At-Tur

Change Language
Change Surah
Change Recitation

Amharic: Muhammed Sadiq and Muhammed Sani Habib

Play All
# Translation Ayah
1 በጡር (ጋራ) እምላለሁ፡፡ وَالطُّورِ
2 በተጻፈው መጽሐፍም፡፡ وَكِتَابٍ مَّسْطُورٍ
3 በተዘረጋ ብራና ላይ፤ (በተጻፈው)፡፡ فِي رَقٍّ مَّنشُورٍ
4 በደመቀው ቤትም፡፡ وَالْبَيْتِ الْمَعْمُورِ
5 ከፍ በተደረገው ጣራም፡፡ وَالسَّقْفِ الْمَرْفُوعِ
6 በተመላው ባሕርም እምላለሁ፡፡ وَالْبَحْرِ الْمَسْجُورِ
7 የጌታህ ቅጣት በእርግጥ ወዳቂ ነው፤ (የማይቀር ነው)፡፡ إِنَّ عَذَابَ رَبِّكَ لَوَاقِعٌ
8 ለእርሱ ምንም ገፍታሪ የለውም፡፡ مَا لَهُ مِن دَافِعٍ
9 ሰማይ ብርቱ መዞርን በምትዞርበት ቀን (ይኾናል)፡፡ يَوْمَ تَمُورُ السَّمَاء مَوْرًا
10 ተራራዎችም መኼድን በሚኼዱበት (ቀን)፡፡ وَتَسِيرُ الْجِبَالُ سَيْرًا
11 ለአስተባባዮችም ያን ጊዜ ወዮላቸው፡፡ فَوَيْلٌ يَوْمَئِذٍ لِلْمُكَذِّبِينَ
12 ለእነዚያ እነርሱ በውሸት ውስጥ የሚጫወቱ ለኾኑት፡፡ الَّذِينَ هُمْ فِي خَوْضٍ يَلْعَبُونَ
13 ወደ ገሀነም እሳት በኀይል መግገፍተርን በሚግገፈተሩበት ቀን፡፡ يَوْمَ يُدَعُّونَ إِلَى نَارِ جَهَنَّمَ دَعًّا
14 ይህቺ ያቺ በእርሷ ታስተባብሉባት የነበራችሁት እሳት ናት፡፡ هَذِهِ النَّارُ الَّتِي كُنتُم بِهَا تُكَذِّبُونَ
15 ይህ (ፊት ትሉ እንደነበራችሁት) ድግምት ነውን? ወይስ እናንተ አታዩምን? أَفَسِحْرٌ هَذَا أَمْ أَنتُمْ لَا تُبْصِرُونَ
16 ግቧት ታገሱም ወይም አትታገሡ በእናንተ ላይ እኩል ነው፡፡ የምትምመነዱት ትሠሩት የነበራችሁትን (ፍዳ) ብቻ ነው (ይባላሉ)፡፡ اصْلَوْهَا فَاصْبِرُوا أَوْ لَا تَصْبِرُوا سَوَاء عَلَيْكُمْ إِنَّمَا تُجْزَوْنَ مَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ
17 አላህን ፈሪዎቹ በእርግጥ በገነቶችና በጸጋ ውስጥ ናቸው፡፡ إِنَّ الْمُتَّقِينَ فِي جَنَّاتٍ وَنَعِيمٍ
18 ጌታቸው በሰጣቸው ጸጋ ተደሳቾች ኾነው (በገነት ውስጥ ናቸው)፡፡ የገሀነምንም ስቃይ ጌታቸው ጠበቃቸው፡፡ فَاكِهِينَ بِمَا آتَاهُمْ رَبُّهُمْ وَوَقَاهُمْ رَبُّهُمْ عَذَابَ الْجَحِيمِ
19 «ትሠሩት በነበራችሁት ምክንያት ተደሳቾች ኾናችሁ ብሉ፤ ጠጡም፤» (ይባላሉ)፡፡ كُلُوا وَاشْرَبُوا هَنِيئًا بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ
20 በተደረደሩ አልጋዎች ላይ ተደጋፊዎች ኾነው (በገነት ይኖራሉ)፡፡ ዓይናማዎች በኾኑ ነጫጭ ሴቶችም እናጠናዳቸዋለን፡፡ مُتَّكِئِينَ عَلَى سُرُرٍ مَّصْفُوفَةٍ وَزَوَّجْنَاهُم بِحُورٍ عِينٍ
21 እነዚያም ያመኑትና ዝርያቸውም በእምነት የተከተለቻቸው ዝርያቸውን በእነርሱ እናስጠጋለን፡፡ ከሥራቸውም ምንም አናጎድልባቸውም፡፡ ሰው ሁሉ በሠራው ሥራ ተያዢ ነው፡፡ وَالَّذِينَ آمَنُوا وَاتَّبَعَتْهُمْ ذُرِّيَّتُهُم بِإِيمَانٍ أَلْحَقْنَا بِهِمْ ذُرِّيَّتَهُمْ وَمَا أَلَتْنَاهُم مِّنْ عَمَلِهِم مِّن شَيْءٍ كُلُّ امْرِئٍ بِمَا كَسَبَ رَهِينٌ
22 ከሚሹትም ሁሉ እሸትንና ስጋን እንጨምርላቸዋለን፡፡ وَأَمْدَدْنَاهُم بِفَاكِهَةٍ وَلَحْمٍ مِّمَّا يَشْتَهُونَ
23 በውስጧ መጠጥን ይሰጣጣሉ፡፡ በውስጧ ውድቅ ንግግርና መውወንጀልም የለም፡፡ يَتَنَازَعُونَ فِيهَا كَأْسًا لَّا لَغْوٌ فِيهَا وَلَا تَأْثِيمٌ
24 ለነርሱም የኾኑ ወጣቶች ልክ የተሸፈነ ሉል መስለው በእነርሱ ላይ (ለማሳለፍ) ይዘዋወራሉ፡፡ وَيَطُوفُ عَلَيْهِمْ غِلْمَانٌ لَّهُمْ كَأَنَّهُمْ لُؤْلُؤٌ مَّكْنُونٌ
25 የሚጠያየቁ ኾነውም ከፊላቸው በከፊሉ ላይ ይዞራል፡፡ وَأَقْبَلَ بَعْضُهُمْ عَلَى بَعْضٍ يَتَسَاءلُونَ
26 «እኛ ፊት በቤተሰቦቻችን ውስጥ (ከቅጣት) ፈሪዎች ነበርን» ይላሉ፡፡ قَالُوا إِنَّا كُنَّا قَبْلُ فِي أَهْلِنَا مُشْفِقِينَ
27 «አላህም በእኛ ላይ ለገሰ፡፡ የመርዛም እሳት ቅጣትንም ጠበቀን፡፡ فَمَنَّ اللَّهُ عَلَيْنَا وَوَقَانَا عَذَابَ السَّمُومِ
28 «እኛ ከዚህ በፊት እንለምነው ነበርን፡፡ እነሆ እርሱ በጎ ዋይ አዛኝ ነውና» (ይላሉ)፡፡ إِنَّا كُنَّا مِن قَبْلُ نَدْعُوهُ إِنَّهُ هُوَ الْبَرُّ الرَّحِيمُ
29 (ሰዎችን) አስታውስም፡፡ አንተም በጌታህ ጸጋ ምክንያት ጠንቋይም ዕብድም አይደለህም፡፡ فَذَكِّرْ فَمَا أَنتَ بِنِعْمَتِ رَبِّكَ بِكَاهِنٍ وَلَا مَجْنُونٍ
30 ይልቁንም የሞትን አደጋ በእርሱ የምንጠባበቅበት የኾነ ባለ ቅኔ ነው ይላሉን? أَمْ يَقُولُونَ شَاعِرٌ نَّتَرَبَّصُ بِهِ رَيْبَ الْمَنُونِ
31 «ተጠባበቁ፤ እኔም ከእናንተ ጋር ከሚጠባበቁት ነኝ» በላቸው፡፡ قُلْ تَرَبَّصُوا فَإِنِّي مَعَكُم مِّنَ الْمُتَرَبِّصِينَ
32 አእምሮዎቻቸው በዚህ ያዟቸዋልን? አይደለም በእውነቱ እነርሱ ወሰን አላፊዎች ሕዝቦች ናቸው፡፡ أَمْ تَأْمُرُهُمْ أَحْلَامُهُم بِهَذَا أَمْ هُمْ قَوْمٌ طَاغُونَ
33 ወይም «ቀጠፈው ይላሉን?» አይደለም፤ በእውነቱ አያምኑም፡፡ أَمْ يَقُولُونَ تَقَوَّلَهُ بَل لَّا يُؤْمِنُونَ
34 እውነተኞችም ቢኾኑ መሰሉ የኾነን ንግግር ያምጡ፡፡ فَلْيَأْتُوا بِحَدِيثٍ مِّثْلِهِ إِن كَانُوا صَادِقِينَ
35 ወይስ ያለ አንዳች (ፈጣሪ) ተፈጠሩን? ወይስ እነርሱ ፈጣሪዎች ናቸውን? أَمْ خُلِقُوا مِنْ غَيْرِ شَيْءٍ أَمْ هُمُ الْخَالِقُونَ
36 ወይስ ሰማያትንና ምድርን ፈጠሩን? አይደለም አያረጋግጡም፡፡ أَمْ خَلَقُوا السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ بَل لَّا يُوقِنُونَ
37 ወይስ የጌታህ ግምጃ ቤቶች እነርሱ ዘንድ ናቸውን? ወይስ እነርሱ አሸናፊዎች ናቸውን? أَمْ عِندَهُمْ خَزَائِنُ رَبِّكَ أَمْ هُمُ الْمُصَيْطِرُونَ
38 ወይስ ለእነርሱ በእርሱ ላይ (ከሰማይ) የሚያዳምጡበት መሰላል አላቸውን? አድማጫቸውም (ሰማሁ ቢል) ግልጽን አስረጅ ያምጣ፡፡ أَمْ لَهُمْ سُلَّمٌ يَسْتَمِعُونَ فِيهِ فَلْيَأْتِ مُسْتَمِعُهُم بِسُلْطَانٍ مُّبِينٍ
39 ወይስ ለእርሱ ሴቶች ልጆች አሉትን? ለእናንተም ወንዶች ልጆች አሏችሁን? أَمْ لَهُ الْبَنَاتُ وَلَكُمُ الْبَنُونَ
40 ወይስ ዋጋን ትጠይቃቸዋለህን? ስለዚህ እነርሱ ከዕዳው የተከበዱ ናቸውን? أَمْ تَسْأَلُهُمْ أَجْرًا فَهُم مِّن مَّغْرَمٍ مُّثْقَلُونَ
41 ወይስ ሩቁ ምስጢር እነርሱ ዘንድ ነውን? ስለዚህ እነርሱ ይጽፋሉን? أَمْ عِندَهُمُ الْغَيْبُ فَهُمْ يَكْتُبُونَ
42 ወይስ ተንኮልን (ባንተ) ይሻሉን? እነዚያም የካዱት እነርሱ በተንኮል ተሸናፊዎች ናቸው፡፡ أَمْ يُرِيدُونَ كَيْدًا فَالَّذِينَ كَفَرُوا هُمُ الْمَكِيدُونَ
43 ወይስ ለእነርሱ ከአላህ ሌላ አምላክ አላቸውን? አላህ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ፡፡ أَمْ لَهُمْ إِلَهٌ غَيْرُ اللَّهِ سُبْحَانَ اللَّهِ عَمَّا يُشْرِكُونَ
44 ከሰማይም ቁራጭን (በእነርሱ ላይ) ወዳቂ ኾኖ ቢያዩ ኖሮ «ይህ የተደራረበ ደመና ነው» ይሉ ነበር፡፡ وَإِن يَرَوْا كِسْفًا مِّنَ السَّمَاء سَاقِطًا يَقُولُوا سَحَابٌ مَّرْكُومٌ
45 ያንንም በእርሱ የሚግገደሉበትን ቀናቸውን እስከሚገናኙ ድረስ ተዋቸው፡፡ فَذَرْهُمْ حَتَّى يُلَاقُوا يَوْمَهُمُ الَّذِي فِيهِ يُصْعَقُونَ
46 ተንኮላቸው ከእነርሱ ምንንም የማይጠቅማቸውንና እነርሱም የማይርረዱበትን ቀን (እስከ ሚገናኙ ተዋቸው)፡፡ يَوْمَ لَا يُغْنِي عَنْهُمْ كَيْدُهُمْ شَيْئًا وَلَا هُمْ يُنصَرُونَ
47 ለእነዚያ ለበደሉትም ከዚህ ሌላ ቅርብ ቅጣት አልላቸው፡፡ ግን አብዛኛዎቻቸው አያውቁም፡፡ وَإِنَّ لِلَّذِينَ ظَلَمُوا عَذَابًا دُونَ ذَلِكَ وَلَكِنَّ أَكْثَرَهُمْ لَا يَعْلَمُونَ
48 ለጌታህ ፍርድም ታገሥ፡፡ አንተ በጥበቃችን ውስጥ ነህና፡፡ ጌታህንም በምትነሳ ጊዜ ከማመስገን ጋር አወድሰው፡፡ وَاصْبِرْ لِحُكْمِ رَبِّكَ فَإِنَّكَ بِأَعْيُنِنَا وَسَبِّحْ بِحَمْدِ رَبِّكَ حِينَ تَقُومُ
49 ከሌሊቱም አወድሰው፡፡ በከዋክብት መዳበቂያ ጊዜም (ንጋት ላይ አወድሰው)፡፡ وَمِنَ اللَّيْلِ فَسَبِّحْهُ وَإِدْبَارَ النُّجُومِ
;