1 |
አንተ ነቢዩ ሆይ! ሴቶችን መፍታት ባሰባችሁ ጊዜ፤ ለዒዳቸው ፍቱዋቸው፡፡ ዒዳንም ቁጠሩ፡፡ አላህንም ጌታችሁን ፍሩ፡፡ ግልጽ የኾነችን ጠያፍ ካልሠሩ በስተቀር ከቤቶቻቸው አታውጡዋቸው፤ አይውጡም፡፡ ይህችም የአላህ ሕግጋት ናት፡፡ የአላህንም ሕግጋት የተላለፈ ሰው በእርግጥ ነፍሱን በደለ፡፡ ከዚህ (ፍች) በኋላ አላህ (የመማለስ) ነገርን ምናልባት ያመጣ እንደኾነ አታውቅም፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/065001.mp3
|
يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ إِذَا طَلَّقْتُمُ النِّسَاء فَطَلِّقُوهُنَّ لِعِدَّتِهِنَّ وَأَحْصُوا الْعِدَّةَ وَاتَّقُوا اللَّهَ رَبَّكُمْ لَا تُخْرِجُوهُنَّ مِن بُيُوتِهِنَّ وَلَا يَخْرُجْنَ إِلَّا أَن يَأْتِينَ بِفَاحِشَةٍ مُّبَيِّنَةٍ وَتِلْكَ حُدُودُ اللَّهِ وَمَن يَتَعَدَّ حُدُودَ اللَّهِ فَقَدْ ظَلَمَ نَفْسَهُ لَا تَدْرِي لَعَلَّ اللَّهَ يُحْدِثُ بَعْدَ ذَلِكَ أَمْرًا |
2 |
ጊዜያቸውንም ለመዳረስ በተቃረቡ ጊዜ በመልካም ያዙዋቸው፡፡ ወይም በመልካም ተለያዩዋቸው፡፡ ከእናንተም ውስጥ ሁለት የትክክለኛነት ባለቤቶችን አስመስክሩ፡፡ ምስክርነትንም ለአላህ አስተካክሉ፡፡ ይህ በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምን የኾነ ሰው ሁሉ በእርሱ ይገሰጽበታል፡፡ አላህንም የሚፈራ ሰው ለእርሱ መውጫን ያደርግለታል፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/065002.mp3
|
فَإِذَا بَلَغْنَ أَجَلَهُنَّ فَأَمْسِكُوهُنَّ بِمَعْرُوفٍ أَوْ فَارِقُوهُنَّ بِمَعْرُوفٍ وَأَشْهِدُوا ذَوَيْ عَدْلٍ مِّنكُمْ وَأَقِيمُوا الشَّهَادَةَ لِلَّهِ ذَلِكُمْ يُوعَظُ بِهِ مَن كَانَ يُؤْمِنُ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ وَمَن يَتَّقِ اللَّهَ يَجْعَل لَّهُ مَخْرَجًا |
3 |
ከማያስበውም በኩል ሲሳየን ይሰጠዋል፡፡ በአላህም ላይ የሚጠጋ ሰው እርሱ በቂው ነው፡፡ አላህ ፈቃዱን አድራሽ ነው፡፡ አላህ ለነገሩ ሁሉ የተወሰነ ጊዜን በእርግጥ አድርጓል፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/065003.mp3
|
وَيَرْزُقْهُ مِنْ حَيْثُ لَا يَحْتَسِبُ وَمَن يَتَوَكَّلْ عَلَى اللَّهِ فَهُوَ حَسْبُهُ إِنَّ اللَّهَ بَالِغُ أَمْرِهِ قَدْ جَعَلَ اللَّهُ لِكُلِّ شَيْءٍ قَدْرًا |
4 |
እኒያም ከሴቶቻቸው ከአደፍ ያቋረጡት (በዒዳቸው ሕግ) ብትጠራጠሩ ዒዳቸው ሦስት ወር ነው፡፡ እኒያም ገና አደፍን ያላዩት (ዒዳቸው እንደዚሁ ነው)፡፡ የእርግዝና ባለቤቶችም ጊዜያቸው እርጉዛቸውን መውለድ ነው፡፡ አላህንም የሚፈራ ሰው ከነገሩ ሁሉ ለርሱ መግራትን ያደርግለታል፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/065004.mp3
|
وَاللَّائِي يَئِسْنَ مِنَ الْمَحِيضِ مِن نِّسَائِكُمْ إِنِ ارْتَبْتُمْ فَعِدَّتُهُنَّ ثَلَاثَةُ أَشْهُرٍ وَاللَّائِي لَمْ يَحِضْنَ وَأُوْلَاتُ الْأَحْمَالِ أَجَلُهُنَّ أَن يَضَعْنَ حَمْلَهُنَّ وَمَن يَتَّقِ اللَّهَ يَجْعَل لَّهُ مِنْ أَمْرِهِ يُسْرًا |
5 |
ይህ የአላህ ፍርድ ነው፡፡ ወደእናንተ አወረደው፡፡ አላህንም የሚፈራ ሰው ኀጢኣቶቹን ከእርሱ ይሰርይለታል፡፡ ምንዳንም ለእርሱ ያተልቅለታል፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/065005.mp3
|
ذَلِكَ أَمْرُ اللَّهِ أَنزَلَهُ إِلَيْكُمْ وَمَن يَتَّقِ اللَّهَ يُكَفِّرْ عَنْهُ سَيِّئَاتِهِ وَيُعْظِمْ لَهُ أَجْرًا |
6 |
ከችሎታችሁ ከተቀመጣችሁበት ስፍራ አስቀምጧቸው፡፡ በእነርሱም ላይ ልታጣብቡ አትጉዷቸው፡፡ የእርግዝና ባለቤቶችም ቢኾኑ እርጉዛቸውን እስኪወልዱ ድረስ በእነርሱ ላይ ቀልቡ፡፡ ለእናንተም (ልጆቻችሁን) ቢያጠቡላችሁ ምንዳዎቻቸውን ስጧቸው፡፡ በመካከላችሁም በመልካም ነገር ተመካከሩ፡፡ ብትቸጋገሩም ለእርሱ ሌላ (ሴት) ታጠባለታለች፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/065006.mp3
|
أَسْكِنُوهُنَّ مِنْ حَيْثُ سَكَنتُم مِّن وُجْدِكُمْ وَلَا تُضَارُّوهُنَّ لِتُضَيِّقُوا عَلَيْهِنَّ وَإِن كُنَّ أُولَاتِ حَمْلٍ فَأَنفِقُوا عَلَيْهِنَّ حَتَّى يَضَعْنَ حَمْلَهُنَّ فَإِنْ أَرْضَعْنَ لَكُمْ فَآتُوهُنَّ أُجُورَهُنَّ وَأْتَمِرُوا بَيْنَكُم بِمَعْرُوفٍ وَإِن تَعَاسَرْتُمْ فَسَتُرْضِعُ لَهُ أُخْرَى |
7 |
የችሎታ ባለቤት ከችሎታው ይቀልብ፡፡ በእርሱም ላይ ሲሳዩ የተጠበበበት ሰው አላህ ከሰጠው ይቀልብ አላህ ነፍስን የሰጣትን እንጅ አያስገድድም፡፡ አላህ ከችግር በኋላ ምቾትን በእርግጥ ያደርጋል፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/065007.mp3
|
لِيُنفِقْ ذُو سَعَةٍ مِّن سَعَتِهِ وَمَن قُدِرَ عَلَيْهِ رِزْقُهُ فَلْيُنفِقْ مِمَّا آتَاهُ اللَّهُ لَا يُكَلِّفُ اللَّهُ نَفْسًا إِلَّا مَا آتَاهَا سَيَجْعَلُ اللَّهُ َعْدَ عُسْرٍ يُسْرًا |
8 |
ከከተማም ከጌታዋ ትዕዛዝ ከመልክተኞቹም ያመጸች፣ ብርቱንም ቁጥጥር የተቆጣጠርናት፣ መጥፎንም ቅጣት የቀጣናት ብዙ ናት፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/065008.mp3
|
وَكَأَيِّن مِّن قَرْيَةٍ عَتَتْ عَنْ أَمْرِ رَبِّهَا وَرُسُلِهِ فَحَاسَبْنَاهَا حِسَابًا شَدِيدًا وَعَذَّبْنَاهَا عَذَابًا نُّكْرًا |
9 |
የነገርዋንም ቅጣት ቀመሰች፡፡ የነገርዋም መጨረሻ ከሳራ ኾነ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/065009.mp3
|
فَذَاقَتْ وَبَالَ أَمْرِهَا وَكَانَ عَاقِبَةُ أَمْرِهَا خُسْرًا |
10 |
አላህ ለእነርሱ ብርቱን ቅጣት አዘጋጀ፡፡ እናንተም የአእምሮ ባለቤቶች ሆይ! አላህን ፍሩ፡፡ እነዚያ ያመኑ (ሆይ)! አላህ ወደናንተ ግሳጼን በእርግጥ አወረደ፡፡ መልክተኛን (ላከ)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/065010.mp3
|
أَعَدَّ اللَّهُ لَهُمْ عَذَابًا شَدِيدًا فَاتَّقُوا اللَّهَ يَا أُوْلِي الْأَلْبَابِ الَّذِينَ آمَنُوا قَدْ أَنزَلَ اللَّهُ إِلَيْكُمْ ذِكْرًا |
11 |
እነዚያን ያመኑትንና መልካሞችን የሠሩትን ከጨለማዎች ወደ ብርሃን ያወጣ ዘንድ የአላህን አንቀጾች ገላጮች ሲኾኑ በእናንተ ላይ የሚያነብላችሁን (ላከ)፡፡ በአላህም አንቀጾች የሚያምን፣ መልካምን ሥራ የሚሠራም ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈስሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘለዓለም ዘውታሪዎች ሲኾኑ ያገባዋል፡፡ አላህ ለእርሱ ሲሳይን በእርግጥ አሳመረ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/065011.mp3
|
رَّسُولًا يَتْلُو عَلَيْكُمْ آيَاتِ اللَّهِ مُبَيِّنَاتٍ لِّيُخْرِجَ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ مِنَ الظُّلُمَاتِ إِلَى النُّورِ وَمَن يُؤْمِن بِاللَّهِ وَيَعْمَلْ صَالِحًا يُدْخِلْهُ جَنَّاتٍ تَجْرِي مِن تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا أَبَدًا قَدْ أَحْسَنَ اللَّهُ لَهُ رِزْقًا |
12 |
አላህ ያ ሰባትን ሰማያት የፈጠረ ነው፡፡ ከምድርም መሰላቸውን (ፈጥሮአል)፤ በመካከላቸው ትእዛዙ ይወርዳል፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ መኾኑን አላህም በነገሩ ሁሉ በዕውቀት ያካበበ መኾኑን በዕውቀት ያካበበ መኾኑን ታወቁ ዘንድ (ይህንን አሳወቃችሁ)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/065012.mp3
|
اللَّهُ الَّذِي خَلَقَ سَبْعَ سَمَاوَاتٍ وَمِنَ الْأَرْضِ مِثْلَهُنَّ يَتَنَزَّلُ الْأَمْرُ بَيْنَهُنَّ لِتَعْلَمُوا أَنَّ اللَّهَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ وَأَنَّ اللَّهَ قَدْ أَحَاطَ بِكُلِّ شَيْءٍ عِلْمًا |