1 |
በሰማያት ውስጥ ያለው በምድርም ውስጥ ያለው ሁሉ ለአላህ አሞገሠ፡፡ እርሱም አሸናፊው ጥበበኛው ነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/061001.mp3
|
سَبَّحَ لِلَّهِ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ وَهُوَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ |
2 |
እላንተ ያመናችሁ ሆይ! የማትሠሩትን ነገር ለምን ትናገራላችሁ? |
/content/ayah/audio/hudhaify/061002.mp3
|
يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آَمَنُوا لِمَ تَقُولُونَ مَا لَا تَفْعَلُونَ |
3 |
የማትሠሩን ነገር መናገራችሁ አላህ ዘንድ መጠላቱ ተለቀ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/061003.mp3
|
كَبُرَ مَقْتًا عِندَ اللَّهِ أَن تَقُولُوا مَا لَا تَفْعَلُونَ |
4 |
አላህ እነዚያን እነርሱ ልክ እንደ ተናሰ ግንብ የተሰለፉ ኾነው በመንገዱ (በሃይማኖቱ) የሚጋደሉትን ይወዳል፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/061004.mp3
|
إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الَّذِينَ يُقَاتِلُونَ فِي سَبِيلِهِ صَفًّا كَأَنَّهُم بُنيَانٌ مَّرْصُوصٌ |
5 |
ሙሳም ለሕዝቦቹ «ሕዝቦቼ ሆይ! እኔ ወደእናንተ የአላህ መልክተኛ መኾኔን በእርግጥ የምታውቁ ስትኾኑ ለምን ታሰቃዩኛላችሁ?» ባለ ጊዜ (አስታውስ፡፡ ከእውነት) በተዘነበሉም ጊዜ አላህ ልቦቻቸውን አዘነበላቸው፡፡ አላህም አመጸኞችን ሕዝቦች አያቀናም፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/061005.mp3
|
وَإِذْ قَالَ مُوسَى لِقَوْمِهِ يَا قَوْمِ لِمَ تُؤْذُونَنِي وَقَد تَّعْلَمُونَ أَنِّي رَسُولُ اللَّهِ إِلَيْكُمْ فَلَمَّا زَاغُوا أَزَاغَ اللَّهُ قُلُوبَهُمْ وَاللَّهُ لَا يَهْدِي الْقَوْمَ الْفَاسِقِينَ |
6 |
የመርየም ልጅ ዒሳም፡- «የእስራኤል ልጆች ሆይ! እኔ ከተውራት በፊቴ ያለውን የማረጋግጥና ከእኔ በኋላ በሚመጣው መልክተኛ ስሙ አሕመድ በኾነው የማበስር ስኾን ወደእናንተ (የተላክሁ) የአላህ መልክተኛ ነኝ» ባለ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ በግልጽ ተዓምራቶች በመጣቸውም ጊዜ «ይህ ግልጽ ድግምት ነው» አሉ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/061006.mp3
|
وَإِذْ قَالَ عِيسَى ابْنُ مَرْيَمَ يَا بَنِي إِسْرَائِيلَ إِنِّي رَسُولُ اللَّهِ إِلَيْكُم مُّصَدِّقًا لِّمَا بَيْنَ يَدَيَّ مِنَ التَّوْرَاةِ وَمُبَشِّرًا بِرَسُولٍ يَأْتِي مِن بَعْدِي اسْمُهُ أَحْمَدُ فَلَمَّا جَاءهُم بِالْبَيِّنَاتِ قَالُوا هَذَا سِحْرٌ مُّبِينٌ |
7 |
እርሱ ወደ ኢስላም የሚጥጠራ ሲኾን በአላህ ላይ ውሸትን ከቀጣጠፈ ሰውም ይበልጥ በደለኛ ማን ነው? አላህም በዳዮችን ሕዝቦች አይመራም፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/061007.mp3
|
وَمَنْ أَظْلَمُ مِمَّنِ افْتَرَى عَلَى اللَّهِ الْكَذِبَ وَهُوَ يُدْعَى إِلَى الْإِسْلَامِ وَاللَّهُ لَا يَهْدِي الْقَوْمَ الظَّالِمِينَ |
8 |
የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ሊያጠፉ ይሻሉ፡፡ አላህም ከሓዲዎቹ ቢጠሉም እንኳ ብርሃኑን ገላጭ ነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/061008.mp3
|
يُرِيدُونَ لِيُطْفِؤُوا نُورَ اللَّهِ بِأَفْوَاهِهِمْ وَاللَّهُ مُتِمُّ نُورِهِ وَلَوْ كَرِهَ الْكَافِرُونَ |
9 |
እርሱ ያ አጋሪዎቹ ቢጠሉም መልክተኛውን በመምሪያ (መጽሐፍ) በእውነተኛው ሃይማኖትም (በኢስላም) ከሃይማኖት ሁሉ በላይ ይፋ ሊያደርገው የላከ ነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/061009.mp3
|
هُوَ الَّذِي أَرْسَلَ رَسُولَهُ بِالْهُدَى وَدِينِ الْحَقِّ لِيُظْهِرَهُ عَلَى الدِّينِ كُلِّهِ وَلَوْ كَرِهَ الْمُشْرِكُونَ |
10 |
«እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከአሳማሚ ቅጣት የምታድናችሁ የኾነችን ንግድ ላመላክታችሁን?» (በላቸው)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/061010.mp3
|
يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آَمَنُوا هَلْ أَدُلُّكُمْ عَلَى تِجَارَةٍ تُنجِيكُم مِّنْ عَذَابٍ أَلِيمٍ |
11 |
(እርሷም) በአላህና በመልክተኛው ታምናላችሁ፣ በአላህ መንገድም በገንዘቦቻችሁ በነፍሶቻችሁም ትታገላላችሁ፣ ይህ የምታውቁ ብትኾኑ ለእናንተ የተሻለ ነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/061011.mp3
|
تُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ وَتُجَاهِدُونَ فِي سَبِيلِ اللَّهِ بِأَمْوَالِكُمْ وَأَنفُسِكُمْ ذَلِكُمْ خَيْرٌ لَّكُمْ إِن كُنتُمْ تَعْلَمُونَ |
12 |
ኃጢኣቶቻችሁን ለእናንተ ይምራል፡፡ ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውንም ገነቶች ያገባችኋል፡፡ በመኖሪያ ገነቶችም በሚያማምሩ ቤቶች ውስጥ (ያስቀምጣችኋል)፡፡ ይህ ታላቅ ዕድል ነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/061012.mp3
|
يَغْفِرْ لَكُمْ ذُنُوبَكُمْ وَيُدْخِلْكُمْ جَنَّاتٍ تَجْرِي مِن تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ وَمَسَاكِنَ طَيِّبَةً فِي جَنَّاتِ عَدْنٍ ذَلِكَ الْفَوْزُ الْعَظِيمُ |
13 |
ሌላይቱንም የምትወዷትን (ጸጋ ይሰጣችኋለ)፡፡ ከአላህ የኾነ እርዳታና ቅርብ የኾነ የአገር መክፈት ነው፡፡ ምእምናንንም አብስር፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/061013.mp3
|
وَأُخْرَى تُحِبُّونَهَا نَصْرٌ مِّنَ اللَّهِ وَفَتْحٌ قَرِيبٌ وَبَشِّرِ الْمُؤْمِنِينَ |
14 |
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! የመርየም ልጅ ዒሳ ለሐዋርያቶቹ «ወደ አላህ ረዳቴ ማነው?» እንዳለ ሐወርያቶቹም «እኛ የአላህ ረዳቶች ነን» እንዳሉት የአላህ ረዳቶች ኹኑ፡፡ ከእስራኤልም ልጆች አንደኛዋ ጭፍራ አመነች፡፡ ሌላይቱም ጭፍራ ካደች፡፡ እነዚያን ያመኑትንም በጠላታቸው ላይ አበረታናቸው፤ አሸናፊዎችም ኾኑ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/061014.mp3
|
يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آَمَنُوا كُونوا أَنصَارَ اللَّهِ كَمَا قَالَ عِيسَى ابْنُ مَرْيَمَ لِلْحَوَارِيِّينَ مَنْ أَنصَارِي إِلَى اللَّهِ قَالَ الْحَوَارِيُّونَ نَحْنُ أَنصَارُ اللَّهِ فَآَمَنَت طَّائِفَةٌ مِّن بَنِي إِسْرَائِيلَ وَكَفَرَت طَّائِفَةٌ فَأَيَّدْنَا الَّذِينَ آَمَنُوا عَلَى عَدُوِّهِمْ فَأَصْبَحُوا ظَاهِرِينَ |