1 |
ነ.(ኑን)፤ በብርእ እምላለሁ በዚያም (መልአኮች) በሚጽፉት፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/068001.mp3
|
ن وَالْقَلَمِ وَمَا يَسْطُرُونَ |
2 |
አንተ በጌታህ ጸጋ የተጎናጸፍክ ስትኾን ዕብድ አይደለህም፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/068002.mp3
|
مَا أَنتَ بِنِعْمَةِ رَبِّكَ بِمَجْنُونٍ |
3 |
ላንተም (ከጌታህ) የማይቋረጥ ዋጋ በእርግጥ አልለህ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/068003.mp3
|
وَإِنَّ لَكَ لَأَجْرًا غَيْرَ مَمْنُونٍ |
4 |
አንተም በታላቅ ጠባይ ላይ ነህ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/068004.mp3
|
وَإِنَّكَ لَعَلى خُلُقٍ عَظِيمٍ |
5 |
ወደፊትም ታያለህ፤ ያያሉም፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/068005.mp3
|
فَسَتُبْصِرُ وَيُبْصِرُونَ |
6 |
ዕብደት በማንኛችሁ እንዳልለ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/068006.mp3
|
بِأَييِّكُمُ الْمَفْتُونُ |
7 |
ጌታህ እርሱ ከመንገዱ የተሳሳተውን ሰው ዐዋቂ ነው፡፡ እርሱም ተመሪዎቹን ዐዋቂ ነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/068007.mp3
|
إِنَّ رَبَّكَ هُوَ أَعْلَمُ بِمَن ضَلَّ عَن سَبِيلِهِ وَهُوَ أَعْلَمُ بِالْمُهْتَدِينَ |
8 |
ለአስተባባዮችም አትታዝዙ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/068008.mp3
|
فَلَا تُطِعِ الْمُكَذِّبِينَ |
9 |
ብትመሳሰላቸውና ቢመሳሰሉህ ተመኙ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/068009.mp3
|
وَدُّوا لَوْ تُدْهِنُ فَيُدْهِنُونَ |
10 |
ወራዳንም ሁሉ አትታዘዝ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/068010.mp3
|
وَلَا تُطِعْ كُلَّ حَلَّافٍ مَّهِينٍ |
11 |
ሰውን አነዋሪንና በማሳበቅ ኼያጅን፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/068011.mp3
|
هَمَّازٍ مَّشَّاء بِنَمِيمٍ |
12 |
ለበጎ ነገር በጣም ከልካይን፣ ወሰን አላፊን፣ ኃጢአተኛን፤ |
/content/ayah/audio/hudhaify/068012.mp3
|
مَنَّاعٍ لِّلْخَيْرِ مُعْتَدٍ أَثِيمٍ |
13 |
ልበ ደረቅን፣ ከዚህ በኋላ ዲቃላን (ሁሉ አትታዘዝ)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/068013.mp3
|
عُتُلٍّ بَعْدَ ذَلِكَ زَنِيمٍ |
14 |
የገንዘብና የልጆች ባለቤት በመኾኑ (ያስተባብላል)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/068014.mp3
|
أَن كَانَ ذَا مَالٍ وَبَنِينَ |
15 |
በእርሱ ላይ አንቀጾቻችን በሚነበቡ ጊዜ «የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች ናቸው» ይላል፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/068015.mp3
|
إِذَا تُتْلَى عَلَيْهِ آيَاتُنَا قَالَ أَسَاطِيرُ الْأَوَّلِينَ |
16 |
በአፍንጫው ላይ በእርግጥ (የሚነወርበት) ምልክት እናደርግበታለን፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/068016.mp3
|
سَنَسِمُهُ عَلَى الْخُرْطُومِ |
17 |
እኛ የአትክልቲቱን ባለቤቶቸ እንደ ሞከርን (የመካን ሰዎች) ሞከርናቸው፡፡ ማልደው (ፍሬዋን) ሊለቅሟት በማሉ ጊዜ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/068017.mp3
|
إِنَّا بَلَوْنَاهُمْ كَمَا بَلَوْنَا أَصْحَابَ الْجَنَّةِ إِذْ أَقْسَمُوا لَيَصْرِمُنَّهَا مُصْبِحِينَ |
18 |
(በመሓላቸው) አያስቀሩምም፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/068018.mp3
|
وَلَا يَسْتَثْنُونَ |
19 |
እነርሱ የተኙ ኾነውም ሳሉ ከጌታህ የኾነ ዟሪ በእርሷ ላይ ዞረባት፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/068019.mp3
|
فَطَافَ عَلَيْهَا طَائِفٌ مِّن رَّبِّكَ وَهُمْ نَائِمُونَ |
20 |
እንደ ሌሊት ጨለማም ኾና አነጋች፤ (ከሰለች)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/068020.mp3
|
فَأَصْبَحَتْ كَالصَّرِيمِ |
21 |
ያነጉም ኾነው ተጠራሩ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/068021.mp3
|
فَتَنَادَوا مُصْبِحِينَ |
22 |
«ቆራጮች እንደ ኾናችሁ በእርሻቸሁ ላይ ማልዱ» በማለት፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/068022.mp3
|
أَنِ اغْدُوا عَلَى حَرْثِكُمْ إِن كُنتُمْ صَارِمِينَ |
23 |
እነርሱ የሚንሾካሾኩ ኾነው ኼዱም፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/068023.mp3
|
فَانطَلَقُوا وَهُمْ يَتَخَافَتُونَ |
24 |
ዛሬ በእናንተ ላይ ድኻ እንዳይገባት በማለት፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/068024.mp3
|
أَن لَّا يَدْخُلَنَّهَا الْيَوْمَ عَلَيْكُم مِّسْكِينٌ |
25 |
(ድኾችን) በመከልከልም ላይ (በሐሳባቸው) ቻዮች ኾነው ማለዱ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/068025.mp3
|
وَغَدَوْا عَلَى حَرْدٍ قَادِرِينَ |
26 |
(ተቃጥላ) ባዩዋትም ጊዜ «እኛ በእርግጥ ተሳሳቾች ነን» አሉ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/068026.mp3
|
فَلَمَّا رَأَوْهَا قَالُوا إِنَّا لَضَالُّونَ |
27 |
«ይልቁንም እኛ የተከለከልን ነን» አሉ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/068027.mp3
|
بَلْ نَحْنُ مَحْرُومُونَ |
28 |
ትክክለኛቸው «ለእናንተ አላህን ለምን አታጠሩም አላልኳችሁምን?» አላቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/068028.mp3
|
قَالَ أَوْسَطُهُمْ أَلَمْ أَقُل لَّكُمْ لَوْلَا تُسَبِّحُونَ |
29 |
«ጌታችን ጥራት ይገባው፡፡ እኛ በዳዮች ነበርን፤» አሉ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/068029.mp3
|
قَالُوا سُبْحَانَ رَبِّنَا إِنَّا كُنَّا ظَالِمِينَ |
30 |
የሚወቃቀሱም ኾነው ከፊሎቻቸው በከፊሉ ላይ መጡ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/068030.mp3
|
فَأَقْبَلَ بَعْضُهُمْ عَلَى بَعْضٍ يَتَلَاوَمُونَ |
31 |
«ዋ ጥፋታችን! እኛ ድንበር አላፊዎች ነበርን፤» አሉ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/068031.mp3
|
قَالُوا يَا وَيْلَنَا إِنَّا كُنَّا طَاغِينَ |
32 |
«ጌታችን ከእርሷ የተሻለን (አትክልት) ሊለውጠን ይከጀላል፡፡ እኛ ወደ ጌታችን ከጃዮች ነን፤» (አሉ)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/068032.mp3
|
عَسَى رَبُّنَا أَن يُبْدِلَنَا خَيْرًا مِّنْهَا إِنَّا إِلَى رَبِّنَا رَاغِبُونَ |
33 |
ቅጣቱ እንደዚሁ ነው፡፡ የመጨረሻይቱም ዓለም ቅጣት ታላቅ ነው፡፡ የሚያውቁት በኾኑ ኖሮ (በተጠነቀቁ ነበር)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/068033.mp3
|
كَذَلِكَ الْعَذَابُ وَلَعَذَابُ الْآخِرَةِ أَكْبَرُ لَوْ كَانُوا يَعْلَمُونَ |
34 |
ለጥንቁቆቹ በጌታቸው ዘንድ መጠቀሚያ ገነቶች አሏቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/068034.mp3
|
إِنَّ لِلْمُتَّقِينَ عِندَ رَبِّهِمْ جَنَّاتِ النَّعِيمِ |
35 |
ሙስሊሞቹን እንደ ከሓዲዎች እናደርጋለን? |
/content/ayah/audio/hudhaify/068035.mp3
|
أَفَنَجْعَلُ الْمُسْلِمِينَ كَالْمُجْرِمِينَ |
36 |
ለእናንተ ምን (አስረጅ) አላችሁ? እንዴት ትፈርዳላችሁ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/068036.mp3
|
مَا لَكُمْ كَيْفَ تَحْكُمُونَ |
37 |
በእውነቱ ለእናንተ በእርሱ የምታጠኑበት መጽሐፍ አላችሁን? |
/content/ayah/audio/hudhaify/068037.mp3
|
أَمْ لَكُمْ كِتَابٌ فِيهِ تَدْرُسُونَ |
38 |
በውስጡ ለእናንተ የምትመርጡት አላችሁ (የሚል) |
/content/ayah/audio/hudhaify/068038.mp3
|
إِنَّ لَكُمْ فِيهِ لَمَا تَخَيَّرُونَ |
39 |
ወይስ ለእናንተ የምትፈርዱት አላችሁ በማለት (ቃል ኪዳን የገባንላችሁ) እስከ ትንሣኤ ቀን ደራሽ የኾኑ መሓላዎች ለእናንተ በእኛ ላይ አሏችሁን? |
/content/ayah/audio/hudhaify/068039.mp3
|
أَمْ لَكُمْ أَيْمَانٌ عَلَيْنَا بَالِغَةٌ إِلَى يَوْمِ الْقِيَامَةِ إِنَّ لَكُمْ لَمَا تَحْكُمُونَ |
40 |
በዚህ ማንኛቸው ተያያዥ እንደ ኾነ ጠይቃቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/068040.mp3
|
سَلْهُم أَيُّهُم بِذَلِكَ زَعِيمٌ |
41 |
ወይስ ለእነርሱ (በፍርዳቸው ተስማሚ) «ተጋሪዎች» አሏቸውን? እውነተኞችም እንደኾኑ «ተጋሪዎቻቸውን» ያምጡ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/068041.mp3
|
أَمْ لَهُمْ شُرَكَاء فَلْيَأْتُوا بِشُرَكَائِهِمْ إِن كَانُوا صَادِقِينَ |
42 |
ባት የሚገለጥበትን (ከሓዲዎች) ወደ መስገድም የሚጥጠሩበትንና የማይችሉበት ቀን (አስታውስ)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/068042.mp3
|
يَوْمَ يُكْشَفُ عَن سَاقٍ وَيُدْعَوْنَ إِلَى السُّجُودِ فَلَا يَسْتَطِيعُونَ |
43 |
ዓይኖቻቸው የፈሩ ውርደት የምትሸፍናቸው ሲኾኑ፤ (ወደ ስግደት የሚጠሩበትን)፤ እነርሱም (በምድረ ዓለም) ደህና ኾነው ሳሉ ወደ ስግደት በእርግጥ ይጠሩ ነበሩ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/068043.mp3
|
خَاشِعَةً أَبْصَارُهُمْ تَرْهَقُهُمْ ذِلَّةٌ وَقَدْ كَانُوا يُدْعَوْنَ إِلَى السُّجُودِ وَهُمْ سَالِمُونَ |
44 |
በዚህም ንግግር ከሚያስተባብሉት ሰዎች ጋር ተዎኝ፡፡ (እነርሱን እኔ እበቃሃለሁ)፡፡ ከማያውቁት ስፍራ አዘናግተን እንይዛቸዋለን፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/068044.mp3
|
فَذَرْنِي وَمَن يُكَذِّبُ بِهَذَا الْحَدِيثِ سَنَسْتَدْرِجُهُم مِّنْ حَيْثُ لَا يَعْلَمُونَ |
45 |
እነርሱንም አዘገያለሁ፡፡ ዘዴዬ ብርቱ ነውና፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/068045.mp3
|
وَأُمْلِي لَهُمْ إِنَّ كَيْدِي مَتِينٌ |
46 |
በእውነቱ ዋጋን ትጠይቃቸዋለህን? ስለዚህ እነርሱ ከዕዳ የተከበዱ ናቸውን? |
/content/ayah/audio/hudhaify/068046.mp3
|
أَمْ تَسْأَلُهُمْ أَجْرًا فَهُم مِّن مَّغْرَمٍ مُّثْقَلُونَ |
47 |
ወይስ እነርሱ ዘንድ የሩቁ ምስጢር ዕውቀት አልለን? ስለዚህ እነርሱ ይጽፋሉን? |
/content/ayah/audio/hudhaify/068047.mp3
|
أَمْ عِندَهُمُ الْغَيْبُ فَهُمْ يَكْتُبُونَ |
48 |
ለጌታህም ፍርድ ታገሥ፤ (በመበሳጨትና ባለ መታገሥ) እንደ ዓሣው ባለቤትም (እንደ ዮናስ) አትኹን፡፡ እርሱ በጭንቀት የተመላ ኾኖ (ጌታውን) በተጣራ ጊዜ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/068048.mp3
|
فَاصْبِرْ لِحُكْمِ رَبِّكَ وَلَا تَكُن كَصَاحِبِ الْحُوتِ إِذْ نَادَى وَهُوَ مَكْظُومٌ |
49 |
ከጌታው የኾነ ጸጋ ባላገኘው ኖሮ በምድረ በዳ ተወቃሽ ኾኖ በተጣለ ነበር፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/068049.mp3
|
لَوْلَا أَن تَدَارَكَهُ نِعْمَةٌ مِّن رَّبِّهِ لَنُبِذَ بِالْعَرَاء وَهُوَ مَذْمُومٌ |
50 |
ጌታውም (በነቢይነት) መረጠው፡፡ ከደጋጎቹም አደረገው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/068050.mp3
|
فَاجْتَبَاهُ رَبُّهُ فَجَعَلَهُ مِنَ الصَّالِحِينَ |
51 |
እነሆ እነዚያም የካዱት ሰዎች ቁርኣኑን በሰሙ ጊዜ በዓይኖቻቸው ሊጥሉህ (ሊያጠፉህ) ይቀርባሉ፡፡ «እርሱም በእርግጥ ዕብድ ነው» ይላሉ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/068051.mp3
|
وَإِن يَكَادُ الَّذِينَ كَفَرُوا لَيُزْلِقُونَكَ بِأَبْصَارِهِمْ لَمَّا سَمِعُوا الذِّكْرَ وَيَقُولُونَ إِنَّهُ لَمَجْنُونٌ |
52 |
ግን እርሱ (ቁርኣን) ለዓለማት መገሰጫ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/068052.mp3
|
وَمَا هُوَ إِلَّا ذِكْرٌ لِّلْعَالَمِينَ |