Al-Qari'a

Change Language
Change Surah
Change Recitation

Amharic: Muhammed Sadiq and Muhammed Sani Habib

Play All
# Translation Ayah
1 ቆርቋሪይቱ (ጩኸት)፤ الْقَارِعَةُ
2 ምን አስደናቂ ቆርቋሪ ናት! مَا الْقَارِعَةُ
3 ቆርቋሪይቱም ምን እንደኾነች ምን አሳወቀህ? وَمَا أَدْرَاكَ مَا الْقَارِعَةُ
4 ሰዎች እንደ ተበታተነ ቢራቢሮ (ወይም ኩብኩባ) በሚኾኑበት ቀን፤ يَوْمَ يَكُونُ النَّاسُ كَالْفَرَاشِ الْمَبْثُوثِ
5 ጋራዎችም እንደ ተነደፈ ሱፍ በሚኾኑበት (ቀን ልቦችን በድንጋጤ ትቆረቁራለች፡፡) وَتَكُونُ الْجِبَالُ كَالْعِهْنِ الْمَنفُوشِ
6 ሚዛኖቹ የከበዱለት ሰውማ፤ فَأَمَّا مَن ثَقُلَتْ مَوَازِينُهُ
7 እርሱ በምትወደድ ኑሮ ውስጥ ይኾናል፡፡ فَهُوَ فِي عِيشَةٍ رَّاضِيَةٍ
8 ሚዛኖቹም የቀለሉበት ሰውማ፤ وَأَمَّا مَنْ خَفَّتْ مَوَازِينُهُ
9 መኖሪያው ሃዊያህ ናት فَأُمُّهُ هَاوِيَةٌ
10 እርሷም ምን እንደ ኾነች ምን አሳወቀህ? وَمَا أَدْرَاكَ مَا هِيَهْ
11 (እርሷ) በጣም ተኳሳ እሳት ናት፡፡ نَارٌ حَامِيَةٌ
;