1 |
ሐ.መ (ሓ ሚም)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044001.mp3
|
حم |
2 |
አብራሪ በኾነው መጽሐፍ እንምላለን፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044002.mp3
|
وَالْكِتَابِ الْمُبِينِ |
3 |
እኛ (ቁርኣኑን) በተባረከች ሌሊት ውስጥ አወረድነው፡፡ እኛ አስፈራሪዎች ነበርንና፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044003.mp3
|
إِنَّا أَنزَلْنَاهُ فِي لَيْلَةٍ مُّبَارَكَةٍ إِنَّا كُنَّا مُنذِرِينَ |
4 |
በውስጧ የተወሰነው ነገር ሁሉ ይልለያል፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044004.mp3
|
فِيهَا يُفْرَقُ كُلُّ أَمْرٍ حَكِيمٍ |
5 |
ከእኛ ዘንድ የኾነ ትእዛዝ ሲኾን (አወረድነው)፡፡ እኛ (መልክተኞችን) ላኪዎች ነበርን፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044005.mp3
|
أَمْرًا مِّنْ عِندِنَا إِنَّا كُنَّا مُرْسِلِينَ |
6 |
ከጌታህ በኾነው ችሮታ (ተላኩ)፡፡ እነሆ እርሱ ሰሚው ዐዋቂው ነውና፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044006.mp3
|
رَحْمَةً مِّن رَّبِّكَ إِنَّهُ هُوَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ |
7 |
የሰማያትና የምድር በመካከላቸውም ያለው ነገር ሁሉ ጌታ ከኾነው (ተላኩ)፡፡ የምታረጋግጡ እንደኾናችሁ (ነገሩ እንዳልነው መኾኑን እወቁ)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044007.mp3
|
رَبِّ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَمَا بَيْنَهُمَا إِن كُنتُم مُّوقِنِينَ |
8 |
ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ ሕያው ያደርጋል፡፡ ይገድላልም፡፡ ጌታችሁ የመጀመሪያዎቹ አባቶቻችሁም ጌታ ነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044008.mp3
|
لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ يُحْيِي وَيُمِيتُ رَبُّكُمْ وَرَبُّ آبَائِكُمُ الْأَوَّلِينَ |
9 |
በእውነቱ እነርሱ የሚጫወቱ ሲኾኑ በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044009.mp3
|
بَلْ هُمْ فِي شَكٍّ يَلْعَبُونَ |
10 |
ሰማይም በግልጽ ጭስ የምትመጣበትን ቀን ተጠባበቅ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044010.mp3
|
فَارْتَقِبْ يَوْمَ تَأْتِي السَّمَاء بِدُخَانٍ مُّبِينٍ |
11 |
ሰዎችን የሚሸፍን (በኾነ ጭስ) ይህ አሳማሚ ቅጣት ነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044011.mp3
|
يَغْشَى النَّاسَ هَذَا عَذَابٌ أَلِيمٌ |
12 |
«ጌታችን ሆይ! ከእኛ ላይ ቅጣቱን ግለጥልን፡፡ እኛ አማኞች እንኾናለንና» (ይላሉም)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044012.mp3
|
رَبَّنَا اكْشِفْ عَنَّا الْعَذَابَ إِنَّا مُؤْمِنُونَ |
13 |
(ቅጣቱ በወረደ ጊዜ) ለእነርሱ መግገሰጽ እንዴት ይኖራቸዋል? አስረጅ መልክተኛ የመጣቸው ሲኾን (የካዱም ሲኾኑ)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044013.mp3
|
أَنَّى لَهُمُ الذِّكْرَى وَقَدْ جَاءهُمْ رَسُولٌ مُّبِينٌ |
14 |
ከዚያም ከእርሱ የዞሩ፤ (ከሰው) «የተሰተማረ ዕብድ ነው» ያሉም ሲኾኑ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044014.mp3
|
ثُمَّ تَوَلَّوْا عَنْهُ وَقَالُوا مُعَلَّمٌ مَّجْنُونٌ |
15 |
እኛ ቅጣቱን ለጥቂት ጊዜ ገላጮች ነን፡፡ እናንተ (ወደ ክህደታችሁ) በእርግጥ ተመላሾች ናችሁ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044015.mp3
|
إِنَّا كَاشِفُو الْعَذَابِ قَلِيلًا إِنَّكُمْ عَائِدُونَ |
16 |
ታላቂቱን ብርቱ አያያዝ በምንይዝበት ቀን፤ እኛ ተበቃዮች ነን፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044016.mp3
|
يَوْمَ نَبْطِشُ الْبَطْشَةَ الْكُبْرَى إِنَّا مُنتَقِمُونَ |
17 |
ከእነርሱም በፊት የፈርዖንን ሕዝቦች በእርግጥ ሞከርን፡፡ ክቡር መልእክተኛም መጣላቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044017.mp3
|
وَلَقَدْ فَتَنَّا قَبْلَهُمْ قَوْمَ فِرْعَوْنَ وَجَاءهُمْ رَسُولٌ كَرِيمٌ |
18 |
«የአላህን ባሮች ወደኔ አድርሱ፡፡ እኔ ለእናንተ ታማኝ መልክተኛ ነኝና፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044018.mp3
|
أَنْ أَدُّوا إِلَيَّ عِبَادَ اللَّهِ إِنِّي لَكُمْ رَسُولٌ أَمِينٌ |
19 |
«በአላህም ላይ አትኩሩ፡፡ እኔ ግልጽ የኾነን አስረጅ ያመጣሁላችሁ ነኝና (በማለት መጣላቸው)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044019.mp3
|
وَأَنْ لَّا تَعْلُوا عَلَى اللَّهِ إِنِّي آتِيكُم بِسُلْطَانٍ مُّبِينٍ |
20 |
«እኔም እንዳትወግሩኝ በጌታየና በጌታችሁ ተጠብቂያለሁ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044020.mp3
|
وَإِنِّي عُذْتُ بِرَبِّي وَرَبِّكُمْ أَن تَرْجُمُونِ |
21 |
«በእኔም ባታምኑ ራቁኝ» (ተዉኝ አለ)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044021.mp3
|
وَإِنْ لَّمْ تُؤْمِنُوا لِي فَاعْتَزِلُونِ |
22 |
ቀጥሎም (ስለ ዛቱበት) «እነዚህ አመጸኞች ሕዝቦች ናቸው» (አጥፋቸው) ሲል ጌታውን ለመነ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044022.mp3
|
فَدَعَا رَبَّهُ أَنَّ هَؤُلَاء قَوْمٌ مُّجْرِمُونَ |
23 |
(ጌታው) «ባሮቼንም ይዘህ በሌሊት ኺድ፡፡ እናንተ የሚከተሉዋችሁ ናችሁና፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044023.mp3
|
فَأَسْرِ بِعِبَادِي لَيْلًا إِنَّكُم مُّتَّبَعُونَ |
24 |
«ባሕሩንም የተከፈተ ኾኖ ተወው፡፡ እነርሱ የሚሰጥጠሙ ሰራዊት ናቸውና» (አለው)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044024.mp3
|
وَاتْرُكْ الْبَحْرَ رَهْوًا إِنَّهُمْ جُندٌ مُّغْرَقُونَ |
25 |
ከአትክልቶችና ከምንጮችም ብዙ ነገሮችን ተዉ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044025.mp3
|
كَمْ تَرَكُوا مِن جَنَّاتٍ وَعُيُونٍ |
26 |
ከአዝመራዎችም ከመልካም መቀመጫም፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044026.mp3
|
وَزُرُوعٍ وَمَقَامٍ كَرِيمٍ |
27 |
በእርሷ ተደሳቾች ከነበሩባትም ድሎት (ብዙን ነገር ተዉ)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044027.mp3
|
وَنَعْمَةٍ كَانُوا فِيهَا فَاكِهِينَ |
28 |
(ነገሩ) እንደዚሁ ኾነ፡፡ ሌሎችንም ሕዝቦች አወረስናት፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044028.mp3
|
كَذَلِكَ وَأَوْرَثْنَاهَا قَوْمًا آخَرِينَ |
29 |
ሰማይና ምድርም በእነርሱ ላይ አላለቀሱም፡፡ የሚቆዩም አልነበሩም፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044029.mp3
|
فَمَا بَكَتْ عَلَيْهِمُ السَّمَاء وَالْأَرْضُ وَمَا كَانُوا مُنظَرِينَ |
30 |
የእስራኤልንም ልጆች አዋራጅ ከኾነ ስቃይ በእርግጥ አዳንናቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044030.mp3
|
وَلَقَدْ نَجَّيْنَا بَنِي إِسْرَائِيلَ مِنَ الْعَذَابِ الْمُهِينِ |
31 |
ከፈርዖን፤ እርሱ የኮራ ከወሰን አላፊዎቹ ነበርና፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044031.mp3
|
مِن فِرْعَوْنَ إِنَّهُ كَانَ عَالِيًا مِّنَ الْمُسْرِفِينَ |
32 |
ከማወቅም ጋር በዓለማት ላይ በእርግጥ መረጥናቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044032.mp3
|
وَلَقَدِ اخْتَرْنَاهُمْ عَلَى عِلْمٍ عَلَى الْعَالَمِينَ |
33 |
ከታምራቶችም በውስጡ ግልጽ የኾነ ፈተና ያለበትን ሰጠናቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044033.mp3
|
وَآتَيْنَاهُم مِّنَ الْآيَاتِ مَا فِيهِ بَلَاء مُّبِينٌ |
34 |
እነዚህ (የመካ ከሓዲዎች) በእርግጥ ይላሉ፡- |
/content/ayah/audio/hudhaify/044034.mp3
|
إِنَّ هَؤُلَاء لَيَقُولُونَ |
35 |
እርሷ የፊተኛይቱ ሞታችን እንጅ አይደለችም፡፡ እኛም የምንቀሰቀስ አይደለንም፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044035.mp3
|
إِنْ هِيَ إِلَّا مَوْتَتُنَا الْأُولَى وَمَا نَحْنُ بِمُنشَرِينَ |
36 |
እውነተኞችም እንደ ኾናችሁ አባቶቻችንን አምጡልን፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044036.mp3
|
فَأْتُوا بِآبَائِنَا إِن كُنتُمْ صَادِقِينَ |
37 |
እነርሱ በላጮች ናቸውን ወይስ የቱብበዕ ሕዝቦችና እነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩት? አጠፋናቸው፡፡ እነርሱ አመጸኞች ነበሩና፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044037.mp3
|
أَهُمْ خَيْرٌ أَمْ قَوْمُ تُبَّعٍ وَالَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ أَهْلَكْنَاهُمْ إِنَّهُمْ كَانُوا مُجْرِمِينَ |
38 |
ሰማያትንና ምድርንም በሁለቱ መካከል ያለውንም ሁሉ ቀላጆች ኾነን አልፈጠርንም፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044038.mp3
|
وَمَا خَلَقْنَا السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ وَمَا بَيْنَهُمَا لَاعِبِينَ |
39 |
ሁለቱንም በምር እንጅ አልፈጠርናቸውም፡፡ ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044039.mp3
|
مَا خَلَقْنَاهُمَا إِلَّا بِالْحَقِّ وَلَكِنَّ أَكْثَرَهُمْ لَا يَعْلَمُونَ |
40 |
የመለያው ቀን ለሁሉም ቀጠሯቸው ነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044040.mp3
|
إِنَّ يَوْمَ الْفَصْلِ مِيقَاتُهُمْ أَجْمَعِينَ |
41 |
ዘመድ ከዘመዱ ምንንም የማይጠቅምበት እነርሱም የማይርረዱበት ቀን ነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044041.mp3
|
يَوْمَ لَا يُغْنِي مَوْلًى عَن مَّوْلًى شَيْئًا وَلَا هُمْ يُنصَرُونَ |
42 |
አላህ ያዘነለት ሰውና ያመነ ብቻ ሲቀር፡፡ (እርሱስ ይርረዳል)፡፡ እርሱ አሸናፊው አዛኙ ነውና፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044042.mp3
|
إِلَّا مَن رَّحِمَ اللَّهُ إِنَّهُ هُوَ الْعَزِيزُ الرَّحِيمُ |
43 |
የዘቁመ ዛፍ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044043.mp3
|
إِنَّ شَجَرَةَ الزَّقُّومِ |
44 |
የኀጢኣተኛው ምግብ ነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044044.mp3
|
طَعَامُ الْأَثِيمِ |
45 |
እንደ ዘይት አተላ ነው፡፡ በሆዶች ውስጥ የሚፈላ ሲኾን፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044045.mp3
|
كَالْمُهْلِ يَغْلِي فِي الْبُطُونِ |
46 |
እንደ ገነፈለ ውሃ አፈላል (የሚፈላ ሲኾን)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044046.mp3
|
كَغَلْيِ الْحَمِيمِ |
47 |
ያዙት፤ ወደ ገሀነም መካከልም በኀይል ጎትቱት፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044047.mp3
|
خُذُوهُ فَاعْتِلُوهُ إِلَى سَوَاء الْجَحِيمِ |
48 |
ከዚያም «ከራሱ በላይ ከፈላ ውሃ ስቃይ አንቧቡበት፡፡» |
/content/ayah/audio/hudhaify/044048.mp3
|
ثُمَّ صُبُّوا فَوْقَ رَأْسِهِ مِنْ عَذَابِ الْحَمِيمِ |
49 |
«ቅመስ፤ አንተ አሸናፊው ክብሩ ነህና» (ይባላል)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044049.mp3
|
ذُقْ إِنَّكَ أَنتَ الْعَزِيزُ الْكَرِيمُ |
50 |
«ይህ ያ በእርሱ ትጠራጠሩበት የነበራችሁት ነው» (ይባላሉ)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044050.mp3
|
إِنَّ هَذَا مَا كُنتُم بِهِ تَمْتَرُونَ |
51 |
ጥንቁቆቹ በእርግጥ በጸጥተኛ መኖሪያ ውስጥ ናቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044051.mp3
|
إِنَّ الْمُتَّقِينَ فِي مَقَامٍ أَمِينٍ |
52 |
በአትክልቶችና በምንጮች ውስጥ ናቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044052.mp3
|
فِي جَنَّاتٍ وَعُيُونٍ |
53 |
ፊት ለፊት የተቅጣጩ ኾነው ከስስ ሐርና ከወፍራም ሐር ይለብሳሉ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044053.mp3
|
يَلْبَسُونَ مِن سُندُسٍ وَإِسْتَبْرَقٍ مُّتَقَابِلِينَ |
54 |
(ነገሩ) እንደዚሁ ነው፤ ዓይናማዎች የኾኑን ነጫጭ ሴቶችም እናጠናዳቸዋለን፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044054.mp3
|
كَذَلِكَ وَزَوَّجْنَاهُم بِحُورٍ عِينٍ |
55 |
በእርሷም ውስጥ የተማመኑ ኾነው፤ ከፍራፍሬ ሁሉ ያዝዛሉ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044055.mp3
|
يَدْعُونَ فِيهَا بِكُلِّ فَاكِهَةٍ آمِنِينَ |
56 |
የፊተኛይቱን ሞት እንጅ (ዳግመኛ) በእርሷ ውስጥ ሞትን አይቀምሱም፡፡ የገሀነምንም ቅጣት (አላህ) ጠበቃቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044056.mp3
|
لَا يَذُوقُونَ فِيهَا الْمَوْتَ إِلَّا الْمَوْتَةَ الْأُولَى وَوَقَاهُمْ عَذَابَ الْجَحِيمِ |
57 |
ከጌታህ በኾነ ችሮታ (ጠበቃቸው)፡፡ ይህ እርሱ ታላቅ ዕድል ነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044057.mp3
|
فَضْلًا مِّن رَّبِّكَ ذَلِكَ هُوَ الْفَوْزُ الْعَظِيمُ |
58 |
(ቁርኣኑን) በቋንቋህም ያገራነው (ሕዝቦችህ) ይገነዘቡ ዘንድ ብቻ ነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044058.mp3
|
فَإِنَّمَا يَسَّرْنَاهُ بِلِسَانِكَ لَعَلَّهُمْ يَتَذَكَّرُونَ |
59 |
ተጠባበቅም እነርሱ ተጠባባቂዎች ናቸውና፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/044059.mp3
|
فَارْتَقِبْ إِنَّهُم مُّرْتَقِبُونَ |