1 |
መሰለፍን በሚሰለፉት፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037001.mp3
|
وَالصَّافَّاتِ صَفًّا |
2 |
መገሠጽንም በሚገሥጹት፤ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037002.mp3
|
فَالزَّاجِرَاتِ زَجْرًا |
3 |
ቁርኣንንም በሚያነቡት እምላለሁ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037003.mp3
|
فَالتَّالِيَاتِ ذِكْرًا |
4 |
አምላካችሁ በእርግጥ አንድ ነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037004.mp3
|
إِنَّ إِلَهَكُمْ لَوَاحِدٌ |
5 |
የሰማያትና የምድር በመካከላቸው ያለውም ፍጡር ሁሉ ጌታ ነው፡፡ የምሥራቆችም ጌታ ነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037005.mp3
|
رَبُّ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَمَا بَيْنَهُمَا وَرَبُّ الْمَشَارِقِ |
6 |
እኛ ቅርቢቱን ሰማይ በከዋክብት ጌጥ አጌጥናት፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037006.mp3
|
إِنَّا زَيَّنَّا السَّمَاء الدُّنْيَا بِزِينَةٍ الْكَوَاكِبِ |
7 |
አመጸኛም ከሆነ ሰይጣን ሁሉ መጠበቅን ጠበቅናት፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037007.mp3
|
وَحِفْظًا مِّن كُلِّ شَيْطَانٍ مَّارِدٍ |
8 |
ወደላይኛው ሰራዊት አያዳምጡም፡፡ ከየወገኑም ሁሉ ችቦ ይጣልባቸዋል፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037008.mp3
|
لَا يَسَّمَّعُونَ إِلَى الْمَلَإِ الْأَعْلَى وَيُقْذَفُونَ مِن كُلِّ جَانِبٍ |
9 |
የሚባረሩ ሲሆኑ (ይጣልባቸዋል)፡፡ ለእነሱም ዘውታሪ ቅጣት አላቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037009.mp3
|
دُحُورًا وَلَهُمْ عَذَابٌ وَاصِبٌ |
10 |
ንጥቂያን የነጠቀ ወዲያውም አብሪ ኮከብ የተከተለው ሲቀር፤ (እርሱ ይሰማዋል)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037010.mp3
|
إِلَّا مَنْ خَطِفَ الْخَطْفَةَ فَأَتْبَعَهُ شِهَابٌ ثَاقِبٌ |
11 |
ጠይቃቸውም፤ እነርሱ በአፈጣጠር ይበልጥ የበረቱ ናቸውን? ወይስ እኛ (ከእነርሱ በፊት) የፈጠርነው? (ፍጡር) እኛ ከሚጣበቅ ጭቃ ፈጠርናቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037011.mp3
|
فَاسْتَفْتِهِمْ أَهُمْ أَشَدُّ خَلْقًا أَم مَّنْ خَلَقْنَا إِنَّا خَلَقْنَاهُم مِّن طِينٍ لَّازِبٍ |
12 |
ይልቁንም (በማስተባበላቸው) ተደነቅህ፤(ከመደነቅህ) ይሳለቃሉም፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037012.mp3
|
بَلْ عَجِبْتَ وَيَسْخَرُونَ |
13 |
በተገሠጹም ጊዜ አይመለሱም፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037013.mp3
|
وَإِذَا ذُكِّرُوا لَا يَذْكُرُونَ |
14 |
ተዓምርን ባዩም ጊዜ ለመሳለቅ ይጠራራሉ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037014.mp3
|
وَإِذَا رَأَوْا آيَةً يَسْتَسْخِرُونَ |
15 |
ይላሉም «ይህ ግልጽ ድግምት እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037015.mp3
|
وَقَالُوا إِنْ هَذَا إِلَّا سِحْرٌ مُّبِينٌ |
16 |
«በሞትንና ዐፈርና አጥንቶችም በኾን ጊዜ እኛ የምንቀሰቀስ ነን? |
/content/ayah/audio/hudhaify/037016.mp3
|
أَئِذَا مِتْنَا وَكُنَّا تُرَابًا وَعِظَامًا أَئِنَّا لَمَبْعُوثُونَ |
17 |
«የቀድሞዎቹ አባቶችንም? (ይላሉ)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037017.mp3
|
أَوَآبَاؤُنَا الْأَوَّلُونَ |
18 |
«አዎን እናንተ ወራዶች ሆናችሁ (ትነሳላችሁ)» በላቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037018.mp3
|
قُلْ نَعَمْ وَأَنتُمْ دَاخِرُونَ |
19 |
እርሷም አንዲት ጩኸት ብቻ ናት፡፡ እነርሱም ወዲያውኑ (ምን እንደሚፈጸምባቸው) ያያሉ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037019.mp3
|
فَإِنَّمَا هِيَ زَجْرَةٌ وَاحِدَةٌ فَإِذَا هُمْ يَنظُرُونَ |
20 |
«ዋ ጥፋታችን! ይህ የፍርዱ ቀን ነው» ይላሉም፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037020.mp3
|
وَقَالُوا يَا وَيْلَنَا هَذَا يَوْمُ الدِّينِ |
21 |
«ይህ ያ በእርሱ ታስተባብሉ የነበራችሁት መለያው ቀን ነው» (ይባላሉ)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037021.mp3
|
هَذَا يَوْمُ الْفَصْلِ الَّذِي كُنتُمْ بِهِ تُكَذِّبُونَ |
22 |
(ለመላእክቶችም) «እነዚያን ነፍሶቻቸውን የበደሉትን ሰዎች ጓደኞቻቸውንም ይግገዟቸው የነበሩትንም (ጣዖታት) ሰብስቡ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037022.mp3
|
احْشُرُوا الَّذِينَ ظَلَمُوا وَأَزْوَاجَهُمْ وَمَا كَانُوا يَعْبُدُونَ |
23 |
«ከአላህ ሌላ (የሚገዙዋቸውን ሰብስቧቸው) ወደ እሳት መንገድም ምሩዋቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037023.mp3
|
مِن دُونِ اللَّهِ فَاهْدُوهُمْ إِلَى صِرَاطِ الْجَحِيمِ |
24 |
«አቁሟቸውም፡፡ እነርሱ ተጠያቂዎች ናቸውና» (ይባላል)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037024.mp3
|
وَقِفُوهُمْ إِنَّهُم مَّسْئُولُونَ |
25 |
(ለእነርሱም) «የማትረዳዱት ለእናንተ ምን አላችሁ? (ይባላሉ)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037025.mp3
|
مَا لَكُمْ لَا تَنَاصَرُونَ |
26 |
በእርግጥ እነርሱ ዛሬ እጃቸውን የሰጡ ወራዳዎች ናቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037026.mp3
|
بَلْ هُمُ الْيَوْمَ مُسْتَسْلِمُونَ |
27 |
የሚወቃቀሱም ሆነው ከፊላቸው በከፊሉ ላይ ይመጣሉ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037027.mp3
|
وَأَقْبَلَ بَعْضُهُمْ عَلَى بَعْضٍ يَتَسَاءلُونَ |
28 |
(ለአስከታዮቹ) እናንተ ከስተቀኝ ትመጡብን ነበር ይላሉ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037028.mp3
|
قَالُوا إِنَّكُمْ كُنتُمْ تَأْتُونَنَا عَنِ الْيَمِينِ |
29 |
(አስከታዮቹም) ይላሉ «አይደለም ፈጽሞ ምእምናን አልነበራችሁም፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037029.mp3
|
قَالُوا بَل لَّمْ تَكُونُوا مُؤْمِنِينَ |
30 |
«ለእኛም በእናንተ ላይ ምንም ስልጣን አልነበረንም፡፡ በእርግጥ እናንተ ጠማሞች ሕዝቦች ነበራችሁ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037030.mp3
|
وَمَا كَانَ لَنَا عَلَيْكُم مِّن سُلْطَانٍ بَلْ كُنتُمْ قَوْمًا طَاغِينَ |
31 |
«በእኛም ላይ የጌታችን ቃል ተረጋገጠብን፤ እኛ (ሁላችንም ቅጣቱን) ቀማሾች ነን፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037031.mp3
|
فَحَقَّ عَلَيْنَا قَوْلُ رَبِّنَا إِنَّا لَذَائِقُونَ |
32 |
«ወደ ጥምመት ጠራናችሁም፡፡ እኛ ጠማሞች ነበርንና» (ይላሉ)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037032.mp3
|
فَأَغْوَيْنَاكُمْ إِنَّا كُنَّا غَاوِينَ |
33 |
ስለዚህ እነርሱ በዚያ ቀን በቅጣቱ ነጋሪዎች ናቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037033.mp3
|
فَإِنَّهُمْ يَوْمَئِذٍ فِي الْعَذَابِ مُشْتَرِكُونَ |
34 |
እኛ በአመጸኞች ሁሉ እንደዚሁ እንሠራለን፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037034.mp3
|
إِنَّا كَذَلِكَ نَفْعَلُ بِالْمُجْرِمِينَ |
35 |
እነርሱ ከአላህ ሌላ አምላክ የለም በተባሉ ጊዜ ይኮሩ ነበሩ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037035.mp3
|
إِنَّهُمْ كَانُوا إِذَا قِيلَ لَهُمْ لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ يَسْتَكْبِرُونَ |
36 |
እኛ ለዕብድ ባለቅኔ ብለን አማልክቶቻችንን የምንተው ነን? ይሉም ነበር፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037036.mp3
|
وَيَقُولُونَ أَئِنَّا لَتَارِكُوا آلِهَتِنَا لِشَاعِرٍ مَّجْنُونٍ |
37 |
አይደለም እውነቱን (ሃይማኖት) አመጣ፡፡ መልክተኞቹንም እውነተኛነታቸውን አረጋገጠ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037037.mp3
|
بَلْ جَاء بِالْحَقِّ وَصَدَّقَ الْمُرْسَلِينَ |
38 |
እናንተ አሳማሚውን ቅጣት በእርግጥ ቀማሾች ናችሁ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037038.mp3
|
إِنَّكُمْ لَذَائِقُو الْعَذَابِ الْأَلِيمِ |
39 |
ትሠሩትም የነበራችሁትን እንጂ ሌላን አትመነዱም፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037039.mp3
|
وَمَا تُجْزَوْنَ إِلَّا مَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ |
40 |
ግን ምርጥ የሆኑት የአላህ ባሮች (ቅጣትን አይቀምሱም)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037040.mp3
|
إِلَّا عِبَادَ اللَّهِ الْمُخْلَصِينَ |
41 |
እነዚያ ለእነርሱ የታወቀ ሲሳይ አላቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037041.mp3
|
أُوْلَئِكَ لَهُمْ رِزْقٌ مَّعْلُومٌ |
42 |
ፍራፍሬዎች (አሏቸው) እነርሱም የተከበሩ ናቸው፤ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037042.mp3
|
فَوَاكِهُ وَهُم مُّكْرَمُونَ |
43 |
በድሎት ገነቶች ውስጥ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037043.mp3
|
فِي جَنَّاتِ النَّعِيمِ |
44 |
ፊት ለፊት የሚታያዩ ሲሆኑ በአልጋዎች ላይ (ይንፈላሰሳሉ)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037044.mp3
|
عَلَى سُرُرٍ مُّتَقَابِلِينَ |
45 |
ከሚመነጭ ወይን ጠጅ በያዘ ብርጭቆ በእነርሱ ላይ ይዞርባቸዋል፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037045.mp3
|
يُطَافُ عَلَيْهِم بِكَأْسٍ مِن مَّعِينٍ |
46 |
ነጭ ለጠጪዎች ጣፋጭ ከኾነች፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037046.mp3
|
بَيْضَاء لَذَّةٍ لِّلشَّارِبِينَ |
47 |
በእርሷ ውስጥም ምታት የለባትም፡፡ እነርሱም ከእርሷ የሚሰክሩ አይደሉም፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037047.mp3
|
لَا فِيهَا غَوْلٌ وَلَا هُمْ عَنْهَا يُنزَفُونَ |
48 |
እነርሱም ዘንድ ዓይናቸውን (በባሎቻቸው ላይ) አሳጣሪዎች የኾኑ ዓይናማዎች አልሉ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037048.mp3
|
وَعِنْدَهُمْ قَاصِرَاتُ الطَّرْفِ عِينٌ |
49 |
እነርሱ ልክ የተሸፈነ (የሰጎን) ዕንቁላል ይመስላሉ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037049.mp3
|
كَأَنَّهُنَّ بَيْضٌ مَّكْنُونٌ |
50 |
የሚጠያየቁም ሆነው ከፊላቸው ወደ ከፊሉ ይመጣሉ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037050.mp3
|
فَأَقْبَلَ بَعْضُهُمْ عَلَى بَعْضٍ يَتَسَاءلُونَ |
51 |
ከእነርሱ የሆነ ተናጋሪ ይላል «እኔ ጓደኛ ነበረኝ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037051.mp3
|
قَالَ قَائِلٌ مِّنْهُمْ إِنِّي كَانَ لِي قَرِينٌ |
52 |
«በእርግጥ አንተ ከሚያምኑት ነህን? የሚል፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037052.mp3
|
يَقُولُ أَئِنَّكَ لَمِنْ الْمُصَدِّقِينَ |
53 |
«በሞትንና ዐፈር አጥንቶችም በሆን ጊዜ እኛ በእርግጥ እንመረመራለን?» (የሚል)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037053.mp3
|
أَئِذَا مِتْنَا وَكُنَّا تُرَابًا وَعِظَامًا أَئِنَّا لَمَدِينُونَ |
54 |
እናንተ ተመልካቾች ናችሁን? ይላል፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037054.mp3
|
قَالَ هَلْ أَنتُم مُّطَّلِعُونَ |
55 |
ይመለከታልም፤ በገሀነም መካከልም (ጓደኛውን) ያየዋል፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037055.mp3
|
فَاطَّلَعَ فَرَآهُ فِي سَوَاء الْجَحِيمِ |
56 |
ይላል «በአላህ እምላለሁ፤ በእርግጥ ልታጠፋኝ ቀርበህ ነበር፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037056.mp3
|
قَالَ تَاللَّهِ إِنْ كِدتَّ لَتُرْدِينِ |
57 |
«የጌታየም ጸጋ ባልነበረ ኖሮ ወደ እሳት ከሚቀርቡት እሆን ነበር፡፡» |
/content/ayah/audio/hudhaify/037057.mp3
|
وَلَوْلَا نِعْمَةُ رَبِّي لَكُنتُ مِنَ الْمُحْضَرِينَ |
58 |
(የገነት ሰዎች ይላሉ) «እኛ የምንሞት አይደለንምን? |
/content/ayah/audio/hudhaify/037058.mp3
|
أَفَمَا نَحْنُ بِمَيِّتِينَ |
59 |
«የመጀመሪያይቱ መሞታችን ብቻ ስትቀር፡፡ እኛም የምንቅቀጣ አይደለንምን?» (ይላሉ)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037059.mp3
|
إِلَّا مَوْتَتَنَا الْأُولَى وَمَا نَحْنُ بِمُعَذَّبِينَ |
60 |
ይህ (ለገነት ሰዎች የተወሳው) እርሱ በእርግጥ ታላቅ ዕድል ነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037060.mp3
|
إِنَّ هَذَا لَهُوَ الْفَوْزُ الْعَظِيمُ |
61 |
ለዚህ ብጤ ሠሪዎች ይሥሩ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037061.mp3
|
لِمِثْلِ هَذَا فَلْيَعْمَلْ الْعَامِلُونَ |
62 |
በመስተንግዶነት ይህ ይበልጣልን? ወይስ የዘቁም ዛፍ? |
/content/ayah/audio/hudhaify/037062.mp3
|
أَذَلِكَ خَيْرٌ نُّزُلًا أَمْ شَجَرَةُ الزَّقُّومِ |
63 |
እኛ ለበዳዮች ፈተና አድርገናታል፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037063.mp3
|
إِنَّا جَعَلْنَاهَا فِتْنَةً لِّلظَّالِمِينَ |
64 |
እርሷ በገሀነም አዘቅት ውስጥ የምትወጣ ዛፍ ናት፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037064.mp3
|
إِنَّهَا شَجَرَةٌ تَخْرُجُ فِي أَصْلِ الْجَحِيمِ |
65 |
እንቡጧ ልክ የሰይጣናት ራሶች ይመስላል፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037065.mp3
|
طَلْعُهَا كَأَنَّهُ رُؤُوسُ الشَّيَاطِينِ |
66 |
እነርሱም ከእርሷ በይዎች ናቸው፤ ሆዶችንም ከእርሷ ሞይዎች ናቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037066.mp3
|
فَإِنَّهُمْ لَآكِلُونَ مِنْهَا فَمَالِؤُونَ مِنْهَا الْبُطُونَ |
67 |
ከዚያም ለእነርሱ በእርሷ ላይ ከተኳሳ ውሃ ቅልቅል (መጠጥ) አልላቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037067.mp3
|
ثُمَّ إِنَّ لَهُمْ عَلَيْهَا لَشَوْبًا مِّنْ حَمِيمٍ |
68 |
ከዚያም መመለሻቸው ወደ ተጋጋመች እሳት ነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037068.mp3
|
ثُمَّ إِنَّ مَرْجِعَهُمْ لَإِلَى الْجَحِيمِ |
69 |
እነሱ አባቶቻቸውን የተሳሳቱ ሆነው አግኝተዋልና፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037069.mp3
|
إِنَّهُمْ أَلْفَوْا آبَاءهُمْ ضَالِّينَ |
70 |
እነሱም በፈለጎቻቸው ላይ ይገሰግሳሉና፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037070.mp3
|
فَهُمْ عَلَى آثَارِهِمْ يُهْرَعُونَ |
71 |
ከእነርሱ በፊትም የቀድሞዎቹ (ሕዝቦች) አብዛኞቻቸው በእርግጥ ተሳስተዋል፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037071.mp3
|
وَلَقَدْ ضَلَّ قَبْلَهُمْ أَكْثَرُ الْأَوَّلِينَ |
72 |
በውስጣቸውም አስፈራሪዎችን በእርግጥ ልከናል፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037072.mp3
|
وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا فِيهِم مُّنذِرِينَ |
73 |
የተስፈራሪዎቹም መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከት፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037073.mp3
|
فَانظُرْ كَيْفَ كَانَ عَاقِبَةُ الْمُنذَرِينَ |
74 |
ምርጥ የሆኑት የአላህ ባሮች ብቻ ሲቀሩ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037074.mp3
|
إِلَّا عِبَادَ اللَّهِ الْمُخْلَصِينَ |
75 |
ኑሕም በእርግጥ ጠራን፡፡ ጥሪውን ተቀባዮቹም ምንኛ አማርን! |
/content/ayah/audio/hudhaify/037075.mp3
|
وَلَقَدْ نَادَانَا نُوحٌ فَلَنِعْمَ الْمُجِيبُونَ |
76 |
እርሱንም ቤተሰቦቹንም ከከባድ ጭንቅ አዳንን፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037076.mp3
|
وَنَجَّيْنَاهُ وَأَهْلَهُ مِنَ الْكَرْبِ الْعَظِيمِ |
77 |
ዘሮቹንም እነርሱን ብቻ ቀሪዎች አደረግን፤ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037077.mp3
|
وَجَعَلْنَا ذُرِّيَّتَهُ هُمْ الْبَاقِينَ |
78 |
በርሱም ላይ በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ (መልካም ዝናን) ተውን፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037078.mp3
|
وَتَرَكْنَا عَلَيْهِ فِي الْآخِرِينَ |
79 |
«በዓለማት ውስጥ ሰላም በኑሕ ላይ ይኹን፡፡» |
/content/ayah/audio/hudhaify/037079.mp3
|
سَلَامٌ عَلَى نُوحٍ فِي الْعَالَمِينَ |
80 |
እኛ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037080.mp3
|
إِنَّا كَذَلِكَ نَجْزِي الْمُحْسِنِينَ |
81 |
እርሱ ከምእምናን ባሮቻችን ነውና፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037081.mp3
|
إِنَّهُ مِنْ عِبَادِنَا الْمُؤْمِنِينَ |
82 |
ከዚያም ሌሎቹን አሰጠምን፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037082.mp3
|
ثُمَّ أَغْرَقْنَا الْآخَرِينَ |
83 |
ኢብራሂምም በእርግጥ ከተከታዮቹ ነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037083.mp3
|
وَإِنَّ مِن شِيعَتِهِ لَإِبْرَاهِيمَ |
84 |
ወደ ጌታው በቅን ልብ በመጣ ጊዜ (የኾነውን አስታውስ)፡፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037084.mp3
|
إِذْ جَاء رَبَّهُ بِقَلْبٍ سَلِيمٍ |
85 |
«ለአባቱና ለሕዝቦቹ ምንን ትግገዛላችሁ?» ባለ ጊዜ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037085.mp3
|
إِذْ قَالَ لِأَبِيهِ وَقَوْمِهِ مَاذَا تَعْبُدُونَ |
86 |
«ለቅጥፈት ብላችሁ ከአላህ ሌላ አማልክትን ትሻላችሁን? |
/content/ayah/audio/hudhaify/037086.mp3
|
أَئِفْكًا آلِهَةً دُونَ اللَّهِ تُرِيدُونَ |
87 |
«በዓለማትም ጌታ ሃሳባችሁ ምንድን ነው?» አለ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037087.mp3
|
فَمَا ظَنُّكُم بِرَبِّ الْعَالَمِينَ |
88 |
በከዋክብትም መመልከትን ተመለከተ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037088.mp3
|
فَنَظَرَ نَظْرَةً فِي النُّجُومِ |
89 |
«እኔ በሽተኛ ነኝም» አለ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037089.mp3
|
فَقَالَ إِنِّي سَقِيمٌ |
90 |
ከእርሱም የሸሹ ሆነው ኼዱ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037090.mp3
|
فَتَوَلَّوْا عَنْهُ مُدْبِرِينَ |
91 |
ወደ አማልክቶቻቸውም ተዘነበለ፡፡ አለም፡- «አትበሉምን?» |
/content/ayah/audio/hudhaify/037091.mp3
|
فَرَاغَ إِلَى آلِهَتِهِمْ فَقَالَ أَلَا تَأْكُلُونَ |
92 |
«የማትናገሩት ለናንተ ምን አላችሁ?» |
/content/ayah/audio/hudhaify/037092.mp3
|
مَا لَكُمْ لَا تَنطِقُونَ |
93 |
በኀይል የሚመታቸውም ሆኖ በእነርሱ ላይ በድብቅ ተዘነበለ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037093.mp3
|
فَرَاغَ عَلَيْهِمْ ضَرْبًا بِالْيَمِينِ |
94 |
ወደእርሱም (ሰዎቹ) እየሮጡ መጡ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037094.mp3
|
فَأَقْبَلُوا إِلَيْهِ يَزِفُّونَ |
95 |
አላቸው «የምትጠርቡትን ትግገዛላችሁን?» |
/content/ayah/audio/hudhaify/037095.mp3
|
قَالَ أَتَعْبُدُونَ مَا تَنْحِتُونَ |
96 |
«አላህ እናንተንም የምትሠሩትንም የፈጠረ ሲኾን፡፡» |
/content/ayah/audio/hudhaify/037096.mp3
|
وَاللَّهُ خَلَقَكُمْ وَمَا تَعْمَلُونَ |
97 |
«ለእርሱም ግንብን ገንቡ በእሳት ነበልባል ውስጥ ጣሉትም» አሉ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037097.mp3
|
قَالُوا ابْنُوا لَهُ بُنْيَانًا فَأَلْقُوهُ فِي الْجَحِيمِ |
98 |
በእርሱም ተንኮልን አሰቡ፡፡ ዝቅተኞችም አደረግናቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037098.mp3
|
فَأَرَادُوا بِهِ كَيْدًا فَجَعَلْنَاهُمُ الْأَسْفَلِينَ |
99 |
አለም «እኔ ወደ ጌታዬ ኼያጅ ነኝ፡፡ በእርግጥ ይመራኛልና፡፡» |
/content/ayah/audio/hudhaify/037099.mp3
|
وَقَالَ إِنِّي ذَاهِبٌ إِلَى رَبِّي سَيَهْدِينِ |
100 |
ጌታዬ ሆይ! ከመልካሞቹ የሆነን (ልጅ) ስጠኝ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037100.mp3
|
رَبِّ هَبْ لِي مِنَ الصَّالِحِينَ |
101 |
ታጋሽ በሆነ ወጣት ልጅም አበሰርነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037101.mp3
|
فَبَشَّرْنَاهُ بِغُلَامٍ حَلِيمٍ |
102 |
ከእርሱ ጋርም ለሥራ በደረሰ ጊዜ «ልጄ ሆይ! እኔ በሕልሜ እኔ የማርድህ ሆኜ አያለሁ፡፡ ተመልከትም፤ ምን ታያለህ?» አለው፡፡ «አባቴ ሆይ! የታዘዝከውን ሥራ፡፡ አላህ ቢሻ ከታጋሾቹ ሆኜ ታገኘኛለህ» አለ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037102.mp3
|
فَلَمَّا بَلَغَ مَعَهُ السَّعْيَ قَالَ يَا بُنَيَّ إِنِّي أَرَى فِي الْمَنَامِ أَنِّي أَذْبَحُكَ فَانظُرْ مَاذَا تَرَى قَالَ يَا أَبَتِ افْعَلْ مَا تُؤْمَرُ سَتَجِدُنِي إِن شَاء اللَّهُ مِنَ الصَّابِرِينَ |
103 |
ሁለቱም ትዕዛዙን በተቀበሉና በግንባሩም ጎን ላይ በጣለው ጊዜ (የሆነው ሆነ)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037103.mp3
|
فَلَمَّا أَسْلَمَا وَتَلَّهُ لِلْجَبِينِ |
104 |
ጠራነውም፤ (አልነው) «ኢብራሂም ሆይ! |
/content/ayah/audio/hudhaify/037104.mp3
|
وَنَادَيْنَاهُ أَنْ يَا إِبْرَاهِيمُ |
105 |
ራእይቱን በእውነት አረጋገጥክ፡፡» እኛ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037105.mp3
|
قَدْ صَدَّقْتَ الرُّؤْيَا إِنَّا كَذَلِكَ نَجْزِي الْمُحْسِنِينَ |
106 |
ይህ እርሱ በእውነት ግልጽ ፈተና ነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037106.mp3
|
إِنَّ هَذَا لَهُوَ الْبَلَاء الْمُبِينُ |
107 |
በታላቅ ዕርድም (መስዋዕት) ተቤዠነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037107.mp3
|
وَفَدَيْنَاهُ بِذِبْحٍ عَظِيمٍ |
108 |
በእርሱም ላይ በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ መልካም ዝናን አስቀረንለት፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037108.mp3
|
وَتَرَكْنَا عَلَيْهِ فِي الْآخِرِينَ |
109 |
ሰላም በኢብራሂም ላይ ይሁን፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037109.mp3
|
سَلَامٌ عَلَى إِبْرَاهِيمَ |
110 |
እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን ሁሉ እንመነዳለን፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037110.mp3
|
كَذَلِكَ نَجْزِي الْمُحْسِنِينَ |
111 |
እርሱ በእርግጥ ካመኑት ባሮቻችን ነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037111.mp3
|
إِنَّهُ مِنْ عِبَادِنَا الْمُؤْمِنِينَ |
112 |
በኢስሐቅም አበሰርነው፡፡ ከመልካሞቹ የሆነ ነቢይ ሲሆን፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037112.mp3
|
وَبَشَّرْنَاهُ بِإِسْحَاقَ نَبِيًّا مِّنَ الصَّالِحِينَ |
113 |
በእርሱና በኢስሐቅ ላይም ባረክን፡፡ ከሁለቱም ዘሮች በጎ ሠሪ አልለ፡፡ ለነፍሱ ግልጽ በዳይም አለ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037113.mp3
|
وَبَارَكْنَا عَلَيْهِ وَعَلَى إِسْحَاقَ وَمِن ذُرِّيَّتِهِمَا مُحْسِنٌ وَظَالِمٌ لِّنَفْسِهِ مُبِينٌ |
114 |
በሙሳና በሃሩን ላይም በእርግጥ ለገስን፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037114.mp3
|
وَلَقَدْ مَنَنَّا عَلَى مُوسَى وَهَارُونَ |
115 |
እነርሱንም ሕዝቦቻቸውንም ከታላቅ ጭንቅ አዳንን፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037115.mp3
|
وَنَجَّيْنَاهُمَا وَقَوْمَهُمَا مِنَ الْكَرْبِ الْعَظِيمِ |
116 |
ረዳናቸውም፡፡ እነርሱም አሸናፊዎች ነበሩ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037116.mp3
|
وَنَصَرْنَاهُمْ فَكَانُوا هُمُ الْغَالِبِينَ |
117 |
በጣም የተብራራውንም መጽሐፍ ሰጠናቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037117.mp3
|
وَآتَيْنَاهُمَا الْكِتَابَ الْمُسْتَبِينَ |
118 |
ቀጥተኛውንም መንገድ መራናቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037118.mp3
|
وَهَدَيْنَاهُمَا الصِّرَاطَ الْمُسْتَقِيمَ |
119 |
በሁለቱም ላይ በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ መልካም ዝናን ተውንላቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037119.mp3
|
وَتَرَكْنَا عَلَيْهِمَا فِي الْآخِرِينَ |
120 |
ሰላም በሙሳና በሃሩን ላይ ይሁን፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037120.mp3
|
سَلَامٌ عَلَى مُوسَى وَهَارُونَ |
121 |
እኛ እንደዚሁ በጎ አድራጊዎችን ሁሉ እንመነዳለን፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037121.mp3
|
إِنَّا كَذَلِكَ نَجْزِي الْمُحْسِنِينَ |
122 |
ሁለቱም በእርግጥ ከአመኑት ባሮቻችን ናቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037122.mp3
|
إِنَّهُمَا مِنْ عِبَادِنَا الْمُؤْمِنِينَ |
123 |
ኢልያስም በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037123.mp3
|
وَإِنَّ إِلْيَاسَ لَمِنْ الْمُرْسَلِينَ |
124 |
ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ (አስታውስ)፤ አላህን አትፈሩምን? |
/content/ayah/audio/hudhaify/037124.mp3
|
إِذْ قَالَ لِقَوْمِهِ أَلَا تَتَّقُونَ |
125 |
በዕልን ትገዛላችሁን? ከሰዓሊዎቹ ሁሉ ይበልጥ በጣም አሳማሪ የሆነውንም አምላክ ትተዋላችሁን? |
/content/ayah/audio/hudhaify/037125.mp3
|
أَتَدْعُونَ بَعْلًا وَتَذَرُونَ أَحْسَنَ الْخَالِقِينَ |
126 |
አላህን ጌታችሁንና የቀድሞዎቹ አባቶቻችሁን ጌታ (ትተዋላችሁን)? |
/content/ayah/audio/hudhaify/037126.mp3
|
وَاللَّهَ رَبَّكُمْ وَرَبَّ آبَائِكُمُ الْأَوَّلِينَ |
127 |
አስተባበሉትም፡፡ ስለዚህ እነርሱ (ለቅጣት) የሚጣዱ ናቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037127.mp3
|
فَكَذَّبُوهُ فَإِنَّهُمْ لَمُحْضَرُونَ |
128 |
ንጹሕ የተደረጉት የአላህ ባሮች ብቻ ሲቀሩ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037128.mp3
|
إِلَّا عِبَادَ اللَّهِ الْمُخْلَصِينَ |
129 |
በእርሱ ላይም በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ መልካም ዝናን ተውንለት፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037129.mp3
|
وَتَرَكْنَا عَلَيْهِ فِي الْآخِرِينَ |
130 |
ሰላም በኢልያሲን ላይ ይሁን፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037130.mp3
|
سَلَامٌ عَلَى إِلْ يَاسِينَ |
131 |
እኛ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037131.mp3
|
إِنَّا كَذَلِكَ نَجْزِي الْمُحْسِنِينَ |
132 |
እርሱ በእርግጥ ከምእመናን ባሮቻችን ነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037132.mp3
|
إِنَّهُ مِنْ عِبَادِنَا الْمُؤْمِنِينَ |
133 |
ሉጥም በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037133.mp3
|
وَإِنَّ لُوطًا لَّمِنَ الْمُرْسَلِينَ |
134 |
እርሱንና ቤተሰቦቹን ሁሉንም በአዳንናቸው ጊዜ (አስታውስ)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037134.mp3
|
إِذْ نَجَّيْنَاهُ وَأَهْلَهُ أَجْمَعِينَ |
135 |
(በቅጣቱ ውስጥ) ከቀሪዎቹ የሆነችው አሮጊት ብቻ ስትቀር፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037135.mp3
|
إِلَّا عَجُوزًا فِي الْغَابِرِينَ |
136 |
ከዚያም ሌሎቹን አጠፋን፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037136.mp3
|
ثُمَّ دَمَّرْنَا الْآخَرِينَ |
137 |
እናንተም ያነጋችሁ ስትሆኑ በእነርሱ (መኖሪያዎች) ላይ (በቀን) ታልፋላችሁ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037137.mp3
|
وَإِنَّكُمْ لَتَمُرُّونَ عَلَيْهِم مُّصْبِحِينَ |
138 |
በሌሊትም (ታልፋላችሁ)፤ ልብም አታደርጉምን? |
/content/ayah/audio/hudhaify/037138.mp3
|
وَبِاللَّيْلِ أَفَلَا تَعْقِلُونَ |
139 |
ዩኑስም በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037139.mp3
|
وَإِنَّ يُونُسَ لَمِنَ الْمُرْسَلِينَ |
140 |
ወደ ተመላው መርከብ በኮበለለ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037140.mp3
|
إِذْ أَبَقَ إِلَى الْفُلْكِ الْمَشْحُونِ |
141 |
ዕጣም ተጣጣለ፡፡ ከተሸነፉትም ሆነ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037141.mp3
|
فَسَاهَمَ فَكَانَ مِنْ الْمُدْحَضِينَ |
142 |
እርሱም ተወቃሽ ሲሆን ዐሳው ዋጠው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037142.mp3
|
فَالْتَقَمَهُ الْحُوتُ وَهُوَ مُلِيمٌ |
143 |
እርሱ ለጌታው ከአወዳሾቹ ባልሆነም ኖሮ፤ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037143.mp3
|
فَلَوْلَا أَنَّهُ كَانَ مِنْ الْمُسَبِّحِينَ |
144 |
እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ በሆዱ ውስጥ በቆየ ነበር፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037144.mp3
|
لَلَبِثَ فِي بَطْنِهِ إِلَى يَوْمِ يُبْعَثُونَ |
145 |
እርሱ በሽተኛ ሆኖ በቃይ በሌለው (በባሕር) ዳርቻ ላይ ጣልነውም፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037145.mp3
|
فَنَبَذْنَاهُ بِالْعَرَاء وَهُوَ سَقِيمٌ |
146 |
በእርሱም ላይ (በአጠገቡ) ከቅል የሆነችን ዛፍ አበቀልን፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037146.mp3
|
وَأَنبَتْنَا عَلَيْهِ شَجَرَةً مِّن يَقْطِينٍ |
147 |
ወደ መቶ ሺሕ ሰዎችም (ዳግመኛ) ላክነው፡፡ ከቶውንም ይጨምራሉ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037147.mp3
|
وَأَرْسَلْنَاهُ إِلَى مِئَةِ أَلْفٍ أَوْ يَزِيدُونَ |
148 |
አመኑም፡፡ እስከ ጊዜ ድረስም አጣቀምናቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037148.mp3
|
فَآمَنُوا فَمَتَّعْنَاهُمْ إِلَى حِينٍ |
149 |
(የመካን ሰዎች) ጠይቃቸውም፡፡ «ለጌታህ ሴቶች ልጆች ለእነርሱም ወንዶች ልጆች ይኖራልን?» |
/content/ayah/audio/hudhaify/037149.mp3
|
فَاسْتَفْتِهِمْ أَلِرَبِّكَ الْبَنَاتُ وَلَهُمُ الْبَنُونَ |
150 |
ወይስ እኛ እነርሱ የተጣዱ ሆነው መላእክትን ሴቶች አድርገን ፈጠርን? |
/content/ayah/audio/hudhaify/037150.mp3
|
أَمْ خَلَقْنَا الْمَلَائِكَةَ إِنَاثًا وَهُمْ شَاهِدُونَ |
151 |
ንቁ! እነርሱ ከቅጥፈታቸው (የተነሳ) ይላሉ፡- |
/content/ayah/audio/hudhaify/037151.mp3
|
أَلَا إِنَّهُم مِّنْ إِفْكِهِمْ لَيَقُولُونَ |
152 |
«አላህ (መላእክትን) ወለደ፡፡» እነርሱም በእርግጥ ውሸታሞች ናቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037152.mp3
|
وَلَدَ اللَّهُ وَإِنَّهُمْ لَكَاذِبُونَ |
153 |
በወንዶች ልጆች ላይ ይልቅ ሴቶችን ልጆች መረጥን? |
/content/ayah/audio/hudhaify/037153.mp3
|
أَصْطَفَى الْبَنَاتِ عَلَى الْبَنِينَ |
154 |
ለእናንተ ምን (አስረጅ) አላችሁ? እንዴት ትፈርዳላችሁ! |
/content/ayah/audio/hudhaify/037154.mp3
|
مَا لَكُمْ كَيْفَ تَحْكُمُونَ |
155 |
አትገነዘቡምን? |
/content/ayah/audio/hudhaify/037155.mp3
|
أَفَلَا تَذَكَّرُونَ |
156 |
ወይስ ለእናንተ ግልጽ አስረጅ አላችሁን? |
/content/ayah/audio/hudhaify/037156.mp3
|
أَمْ لَكُمْ سُلْطَانٌ مُّبِينٌ |
157 |
«እውነተኞች እንደ ሆናችሁ መጽሐፋችሁን አምጡ» (በላቸው)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037157.mp3
|
فَأْتُوا بِكِتَابِكُمْ إِن كُنتُمْ صَادِقِينَ |
158 |
በአላህና በአጋንንት መካከልም ዝምድናን አደረጉ፡፡ አጋንንትም እነርሱ (ይህን ባዮች በእሳት) የሚጣዱ መሆናቸውን በእርግጥ ዐውቀዋል፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037158.mp3
|
وَجَعَلُوا بَيْنَهُ وَبَيْنَ الْجِنَّةِ نَسَبًا وَلَقَدْ عَلِمَتِ الْجِنَّةُ إِنَّهُمْ لَمُحْضَرُونَ |
159 |
አላህ ከሚመጥኑት ሁሉ ጠራ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037159.mp3
|
سُبْحَانَ اللَّهِ عَمَّا يَصِفُونَ |
160 |
ግን የተመረጡት የአላህ ባሮች (በአላህ ላይ አይዋሹም)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037160.mp3
|
إِلَّا عِبَادَ اللَّهِ الْمُخْلَصِينَ |
161 |
እናንተም የምትገዟቸውም ሁሉ፤ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037161.mp3
|
فَإِنَّكُمْ وَمَا تَعْبُدُونَ |
162 |
በእርሱ (በአላህ) ላይ አንድንም አጥማሚዎች አይደላችሁም፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037162.mp3
|
مَا أَنتُمْ عَلَيْهِ بِفَاتِنِينَ |
163 |
ያንን እርሱ ገሀነምን ገቢ የሆነውን ሰው ቢሆን እንጅ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037163.mp3
|
إِلَّا مَنْ هُوَ صَالِ الْجَحِيمِ |
164 |
(ጂብሪል አለ) ከእኛም አንድም የለም፤ ለእርሱ የታወቀ ደረጃ ያለው ቢሆን እንጅ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037164.mp3
|
وَمَا مِنَّا إِلَّا لَهُ مَقَامٌ مَّعْلُومٌ |
165 |
እኛም (ጌታን ለመግገዛት) ተሰላፊዎቹ እኛ ነን፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037165.mp3
|
وَإِنَّا لَنَحْنُ الصَّافُّونَ |
166 |
እኛም (አላህን) አጥሪዎቹ እኛ ነን፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037166.mp3
|
وَإِنَّا لَنَحْنُ الْمُسَبِّحُونَ |
167 |
እነርሱም (ከሓዲዎቹ) በእርግጥ ይሉ ነበሩ፡- |
/content/ayah/audio/hudhaify/037167.mp3
|
وَإِنْ كَانُوا لَيَقُولُونَ |
168 |
«ከቀድሞዎቹ (መጻሕፍት) ገሳጭ መጽሐፍ እኛ ዘንድ በነበረን ኖሮ፤ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037168.mp3
|
لَوْ أَنَّ عِندَنَا ذِكْرًا مِّنْ الْأَوَّلِينَ |
169 |
«የአላህ ምርጦች ባሮች በሆን ነበር፡፡» |
/content/ayah/audio/hudhaify/037169.mp3
|
لَكُنَّا عِبَادَ اللَّهِ الْمُخْلَصِينَ |
170 |
ግን (ቁርኣኑ በመጣላቸው ጊዜ) በእርሱ ካዱ፡፡ ወደፊትም በእርግጥ ያውቃሉ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037170.mp3
|
فَكَفَرُوا بِهِ فَسَوْفَ يَعْلَمُونَ |
171 |
(የእርዳታ) ቃላችንም መልክተኞች ለሆኑት ባሮቻችን በእውነት አልፋለች፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037171.mp3
|
وَلَقَدْ سَبَقَتْ كَلِمَتُنَا لِعِبَادِنَا الْمُرْسَلِينَ |
172 |
እነርሱ ተረጂዎቹ እነርሱ ናቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037172.mp3
|
إِنَّهُمْ لَهُمُ الْمَنصُورُونَ |
173 |
ሰራዊቶቻችንም በእርግጥ አሸናፊዎቹ እነርሱ ናቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037173.mp3
|
وَإِنَّ جُندَنَا لَهُمُ الْغَالِبُونَ |
174 |
ከእነርሱም (ከመካ ከሓዲዎች) እስከ ጥቂት ጊዜ ድረስ ዙር (ተዋቸው)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037174.mp3
|
فَتَوَلَّ عَنْهُمْ حَتَّى حِينٍ |
175 |
እያቸውም ወደፊትም (የሚደርስባቸውን) ያያሉ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037175.mp3
|
وَأَبْصِرْهُمْ فَسَوْفَ يُبْصِرُونَ |
176 |
በቅጣታችንም ያቻኩላሉን? |
/content/ayah/audio/hudhaify/037176.mp3
|
أَفَبِعَذَابِنَا يَسْتَعْجِلُونَ |
177 |
በቀያቸውም በወረደ ጊዜ የተስፈራሪዎቹ ንጋት ከፋ! |
/content/ayah/audio/hudhaify/037177.mp3
|
فَإِذَا نَزَلَ بِسَاحَتِهِمْ فَسَاء صَبَاحُ الْمُنذَرِينَ |
178 |
እነርሱንም እስከ (ጥቂት) ጊዜ ድረስ ተዋቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037178.mp3
|
وَتَوَلَّ عَنْهُمْ حَتَّى حِينٍ |
179 |
ተመልከትም በእርግጥም ያያሉ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037179.mp3
|
وَأَبْصِرْ فَسَوْفَ يُبْصِرُونَ |
180 |
የማሸነፍ ጌታ የሆነው ጌታህ ከሚሉት ሁሉ ጠራ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037180.mp3
|
سُبْحَانَ رَبِّكَ رَبِّ الْعِزَّةِ عَمَّا يَصِفُونَ |
181 |
በመልክተኞቹም ላይ ሰላም ይኹኑ፤ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037181.mp3
|
وَسَلَامٌ عَلَى الْمُرْسَلِينَ |
182 |
ምስጋናም ለዓለማት ጌታ ለአላህ ይሁን፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/037182.mp3
|
وَالْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ |