لَهُمْ تَمَتَّعُوا حَتَّى حِينٍ |
44 |
ከጌታቸው ትዕዛዝም ኮሩ፡፡ እነርሱም እያዩ ጩኸት ያዘቻቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051044.mp3
|
فَعَتَوْا عَنْ أَمْرِ رَبِّهِمْ فَأَخَذَتْهُمُ الصَّاعِقَةُ وَهُمْ يَنظُرُونَ |
45 |
መቆምንም ምንም አልቻሉም፡፡ የሚርረዱም አልነበሩም፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051045.mp3
|
فَمَا اسْتَطَاعُوا مِن قِيَامٍ وَمَا كَانُوا مُنتَصِرِينَ |
46 |
የኑሕንም ሕዝቦች ከዚህ በፊት (አጠፋን)፡፡ እነርሱ አመጸኞች ሕዝቦች ነበሩና፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051046.mp3
|
وَقَوْمَ نُوحٍ مِّن قَبْلُ إِنَّهُمْ كَانُوا قَوْمًا فَاسِقِينَ |
47 |
ሰማይንም በኀይል ገነባናት፡፡ እኛም በእርግጥ ቻዮች ነን፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051047.mp3
|
وَالسَّمَاء بَنَيْنَاهَا بِأَيْدٍ وَإِنَّا لَمُوسِعُونَ |
48 |
ምድርንም ዘረጋናት፡፡ ምን ያማርንም ዘርጊዎች (ነን!) |
/content/ayah/audio/hudhaify/051048.mp3
|
وَالْأَرْضَ فَرَشْنَاهَا فَنِعْمَ الْمَاهِدُونَ |
49 |
ትገነዘቡም ዘንድ ከነገሩ ሁሉ ሁለት (ተቃራኒ) ዓይነትን ፈጠርን፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051049.mp3
|
وَمِن كُلِّ شَيْءٍ خَلَقْنَا زَوْجَيْنِ لَعَلَّكُمْ تَذَكَّرُونَ |
50 |
«ወደ አላህም ሽሹ፤ እኔ ለእናንተ ከርሱ ግልጽ አስጠንቃቂ ነኝና» (በላቸው)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051050.mp3
|
فَفِرُّوا إِلَى اللَّهِ إِنِّي لَكُم مِّنْهُ نَذِيرٌ مُّبِينٌ |
51 |
ከአላህም ጋር ሌላን አምላክ አታድርጉ፡፡ እኔ ለእናንተ ከእርሱ (የተላክሁ) ግልጽ አስፈራሪ ነኝና፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051051.mp3
|
وَلَا تَجْعَلُوا مَعَ اللَّهِ إِلَهًا آخَرَ إِنِّي لَكُم مِّنْهُ نَذِيرٌ مُّبِينٌ |
52 |
(ነገሩ) እንደዚሁ ነው፡፡ እነዚያን ከእነርሱ በፊት የነበሩትን ከመልክተኛ ማንም አልመጣቸውም፡፡ (እርሱ) «ድግምተኛ ወይም ዕብድ ነው» ያሉ ቢኾኑ እንጂ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051052.mp3
|
كَذَلِكَ مَا أَتَى الَّذِينَ مِن قَبْلِهِم مِّن رَّسُولٍ إِلَّا قَالُوا سَاحِرٌ أَوْ مَجْنُونٌ |
53 |
በእርሱ (በዚህ ቃል) አደራ ተባብለዋልን? አይደለም፤ እነርሱ ጥጋበኞች ሕዝቦች ናቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051053.mp3
|
أَتَوَاصَوْا بِهِ بَلْ هُمْ قَوْمٌ طَاغُونَ |
54 |
ከእነርሱም (ክርክር) ዘወር በል፤ (ተዋቸው)፡፡ አንተ ምንም ተወቃሽ አይደለህምና፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051054.mp3
|
فَتَوَلَّ عَنْهُمْ فَمَا أَنتَ بِمَلُومٍ |
55 |
ገሥጽም፤ ግሣጼ ምእመናንን ትጠቅማለችና፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051055.mp3
|
وَذَكِّرْ فَإِنَّ الذِّكْرَى تَنفَعُ الْمُؤْمِنِينَ |
56 |
ጋኔንንና ሰውንም ሊግገዙኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051056.mp3
|
وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ |
57 |
ከነርሱም ምንም ሲሳይ አልፈልግም፡፡ ሊመግቡኝም አልሻም፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051057.mp3
|
مَا أُرِيدُ مِنْهُم مِّن رِّزْقٍ وَمَا أُرِيدُ أَن يُطْعِمُونِ |
58 |
አላህ እርሱ ሲሳይን ሰጪ የብርቱ ኀይል ባለቤት ነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051058.mp3
|
إِنَّ اللَّهَ هُوَ الرَّزَّاقُ ذُو الْقُوَّةِ الْمَتِينُ |
59 |
ለእነዚያም ለበደሉት እንደ ጓደኞቻቸው ፋንታ ብጤ (የቅጣት) ፋንታ አልላቸው፡፡ ስለዚህ አያስቸኩሉኝ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051059.mp3
|
فَإِنَّ لِلَّذِينَ ظَلَمُوا ذَنُوبًا مِّثْلَ ذَنُوبِ أَصْحَابِهِمْ فَلَا يَسْتَعْجِلُونِ |
60 |
ለነዚያም ለካዱት ከዚያ ከሚቀጠሩት ቀናቸው ወዮላቸው፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/051060.mp3
|
فَوَيْلٌ لِّلَّذِينَ كَفَرُوا مِن يَوْمِهِمُ الَّذِي يُوعَدُونَ |