1 |
አንተ ተከናናቢው ሆይ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/073001.mp3
|
يَا أَيُّهَا الْمُزَّمِّلُ |
2 |
ሌሊቱን ሁሉ ጥቂት ሲቀር ቁም፤ (ስገደ)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/073002.mp3
|
قُمِ اللَّيْلَ إِلَّا قَلِيلًا |
3 |
ግማሹን (ቁም)፤ ወይም ከርሱ ጥቂትን ቀንስ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/073003.mp3
|
نِصْفَهُ أَوِ انقُصْ مِنْهُ قَلِيلًا |
4 |
ወይም በእርሱ ላይ ጨምር፡፡ ቁርኣንንም በዝግታ ማንበብን አንብብ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/073004.mp3
|
أَوْ زِدْ عَلَيْهِ وَرَتِّلِ الْقُرْآنَ تَرْتِيلًا |
5 |
እኛ ባንተ ላይ ከባድ ቃልን እንጥላለንና፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/073005.mp3
|
إِنَّا سَنُلْقِي عَلَيْكَ قَوْلًا ثَقِيلًا |
6 |
የሌሊት መነሳት እርሷ (ሕዋሳትንና ልብን) ለማስማማት በጣም ብርቱ ናት፡፡ ለማንበብም ትክክለኛ ናት፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/073006.mp3
|
إِنَّ نَاشِئَةَ اللَّيْلِ هِيَ أَشَدُّ وَطْءًا وَأَقْوَمُ قِيلًا |
7 |
ላንተ በቀን ውስጥ ረዥም መዘዋወር አልለህ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/073007.mp3
|
إِنَّ لَكَ فِي اَلنَّهَارِ سَبْحًا طَوِيلًا |
8 |
የጌታህንም ስም አውሳ፤ ወደእርሱም (መግገዛት) መቋረጥን ተቋረጥ ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/073008.mp3
|
وَاذْكُرِ اسْمَ رَبِّكَ وَتَبَتَّلْ إِلَيْهِ تَبْتِيلًا |
9 |
(እርሱም) የምሥራቅና የምዕራብ ጌታ ነው፡፡ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ መጠጊያ አድርገህም ያዘው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/073009.mp3
|
رَبُّ الْمَشْرِقِ وَالْمَغْرِبِ لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ فَاتَّخِذْهُ وَكِيلًا |
10 |
(ከሓዲዎች) በሚሉትም ላይ ታገሥ፡፡ መልካምንም መተው ተዋቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/073010.mp3
|
وَاصْبِرْ عَلَى مَا يَقُولُونَ وَاهْجُرْهُمْ هَجْرًا جَمِيلًا |
11 |
የድሎት ባለቤቶችም ከኾኑት አስተባባዮች ጋር ተዎኝ፡፡ ጥቂትንም ጊዜ አቆያቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/073011.mp3
|
وَذَرْنِي وَالْمُكَذِّبِينَ أُولِي النَّعْمَةِ وَمَهِّلْهُمْ قَلِيلًا |
12 |
እኛ ዘንድ ከባድ ማሰሪያዎች እሳትም አልለና፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/073012.mp3
|
إِنَّ لَدَيْنَا أَنكَالًا وَجَحِيمًا |
13 |
የሚያንቅ ምግብም፤ አሳማሚ ቅጣትም (አልለ) |
/content/ayah/audio/hudhaify/073013.mp3
|
وَطَعَامًا ذَا غُصَّةٍ وَعَذَابًا أَلِيمًا |
14 |
ምድርና ገራዎች በሚርገፈገፉበት፣ ጋራዎችም ፈሳሽ የአሸዋ ክምር በሚኾኑበት ቀን፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/073014.mp3
|
يَوْمَ تَرْجُفُ الْأَرْضُ وَالْجِبَالُ وَكَانَتِ الْجِبَالُ كَثِيبًا مَّهِيلًا |
15 |
እኛ በእናንተ ላይ መስካሪ መልክተኛን ወደእናንተ ላክን፡፡ ወደ ፈርዖን መልክተኛን እንደላክን፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/073015.mp3
|
إِنَّا أَرْسَلْنَا إِلَيْكُمْ رَسُولًا شَاهِدًا عَلَيْكُمْ كَمَا أَرْسَلْنَا إِلَى فِرْعَوْنَ رَسُولًا |
16 |
ፈርዖንም መልክተኛውን አመጸ፤ ብርቱ መያዝንም ያዝነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/073016.mp3
|
فَعَصَى فِرْعَوْنُ الرَّسُولَ فَأَخَذْنَاهُ أَخْذًا وَبِيلًا |
17 |
ብትክዱ ልጆችን ሸበቶዎች የሚያደርገውን ቀን (ቅጣት) እንዴት ትጠበቃላችሁ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/073017.mp3
|
فَكَيْفَ تَتَّقُونَ إِن كَفَرْتُمْ يَوْمًا يَجْعَلُ الْوِلْدَانَ شِيبًا |
18 |
ሰማዩ በርሱ (በዚያ ቀን) ተሰንጣቂ ነው፡፡ ቀጠሮው ተፈጻሚ ነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/073018.mp3
|
السَّمَاء مُنفَطِرٌ بِهِ كَانَ وَعْدُهُ مَفْعُولًا |
19 |
ይህቺ መገሠጫ ናት፡፡ (መዳንን) የሻም ሰው ወደ ጌታው መንገድን ይይዛል፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/073019.mp3
|
إِنَّ هَذِهِ تَذْكِرَةٌ فَمَن شَاء اتَّخَذَ إِلَى رَبِّهِ سَبِيلًا |
20 |
አንተ ከሌሊቱ ሁለት እጅ ያነሰን ግማሹንም ሲሶውንም የምትቆም መኾንህን ጌታህ በእርግጥ ያውቃል፡፡ ከእነዚያም አብረውህ ካሉት ከፊሎች (የሚቆሙ መኾናቸውን ያውቃል)፡፡ አላህም ሌሊትንና ቀንን ይለክካል፡፡ (ሌሊቱን) የማታዳርሱት መኾናችሁን ዐወቀ፡፡ በእናንተ ላይም (ወደ ማቃለል) ተመለሰላችሁ፡፡ ስለዚህ ከቁርኣን (በስግደት) የተቻላችሁን አንብቡ፡፡ ከእናንተ ውስጥ በሽተኞች፣ ሌሎችም ከአላህ ችሮታ ለመፈለግ በምድር ላይ የሚጓዙ፣ ሌሎችም በአላህ መንገድ (ሃይማኖት) የሚጋደሉ እንደሚኖሩ ዐወቀ፡፡ (አቃለለላቸውም)፡፡ ከእርሱም የተቻለችሁን አንብቡ፡፡ ሶላትንም ስገዱ፡፡ ዘካንም ስጡ፡፡ ለአላህም መልካም ብደርን አበድሩ፡፡ ከመልካም ሥራም ለነፍሶቻችሁ የምታስቀድሙትን ሁሉ እርሱ የተሻለና በምንዳም ታላቅ ኾኖ አላህ ዘንድ ታገኙታላችሁ፡፡ አላህንም ምሕረትን ለምኑት፡፡ አላህ በጣም መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/073020.mp3
|
إِنَّ رَبَّكَ يَعْلَمُ أَنَّكَ تَقُومُ أَدْنَى مِن ثُلُثَيِ اللَّيْلِ وَنِصْفَهُ وَثُلُثَهُ وَطَائِفَةٌ مِّنَ الَّذِينَ مَعَكَ وَاللَّهُ يُقَدِّرُ اللَّيْلَ وَالنَّهَارَ عَلِمَ أَن لَّن تُحْصُوهُ فَتَابَ عَلَيْكُمْ فَاقْرَؤُوا مَا تَيَسَّرَ مِنَ الْقُرْآنِ عَلِمَ أَن سَيَكُونُ مِنكُم مَّرْضَى وَآخَرُونَ يَضْرِبُونَ فِي الْأَرْضِ يَبْتَغُونَ مِن فَضْلِ اللَّهِ وَآخَرُونَ يُقَاتِلُونَ فِي سَبِيلِ اللَّهِ فَاقْرَؤُوا مَا تَيَسَّرَ مِنْهُ وَأَقِيمُوا الصَّلَاةَ وَآتُوا الزَّكَاةَ وَأَقْرِضُوا اللَّهَ قَرْضًا حَسَنًا وَمَا تُقَدِّمُوا لِأَنفُسِكُم مِّنْ خَيْرٍ تَجِدُوهُ عِندَ اللَّهِ هُوَ خَيْرًا وَأَعْظَمَ أَجْرًا وَاسْتَغْفِرُوا اللَّهَ إِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ |