1 |
ሐ.መ (ሓ ሚም)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/045001.mp3
|
حم |
2 |
የመጽሐፉ መወረድ አሸናፊ ጥበበኛ ከኾነው አላህ ነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/045002.mp3
|
تَنزِيلُ الْكِتَابِ مِنَ اللَّهِ الْعَزِيزِ الْحَكِيمِ |
3 |
በሰማያትና በምድር ውስጥ ለምእምናን ሁሉ (ለችሎታው) እርገጠኛ ምልክቶች አልሉ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/045003.mp3
|
إِنَّ فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ لَآيَاتٍ لِّلْمُؤْمِنِينَ |
4 |
እናንተንም በመፍጠር ከተንቀሳቃሽም (በምድር ላይ) የሚበትነውን ሁሉ (በመፍጠሩ) ለሚያረጋግጡ ሕዝቦች ተዓምራቶች አልሉ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/045004.mp3
|
وَفِي خَلْقِكُمْ وَمَا يَبُثُّ مِن دَابَّةٍ آيَاتٌ لِّقَوْمٍ يُوقِنُونَ |
5 |
በሌሊትና መዓልት መተካካትም፣ ከሲሳይም (ከዝናም) አላህ ከሰማይ ባወረደው በርሱም ምድርን ከሞተች በኋላ ሕያው በማድረጉ፣ ነፋሶችንም (በያቅጣጫቸው) በማዘዋወሩ ለሚያውቁ ሕዝቦች ማስረጃዎች አልሉ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/045005.mp3
|
وَاخْتِلَافِ اللَّيْلِ وَالنَّهَارِ وَمَا أَنزَلَ اللَّهُ مِنَ السَّمَاء مِن رِّزْقٍ فَأَحْيَا بِهِ الْأَرْضَ بَعْدَ مَوْتِهَا وَتَصْرِيفِ الرِّيَاحِ آيَاتٌ لِّقَوْمٍ يَعْقِلُونَ |
6 |
እነዚህ ባንተ ላይ በውነት የምናነባቸው ሲኾኑ የአላህ ማስረጃዎች ናቸው፡፡ ከአላህና ከማስረጃዎቹም ወዲያ በየትኛው ንግግር ያምናሉ? |
/content/ayah/audio/hudhaify/045006.mp3
|
تِلْكَ آيَاتُ اللَّهِ نَتْلُوهَا عَلَيْكَ بِالْحَقِّ فَبِأَيِّ حَدِيثٍ بَعْدَ اللَّهِ وَآيَاتِهِ يُؤْمِنُونَ |
7 |
ውሸታም ኀጢአተኛ ለኾነ ሁሉ ወዮለት፡፡ (ጥፋት ተገባው)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/045007.mp3
|
وَيْلٌ لِّكُلِّ أَفَّاكٍ أَثِيمٍ |
8 |
የአላህን አንቀጾች በእርሱ ላይ የሚነበቡለት ሲኾኑ ይሰማል፡፡ ከዚያም የኮራ ሲኾን እንዳልሰማት ኾኖ (በክሕደቱ ላይ) ይዘወትራል፡፡ በአሳማሚም ቅጣት አብስረው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/045008.mp3
|
يَسْمَعُ آيَاتِ اللَّهِ تُتْلَى عَلَيْهِ ثُمَّ يُصِرُّ مُسْتَكْبِرًا كَأَن لَّمْ يَسْمَعْهَا فَبَشِّرْهُ بِعَذَابٍ أَلِيمٍ |
9 |
ከአንቀጾቻችንም አንዳችን ባወቀ ጊዜ መሳለቂያ አድርጎ ይይዛታል፡፡ እነዚያ ለእነርሱ አዋራጅ ቅጣት አልላቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/045009.mp3
|
وَإِذَا عَلِمَ مِنْ آيَاتِنَا شَيْئًا اتَّخَذَهَا هُزُوًا أُوْلَئِكَ لَهُمْ عَذَابٌ مُّهِينٌ |
10 |
ከፊታቸውም ገሀነም አልለች፡፡ የሰበሰቡትም ሀብት ከእነርሱ ላይ ምንንም አይመልስላቸውም፡፡ ከአላህ ሌላም ረዳቶች አድርገው የያዙዋቸው (አይጠቅሟቸውም)፡፡ ለእነርሱም ታላቅ ቅጣት አልላቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/045010.mp3
|
مِن وَرَائِهِمْ جَهَنَّمُ وَلَا يُغْنِي عَنْهُم مَّا كَسَبُوا شَيْئًا وَلَا مَا اتَّخَذُوا مِن دُونِ اللَّهِ أَوْلِيَاء وَلَهُمْ عَذَابٌ عَظِيمٌ |
11 |
ይህ (ቁርኣን) መሪ ነው፡፡ እነዚያም በጌታቸው አንቀጾች የካዱት ለእነርሱ ከብርቱ ቅጣት የኾነ አሳማሚ ስቃይ አልላቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/045011.mp3
|
هَذَا هُدًى وَالَّذِينَ كَفَرُوا بِآيَاتِ رَبِّهِمْ لَهُمْ عَذَابٌ مَّن رِّجْزٍ أَلِيمٌ |
12 |
አላህ ያ ባሕርን በውስጡ ታንኳዎች በፈቃዱ እንዲንሻለሉበት ከችሮታውም እንድትፈልጉበት እንድታመሰግኑትም ለእናነተ የገራላችሁ ነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/045012.mp3
|
اللَّهُ الَّذِي سخَّرَ لَكُمُ الْبَحْرَ لِتَجْرِيَ الْفُلْكُ فِيهِ بِأَمْرِهِ وَلِتَبْتَغُوا مِن فَضْلِهِ وَلَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ |
13 |
ለናንተም በሰማያት ያለውንና በምድርም ያለውን ሁሉ በመላ ከእርሱ ሲኾን የገራላችሁ ነው፡፡ በዚህ ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች ተዓምራት አልለበት፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/045013.mp3
|
وَسَخَّرَ لَكُم مَّا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ جَمِيعًا مِّنْهُ إِنَّ فِي ذَلِكَ لَآيَاتٍ لَّقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ |
14 |
ለእነዚያ ለአመኑት ሰዎች (ምሕረት አድርጉ) በላቸው፡፡ ለእነዚያ የአላህን ቀኖች ለማይፈሩት ይምራሉና፡፡ ሕዝቦችን ይሠሩት በነበሩት ነገር ይመነዳ ዘንድ (ምሕረት አድርጉ በላቸው)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/045014.mp3
|
قُل لِّلَّذِينَ آمَنُوا يَغْفِرُوا لِلَّذِينَ لا يَرْجُون أَيَّامَ اللَّهِ لِيَجْزِيَ قَوْمًا بِما كَانُوا يَكْسِبُونَ |
15 |
መልካምን የሠራ ሰው ለነፍሱ ነው፡፡ ያከፋም ሰው በእርሷ ላይ ነው፡፡ ከዚያም ወደ ጌታችሁ ትመለሳላችሁ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/045015.mp3
|
مَنْ عَمِلَ صَالِحًا فَلِنَفْسِهِ وَمَنْ أَسَاء فَعَلَيْهَا ثُمَّ إِلَى رَبِّكُمْ تُرْجَعُونَ |
16 |
ለእስራኤል ልጆችም መጽሐፍንና ሕግን፣ ነቢይነትንም በእርግጥ ሰጠናቸው፡፡ ከመልካም ሲሳዮችም ለገስንላቸው፡፡ በዓለማት ላይም አበለጥናቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/045016.mp3
|
وَلَقَدْ آتَيْنَا بَنِي إِسْرَائِيلَ الْكِتَابَ وَالْحُكْمَ وَالنُّبُوَّةَ وَرَزَقْنَاهُم مِّنَ الطَّيِّبَاتِ وَفَضَّلْنَاهُمْ عَلَى الْعَالَمِينَ |
17 |
ከትዕዛዝም ግልጾችን ሰጠናቸው፡፡ ዕውቀቱም ከመጣላቸው በኋላ በመካከላቸው ለምቀኝነት እንጅ ለሌላ አልተለያዩም፡፡ ጌታህ በትንሣኤ ቀን በዚያ በእርሱ ይለያዩበት በነበሩት ነገር በመካከላቸው በእርግጥ ይፈርዳል፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/045017.mp3
|
وَآتَيْنَاهُم بَيِّنَاتٍ مِّنَ الْأَمْرِ فَمَا اخْتَلَفُوا إِلَّا مِن بَعْدِ مَا جَاءهُمْ الْعِلْمُ بَغْيًا بَيْنَهُمْ إِنَّ رَبَّكَ يَقْضِي بَيْنَهُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ فِيمَا كَانُوا فِيهِ يَخْتَلِفُونَ |
18 |
ከዚያም ከነገሩ (ከሃይማኖት) በትክክለኛይቱ ሕግ ላይ አደረግንህ፡፡ ስለዚህ ተከተላት፡፡ የእነዚያንም የማያውቁትን ሕዝቦች ዝንባሌዎች አትከተል፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/045018.mp3
|
ثُمَّ جَعَلْنَاكَ عَلَى شَرِيعَةٍ مِّنَ الْأَمْرِ فَاتَّبِعْهَا وَلَا تَتَّبِعْ أَهْوَاء الَّذِينَ لَا يَعْلَمُونَ |
19 |
እነርሱ ከአላህ (ቅጣት) ምንንም ከአንተ አይገፈትሩልህምና፡፡ በደለኞም ከፊላቸው የከፊሉ ረዳቶች ናቸው፡፡ አላህም የጥንቁቆቹ ረዳት ነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/045019.mp3
|
إِنَّهُمْ لَن يُغْنُوا عَنكَ مِنَ اللَّهِ شَيئًا وإِنَّ الظَّالِمِينَ بَعْضُهُمْ أَوْلِيَاء بَعْضٍ وَاللَّهُ وَلِيُّ الْمُتَّقِينَ |
20 |
ይሀ (ቁርኣን) ለሰዎች የልብ ብርሃኖች ነው፡፡ ለሚያረጋግጡም ሕዝቦች መሪና እዝነት ነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/045020.mp3
|
هَذَا بَصَائِرُ لِلنَّاسِ وَهُدًى وَرَحْمَةٌ لِّقَوْمِ يُوقِنُونَ |
21 |
እነዚያ ኀጢአቶችን የሠሩ ሕይወታቸውም ሞታቸውም ትክክል ሲኾን እንደእነዚያ እንደ አመኑትና መልካሞችን እንደሠሩት ልናደርጋቸው ይጠረጥራሉን? (አይጠርጥሩ)፡፡ የሚፈርዱት ምንኛ ከፋ! |
/content/ayah/audio/hudhaify/045021.mp3
|
أًمْ حَسِبَ الَّذِينَ اجْتَرَحُوا السَّيِّئَاتِ أّن نَّجْعَلَهُمْ كَالَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ سَوَاء مَّحْيَاهُم وَمَمَاتُهُمْ سَاء مَا يَحْكُمُونَ |
22 |
አላህም ሰማያትንና ምድርን (ለችሎታው እንደሚያመለክትባቸውና) ነፍስም ሁሉ በሠራችው ሥራ ትምመነዳ ዘንድ በትክክል ፈጠረ፡፡ እነርሱም አይበደሉም፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/045022.mp3
|
وَخَلَقَ اللَّهُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ بِالْحَقِّ وَلِتُجْزَى كُلُّ نَفْسٍ بِمَا كَسَبَتْ وَهُمْ لَا يُظْلَمُونَ |
23 |
ዝንባሌውን አምላኩ አድርጎ የያዘውን፣ አላህም ከዕውቀት ጋር ያጠመመውን፣ በጆሮውና በልቡ ላይም ያተመበትን፣ በዓይኑም ላይ ሺፋን ያደረገበትን ሰው አየህን! ታዲያ ከአላህ በኋላ የሚያቀናው ማነው? አትገሠጹምን? |
/content/ayah/audio/hudhaify/045023.mp3
|
أَفَرَأَيْتَ مَنِ اتَّخَذَ إِلَهَهُ هَوَاهُ وَأَضَلَّهُ اللَّهُ عَلَى عِلْمٍ وَخَتَمَ عَلَى سَمْعِهِ وَقَلْبِهِ وَجَعَلَ عَلَى بَصَرِهِ غِشَاوَةً فَمَن يَهْدِيهِ مِن بَعْدِ اللَّهِ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ |
24 |
እርሷም (ሕይወት) የቅርቢቱ ሕይወታችን እንጅ ሌላ አይደለችም፡፡ «እንሞታለን፤ ሕያውም እንኾናለን፡፡ ከጊዜም (ማለፍ) በስተቀር ሌላ አያጠፋንም» አሉ፡፡ ለእነርሱም በዚህ (በሚሉት) ምንም ዕውቀት የላቸውም፡፡ እነርሱ የሚጠራጠሩ እንጅ ሌላ አይደሉም፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/045024.mp3
|
وَقَالُوا مَا هِيَ إِلَّا حَيَاتُنَا الدُّنْيَا نَمُوتُ وَنَحْيَا وَمَا يُهْلِكُنَا إِلَّا الدَّهْرُ وَمَا لَهُم بِذَلِكَ مِنْ عِلْمٍ إِنْ هُمْ إِلَّا يَظُنُّونَ |
25 |
አንቀጾቻችንም ግልጾች ኾነው በእነርሱ ላይ በተነበቡላቸው ጊዜ ክርክራቸው «እውነተኞች እንደ ኾናችሁ አባቶቻችንን አምጡ» ማለት እንጅ ሌላ አልነበረም፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/045025.mp3
|
وَإِذَا تُتْلَى عَلَيْهِمْ آيَاتُنَا بَيِّنَاتٍ مَّا كَانَ حُجَّتَهُمْ إِلَّا أَن قَالُوا ائْتُوا بِآبَائِنَا إِن كُنتُمْ صَادِقِينَ |
26 |
«አላህ ሕያው ያደርጋችኋል፤ ከዚያም ይገድላችኋል፣ ከዚያም ወደ ትንሣኤ ቀን ይሰበስባችኋል፡፡ በእርሱ ጥርጥር የለበትም፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም» በላቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/045026.mp3
|
قُلِ اللَّهُ يُحْيِيكُمْ ثُمَّ يُمِيتُكُمْ ثُمَّ يَجْمَعُكُمْ إِلَى يَوْمِ الْقِيَامَةِ لَا رَيبَ فِيهِ وَلَكِنَّ أَكَثَرَ النَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ |
27 |
የሰማያትና የምድር ግዛት የአላህ ብቻ ነው፡፡ ሰዓቲቱም በምትቆምበት ቀን ያን ጊዜ አጥፊዎች ሁሉ ይከስራሉ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/045027.mp3
|
وَلَلَّهِ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرضِ وَيَومَ تَقُومُ السَّاعَةُ يَوْمَئِذٍ يَخْسَرُ الْمُبْطِلُونَ |
28 |
ሕዝብንም ሁሉ ተንበርካኪ ኾና ታያታለህ፡፡ ሕዝብ ሁሉ ወደ መጽሐፏ ትጥጠራለች፡፡ «ዛሬ ትሠሩት የነበራችሁትን ነገር ትመነዳላችሁ» (ይባላሉ)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/045028.mp3
|
وَتَرَى كُلَّ أُمَّةٍ جَاثِيَةً كُلُّ أُمَّةٍ تُدْعَى إِلَى كِتَابِهَا الْيَوْمَ تُجْزَوْنَ مَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ |
29 |
ይህ መጽሐፋችን ነው፡፡ በእናንተ ላይ በእውነት ይናገራል፡፡ እኛ ያንን ትሠሩት የነበራችሁትን እናስገለብጥ ነበርን (ይባላሉ)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/045029.mp3
|
هَذَا كِتَابُنَا يَنطِقُ عَلَيْكُم بِالْحَقِّ إِنَّا كُنَّا نَسْتَنسِخُ مَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ |
30 |
እነዚያ ያመኑትና መልካሞችን የሠሩትማ ጌታቸው በእዝነቱ ውስጥ ያገባቸዋል፡፡ ይህ እርሱ ግልጽ የኾነ ማግኘት ነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/045030.mp3
|
فَأَمَّا الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ فَيُدْخِلُهُمْ رَبُّهُمْ فِي رَحْمَتِهِ ذَلِكَ هُوَ الْفَوْزُ الْمُبِينُ |
31 |
እነዚያም የካዱትማ (ለእነርሱ ይባላሉ) «አንቀጾቼ በእናንተ ላይ ይነበቡ አልነበሩምን? ኮራችሁም፡፡ ከሓዲዎች ሕዝቦችም ነበራችሁ፡፡» |
/content/ayah/audio/hudhaify/045031.mp3
|
وَأَمَّا الَّذِينَ كَفَرُوا أَفَلَمْ تَكُنْ آيَاتِي تُتْلَى عَلَيْكُمْ فَاسْتَكْبَرْتُمْ وَكُنتُمْ قَوْمًا مُّجْرِمِينَ |
32 |
«የአላህ ቀጠሮ እውነት ነው፡፡ ሰዓቲቱም በእርሷ (መምጣት) ጥርጥር የለም፡፡» በተባለ ጊዜም «ሰዓቲቱ ምን እንደ ኾነች አናውቅም፡፡ መጠራጠርን የምንጠራጠር እንጅ ሌላ አይደለንም፡፡ እኛም አረጋጋጮች አይደለንም» አላችሁ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/045032.mp3
|
وَإِذَا قِيلَ إِنَّ وَعْدَ اللَّهِ حَقٌّ وَالسَّاعَةُ لَا رَيْبَ فِيهَا قُلْتُم مَّا نَدْرِي مَا السَّاعَةُ إِن نَّظُنُّ إِلَّا ظَنًّا وَمَا نَحْنُ بِمُسْتَيْقِنِينَ |
33 |
የሠሩዋቸውም ኀጢአቶች ለእነርሱ ይገለጹላቸዋል፡፡ ያም በእርሱ ይሳለቁበት የነበሩት ቅጣት በእነርሱ ላይ ይወርድባቸዋል፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/045033.mp3
|
وَبَدَا لَهُمْ سَيِّئَاتُ مَا عَمِلُوا وَحَاقَ بِهِم مَّا كَانُوا بِهِ يَسْتَهْزِئُون |
34 |
«ይህንንም ቀናችሁን መገናኘትን እንደ ረሳችሁ ዛሬ እንረሳችኋለን፡፡ (እንተዋችኋለን)፡፡ መኖሪያችሁም እሳት ናት፡፡ ለእናንተም ከረዳቶች ምንም የላችሁም» ይባላል፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/045034.mp3
|
وَقِيلَ الْيَوْمَ نَنسَاكُمْ كَمَا نَسِيتُمْ لِقَاء يَوْمِكُمْ هَذَا وَمَأْوَاكُمْ النَّارُ وَمَا لَكُم مِّن نَّاصِرِينَ |
35 |
ይህ እናንተ የአላህን አንቀጾች መቀለጃ አድርጋችሁ በመያዛችሁና ቅርቢቱም ሕይወት ስለአታለለቻችሁ ነው፤ (ይባላሉ)፡፡ ዛሬ ከእርሷ አይወጥጡም፤ እነርሱም በወቀሳ አይታለፉም፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/045035.mp3
|
ذَلِكُم بِأَنَّكُمُ اتَّخَذْتُمْ آيَاتِ اللَّهِ هُزُوًا وَغَرَّتْكُمُ الْحَيَاةُ الدُّنْيَا فَالْيَوْمَ لَا يُخْرَجُونَ مِنْهَا وَلَا هُمْ يُسْتَعْتَبُونَ |
36 |
ምስጋናም ለአላህ ለሰማያት ጌታ ለምድርም ጌታ ለዓለማት ጌታ የተገባው ነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/045036.mp3
|
فَلِلَّهِ الْحَمْدُ رَبِّ السَّمَاوَاتِ وَرَبِّ الْأَرْضِ رَبِّ الْعَالَمِينَ |
37 |
ኩራትም በሰማያትም በምድርም ለእርሱ ብቻ ነው፡፡ እርሱም አሸነፊው ጥበበኛው ነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/045037.mp3
|
وَلَهُ الْكِبْرِيَاء فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَهُوَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ |