1 |
አ.ለ.ረ (አሊፍ ላም ራ) ይህች (አናቅጽ) ከመጽሐፉ አንቀጾችና ገላጭ ከኾነው ቁርኣን ናት፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015001.mp3
|
الَرَ تِلْكَ آيَاتُ الْكِتَابِ وَقُرْآنٍ مُّبِينٍ |
2 |
እነዚያ የካዱት (በትንሣኤ ቀን) ሙስሊሞች በኾኑ ኖሩ በብዛት ይመኛሉ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015002.mp3
|
رُّبَمَا يَوَدُّ الَّذِينَ كَفَرُواْ لَوْ كَانُواْ مُسْلِمِينَ |
3 |
ተዋቸው ይብሉ፤ ይጠቀሙም፡፡ ተስፋም ያዘናጋቸው፡፡ በእርግጥም (መጥፎ ፍጻሜያቸውን) ያውቃሉ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015003.mp3
|
ذَرْهُمْ يَأْكُلُواْ وَيَتَمَتَّعُواْ وَيُلْهِهِمُ الأَمَلُ فَسَوْفَ يَعْلَمُونَ |
4 |
ማንኛይቱንም ከተማ ለእርሷ የተወሰነ መጽሐፍ (ጊዜያት) ያላት ኾና እንጂ አላጠፋንም፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015004.mp3
|
وَمَا أَهْلَكْنَا مِن قَرْيَةٍ إِلاَّ وَلَهَا كِتَابٌ مَّعْلُومٌ |
5 |
ማንኛይቱም ሕዝብ ጊዜዋን ምንም አትቀድምም፡፡ (ከእርሱ) አይቆዩምም፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015005.mp3
|
مَّا تَسْبِقُ مِنْ أُمَّةٍ أَجَلَهَا وَمَا يَسْتَأْخِرُونَ |
6 |
«አንተ ያ በእርሱ ላይ ቁርኣን የተወረደለት ሆይ! አንተ በእርግጥ ዕብድ ነህ» አሉም፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015006.mp3
|
وَقَالُواْ يَا أَيُّهَا الَّذِي نُزِّلَ عَلَيْهِ الذِّكْرُ إِنَّكَ لَمَجْنُونٌ |
7 |
«ከእውነተኞቹ እንደ ኾንክ በመላእክት (መስካሪ) ለምን አትመጣንም» (አሉ)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015007.mp3
|
لَّوْ مَا تَأْتِينَا بِالْمَلائِكَةِ إِن كُنتَ مِنَ الصَّادِقِينَ |
8 |
መላእክትን በእውነት (በቅጣት) እንጂ አናወርድም፡፡ ያን ጊዜም የሚቆዩ አይደሉም፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015008.mp3
|
مَا نُنَزِّلُ الْمَلائِكَةَ إِلاَّ بِالحَقِّ وَمَا كَانُواْ إِذًا مُّنظَرِينَ |
9 |
እኛ ቁርኣንን እኛው አወረድነው፡፡ እኛም ለእርሱ ጠባቂዎቹ ነን፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015009.mp3
|
إِنَّا نَحْنُ نَزَّلْنَا الذِّكْرَ وَإِنَّا لَهُ لَحَافِظُونَ |
10 |
ከአንተም በፊት በነበሩት በመጀመሪያዎቹ ሕዝቦች ውስጥ (መልክተኞችን) በእርግጥ ልከናል፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015010.mp3
|
وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ فِي شِيَعِ الأَوَّلِينَ |
11 |
ማንኛውም መልእክተኛ በእርሱ የሚያላግጡበት ኾነው እንጅ አይመጣቸውም ነበር፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015011.mp3
|
وَمَا يَأْتِيهِم مِّن رَّسُولٍ إِلاَّ كَانُواْ بِهِ يَسْتَهْزِئُونَ |
12 |
እንደዚሁ (ማስተባበልን) በአመጸኞቹ ልቦች ውስጥ እናገባዋለን፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015012.mp3
|
كَذَلِكَ نَسْلُكُهُ فِي قُلُوبِ الْمُجْرِمِينَ |
13 |
በእርሱ አያምኑበትም፡፡ የቀድሞዎቹም ድርጊት በእርግጥ አልፋለች፤ (እንደጠፉ ይጠፋሉ)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015013.mp3
|
لاَ يُؤْمِنُونَ بِهِ وَقَدْ خَلَتْ سُنَّةُ الأَوَّلِينَ |
14 |
በእነርሱም ላይ ከሰማይ ደጃፍን በከፈትንላቸውና በእርሱ ሲወጡ በዋሉ ኖሮ፤ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015014.mp3
|
وَلَوْ فَتَحْنَا عَلَيْهِم بَابًا مِّنَ السَّمَاء فَظَلُّواْ فِيهِ يَعْرُجُونَ |
15 |
«የተዘጉት ዓይኖቻችን ናቸው፡፡ እንዲያውም እኛ የተደገመብን ሰዎች ነን» ባሉ ነበር፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015015.mp3
|
لَقَالُواْ إِنَّمَا سُكِّرَتْ أَبْصَارُنَا بَلْ نَحْنُ قَوْمٌ مَّسْحُورُونَ |
16 |
በሰማይም ላይ ቡርጆችን በእርግጥ አድርገናል፡፡ ለተመልካቾችም (በከዋክብት) አጊጠናታል፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015016.mp3
|
وَلَقَدْ جَعَلْنَا فِي السَّمَاء بُرُوجًا وَزَيَّنَّاهَا لِلنَّاظِرِينَ |
17 |
ከተባረረ ሰይጣንም ሁሉ ጠብቀናታል፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015017.mp3
|
وَحَفِظْنَاهَا مِن كُلِّ شَيْطَانٍ رَّجِيمٍ |
18 |
ግን (ወሬ) መስማትን የሚሰርቅ ወዲየውኑ አብሪ ችቦ ይከተለዋል፡፡ (ያቃጥለዋል)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015018.mp3
|
إِلاَّ مَنِ اسْتَرَقَ السَّمْعَ فَأَتْبَعَهُ شِهَابٌ مُّبِينٌ |
19 |
ምድርንም ዘረጋናት፡፡ በውስጧም ኮረብታዎችን ጣልናባት፡፡ በውስጧም (የተለካን) በቃይ ሁሉ አበቀልንባት፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015019.mp3
|
وَالأَرْضَ مَدَدْنَاهَا وَأَلْقَيْنَا فِيهَا رَوَاسِيَ وَأَنبَتْنَا فِيهَا مِن كُلِّ شَيْءٍ مَّوْزُونٍ |
20 |
በእርሷም ውስጥ ለእናንተ መኖሪያዎችንና ለእርሱ መጋቢዎቹ ያልኾናችሁትንም (እንስሳትን) አደረግንላችሁ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015020.mp3
|
وَجَعَلْنَا لَكُمْ فِيهَا مَعَايِشَ وَمَن لَّسْتُمْ لَهُ بِرَازِقِينَ |
21 |
መካዚኖቹም (መክፈቻቸው) እኛ ዘንድ ያልሆነ ምንም ነገር የለም፡፡ በተወሰነም ልክ እንጂ አናወርደውም፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015021.mp3
|
وَإِن مِّن شَيْءٍ إِلاَّ عِندَنَا خَزَائِنُهُ وَمَا نُنَزِّلُهُ إِلاَّ بِقَدَرٍ مَّعْلُومٍ |
22 |
ነፋሶችንም (ደመናን) ተሸካሚዎች አድርገን ላክን፡፡ ከሰማይም (ከደመና) ዝናብን አወረድን፡፡ እርሱንም አጠጣናችሁ፡፡ እናንተም ለእርሱ አድላቢዎች አይደላችሁም፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015022.mp3
|
لَوَاقِحَ فَأَنزَلْنَا مِنَ السَّمَاء مَاء فَأَسْقَيْنَاكُمُوهُ وَمَا أَنتُمْ لَهُ بِخَازِنِينَ |
23 |
እኛም ሕያው የምናደርግና የምንገድል እኛው ብቻ ነን፡፡ እኛም (ፍጡርን ሁሉ ) የምንወርስ (ቀሪ) ነን፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015023.mp3
|
وَإنَّا لَنَحْنُ نُحْيِي وَنُمِيتُ وَنَحْنُ الْوَارِثُونَ |
24 |
ከእናንተም ተቀዳሚዎቹን በእርግጥ ዐውቀናል፡፡ ወደ ኋላም ቀሪዎቹን በእርግጥ ዐውቀናል፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015024.mp3
|
وَلَقَدْ عَلِمْنَا الْمُسْتَقْدِمِينَ مِنكُمْ وَلَقَدْ عَلِمْنَا الْمُسْتَأْخِرِينَ |
25 |
ጌታህም እርሱ ይሰበስባችኋል፡፡ እርሱ ጥበበኛ ዐዋቂ ነውና፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015025.mp3
|
وَإِنَّ رَبَّكَ هُوَ يَحْشُرُهُمْ إِنَّهُ حَكِيمٌ عَلِيمٌ |
26 |
ሰውንም ከሚቅጨለጨል ሸክላ ከሚገማ ጥቁር ጭቃ በእርግጥ ፈጠርነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015026.mp3
|
وَلَقَدْ خَلَقْنَا الإِنسَانَ مِن صَلْصَالٍ مِّنْ حَمَإٍ مَّسْنُونٍ |
27 |
ጃንንም (ከሰው) በፊት ከእሳት ነበልባል ፈጠርነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015027.mp3
|
وَالْجَآنَّ خَلَقْنَاهُ مِن قَبْلُ مِن نَّارِ السَّمُومِ |
28 |
ጌታህም ለመላእክት ባለጊዜ (አስታውስ)፡፡ እኔ ሰውን ከሚቅጨለጨል ሸክላ ከሚገማ ጭቃ እፈጥራለሁ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015028.mp3
|
وَإِذْ قَالَ رَبُّكَ لِلْمَلاَئِكَةِ إِنِّي خَالِقٌ بَشَرًا مِّن صَلْصَالٍ مِّنْ حَمَإٍ مَّسْنُونٍ |
29 |
(ፍጥረቱን) ባስተካከልኩትና በውስጡ ከመንፈሴ በነፋሁበትም ጊዜ ለእርሱ ሰጋጆች ኾናችሁ ውደቁ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015029.mp3
|
فَإِذَا سَوَّيْتُهُ وَنَفَخْتُ فِيهِ مِن رُّوحِي فَقَعُواْ لَهُ سَاجِدِينَ |
30 |
መላእክትም መላውም ተሰብስበው ሰገዱ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015030.mp3
|
فَسَجَدَ الْمَلآئِكَةُ كُلُّهُمْ أَجْمَعُونَ |
31 |
ኢብሊስ (ዲያብሎስ) ብቻ ሲቀር፡፡ ከሰጋጆቹ ጋር ከመኾን እንቢ አለ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015031.mp3
|
إِلاَّ إِبْلِيسَ أَبَى أَن يَكُونَ مَعَ السَّاجِدِينَ |
32 |
(አላህም) «ኢብሊስ ሆይ! ከሰጋጆቹ ጋር የማትኾን ላንተ ምን ምክንያት አለህ» አለው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015032.mp3
|
قَالَ يَا إِبْلِيسُ مَا لَكَ أَلاَّ تَكُونَ مَعَ السَّاجِدِينَ |
33 |
«ከሚቅጨለጨል ሸክላ ከግም ጭቃ ለፈጠርከው ሰው ልሰግድ አይገባኝም» አለ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015033.mp3
|
قَالَ لَمْ أَكُن لِّأَسْجُدَ لِبَشَرٍ خَلَقْتَهُ مِن صَلْصَالٍ مِّنْ حَمَإٍ مَّسْنُونٍ |
34 |
(አላህ) አለው «ከርሷም ውጣ፡፡ አንተ የተባረርክ እርጉም ነህና፡፡» |
/content/ayah/audio/hudhaify/015034.mp3
|
قَالَ فَاخْرُجْ مِنْهَا فَإِنَّكَ رَجِيمٌ |
35 |
«ባንተ ላይም እስከ ፍርዱ ቀን ድረስ እርግማን አለብህ፡፡» |
/content/ayah/audio/hudhaify/015035.mp3
|
وَإِنَّ عَلَيْكَ اللَّعْنَةَ إِلَى يَوْمِ الدِّينِ |
36 |
«ጌታዬ ሆይ! እንግዲውያስ (ሰዎች) እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ አቆየኝ» አለ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015036.mp3
|
قَالَ رَبِّ فَأَنظِرْنِي إِلَى يَوْمِ يُبْعَثُونَ |
37 |
(አላህም) አለ «አንተ ከሚቆዩት ነህ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015037.mp3
|
قَالَ فَإِنَّكَ مِنَ الْمُنظَرِينَ |
38 |
«እስከታወቀው ወቅት ቀን ድረስ፡፡» |
/content/ayah/audio/hudhaify/015038.mp3
|
إِلَى يَومِ الْوَقْتِ الْمَعْلُومِ |
39 |
(ኢብሊስ) አለ «ጌታዬ ሆይ! እኔን በማጥመምህ ይኹንብኝ ለነርሱ በምድር ላይ (ኀጢአትን) እሸልምላቸዋለሁ፡፡ ሁሉንም አጠማቸዋለሁም፡፡» |
/content/ayah/audio/hudhaify/015039.mp3
|
قَالَ رَبِّ بِمَا أَغْوَيْتَنِي لأُزَيِّنَنَّ لَهُمْ فِي الأَرْضِ وَلأُغْوِيَنَّهُمْ أَجْمَعِينَ |
40 |
«ከነርሱ ፍጹሞቹ ባሮችህ ብቻ ሲቀሩ፡፡» |
/content/ayah/audio/hudhaify/015040.mp3
|
إِلاَّ عِبَادَكَ مِنْهُمُ الْمُخْلَصِينَ |
41 |
(አላህም) አለ «ይህ በእኔ ላይ (መጠበቁ የተገባ) ቀጥተኛ መንገድ ነው፡፡» |
/content/ayah/audio/hudhaify/015041.mp3
|
قَالَ هَذَا صِرَاطٌ عَلَيَّ مُسْتَقِيمٌ |
42 |
«እነሆ ባሮቼ በእነሱ ላይ ላንተ ስልጣን የለህም፡፡ ከጠማሞቹ የተከተለህ ሰው ብቻ ሲቀር፡፡» |
/content/ayah/audio/hudhaify/015042.mp3
|
إِنَّ عِبَادِي لَيْسَ لَكَ عَلَيْهِمْ سُلْطَانٌ إِلاَّ مَنِ اتَّبَعَكَ مِنَ الْغَاوِينَ |
43 |
«ገሀነምም (ለርሱና ለተከተሉት) ለመላውም በእርግጥ ቀጠሯቸው ናት፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015043.mp3
|
وَإِنَّ جَهَنَّمَ لَمَوْعِدُهُمْ أَجْمَعِينَ |
44 |
«ለእርሷ ሰባት ደጃፎች አሏት፡፡ ለየደጀፉም ሁሉ ከእነሱ የተከፈለ ፋንታ አለ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015044.mp3
|
لَهَا سَبْعَةُ أَبْوَابٍ لِّكُلِّ بَابٍ مِّنْهُمْ جُزْءٌ مَّقْسُومٌ |
45 |
«እነዚያ (ከኀጢአት) የተጠነቀቁት በአትክልቶችና በምንጮች ውስጥ ናቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015045.mp3
|
إِنَّ الْمُتَّقِينَ فِي جَنَّاتٍ وَعُيُونٍ |
46 |
«ጸጥተኞች ኾናችሁ በሰላም ግቧት (ይባላሉ)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015046.mp3
|
ادْخُلُوهَا بِسَلاَمٍ آمِنِينَ |
47 |
«ባልጋዎችም ላይ ፊት ለፊት የሚቅጣጩ ወንድማማቾች ኾነው በደረቶቻቸው ውስጥ ከቂም ያለውን ሁሉ እናስወግዳለን፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015047.mp3
|
وَنَزَعْنَا مَا فِي صُدُورِهِم مِّنْ غِلٍّ إِخْوَانًا عَلَى سُرُرٍ مُّتَقَابِلِينَ |
48 |
«በእርሷም ውስጥ ድካም አይነካቸውም፡፡ እነሱም ከእርሷ የሚወጡ አይደሉም፡፡» |
/content/ayah/audio/hudhaify/015048.mp3
|
لاَ يَمَسُّهُمْ فِيهَا نَصَبٌ وَمَا هُم مِّنْهَا بِمُخْرَجِينَ |
49 |
ባሮቼን እኔ መሓሪው አዛኙ እኔው ብቻ መኾኔን ንገራቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015049.mp3
|
نَبِّئْ عِبَادِي أَنِّي أَنَا الْغَفُورُ الرَّحِيمُ |
50 |
ቅጣቴም እርሱ አሳማሚ ቅጣት መኾኑን (ንገራቸው)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015050.mp3
|
وَ أَنَّ عَذَابِي هُوَ الْعَذَابُ الأَلِيمَ |
51 |
ከኢብራሂም እንግዶችም (ወሬ) ንገራቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015051.mp3
|
وَنَبِّئْهُمْ عَن ضَيْفِ إِ بْراَهِيمَ |
52 |
በእርሱ ላይ በገቡና ሰላም ባሉት ጊዜ የኾነውን (አስታውስ)፡፡ (እርሱም) «እኛ ከእናንተ ፈሪዎች ነን» አላቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015052.mp3
|
إِذْ دَخَلُواْ عَلَيْهِ فَقَالُواْ سَلامًا قَالَ إِنَّا مِنكُمْ وَجِلُونَ |
53 |
«አትፍራ፤ እኛ ዐዋቂ በኾነ ወንድ ልጅ እናበስርሃለን» አሉት፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015053.mp3
|
قَالُواْ لاَ تَوْجَلْ إِنَّا نُبَشِّرُكَ بِغُلامٍ عَلِيمٍ |
54 |
«እርጅና የደረሰብኝ ከመኾኔ ጋር አበሰራችሁኝን በምን ታበስሩኛላችሁ» አለ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015054.mp3
|
قَالَ أَبَشَّرْتُمُونِي عَلَى أَن مَّسَّنِيَ الْكِبَرُ فَبِمَ تُبَشِّرُونَ |
55 |
«በእውነት አበሰርንህ፡፡ ከተሰፋ ቆራጮችም አትኹን» አሉ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015055.mp3
|
قَالُواْ بَشَّرْنَاكَ بِالْحَقِّ فَلاَ تَكُن مِّنَ الْقَانِطِينَ |
56 |
«ከጠማማዎችም በስተቀር ከጌታው እዝነት ተስፋን የሚቆርጥ ማነው» አለ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015056.mp3
|
قَالَ وَمَن يَقْنَطُ مِن رَّحْمَةِ رَبِّهِ إِلاَّ الضَّآلُّونَ |
57 |
«እናንተ መልክተኞች ሆይ! ኧረ ለመኾኑ ነገራችሁ ምንድን ነው» አለ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015057.mp3
|
قَالَ فَمَا خَطْبُكُمْ أَيُّهَا الْمُرْسَلُونَ |
58 |
«እኛ አመጸኞች ወደ ኾኑ ሕዝቦች ተልከናል» አሉት፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015058.mp3
|
قَالُواْ إِنَّا أُرْسِلْنَا إِلَى قَوْمٍ مُّجْرِمِينَ |
59 |
«የሉጥ ቤተሰቦች ብቻ ሲቀሩ፡፡ (እነርሱን) እኛ ሁላቸውንም በእርግጥ የምናድናቸው ነን፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015059.mp3
|
إِلاَّ آلَ لُوطٍ إِنَّا لَمُنَجُّوهُمْ أَجْمَعِينَ |
60 |
«ሚስቱ ብቻ ስትቀር፡፡ እርሷን (በቅጣቱ ውስጥ) ከሚቀሩት መኾኗን ወሰነናል» (አሉ)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015060.mp3
|
إِلاَّ امْرَأَتَهُ قَدَّرْنَا إِنَّهَا لَمِنَ الْغَابِرِينَ |
61 |
መልክተኞቹም የሉጥን ቤተሰቦች በመጡባቸው ጊዜ፤ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015061.mp3
|
فَلَمَّا جَاء آلَ لُوطٍ الْمُرْسَلُونَ |
62 |
(ሉጥ) «እናንተ የተሳታችሁ ሕዝቦች ናችሁ» አላቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015062.mp3
|
قَالَ إِنَّكُمْ قَوْمٌ مُّنكَرُونَ |
63 |
«አይደለም እኛ ሕዝቦችህ በርሱ ይጠራጠሩበት በነበሩት ቅጣት መጣንህ» አሉት፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015063.mp3
|
قَالُواْ بَلْ جِئْنَاكَ بِمَا كَانُواْ فِيهِ يَمْتَرُونَ |
64 |
«እውነትንም ይዘን መጣንህ፡፡ እኛም በእርግጥ እውነተኞች ነን፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015064.mp3
|
وَأَتَيْنَاكَ بَالْحَقِّ وَإِنَّا لَصَادِقُونَ |
65 |
ከቤተሰብህም ጋር በሌሊቱ ከፊል ኺድ፡፡ ከኋላቸውም ተከተል፡፡ ከእናንተም አንድም ሰው ወደ ኋላው አይገላመጥ፡፡ ወደ ታዘዛችሁበትም ስፍራ እለፉ» (አሉት)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015065.mp3
|
فَأَسْرِ بِأَهْلِكَ بِقِطْعٍ مِّنَ اللَّيْلِ وَاتَّبِعْ أَدْبَارَهُمْ وَلاَ يَلْتَفِتْ مِنكُمْ أَحَدٌ وَامْضُواْ حَيْثُ تُؤْمَرُونَ |
66 |
ወደርሱም ያንን ትእዛዝ አወረድን፡፡ (እርሱም) የእነዚህ (ሕዝቦች) መጨረሻ ያነጉ ሲኾኑ (ሥራቸው) መቆረጥ ነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015066.mp3
|
وَقَضَيْنَا إِلَيْهِ ذَلِكَ الأَمْرَ أَنَّ دَابِرَ هَؤُلاء مَقْطُوعٌ مُّصْبِحِينَ |
67 |
የከተማይቱም ሰዎች የሚበሳሰሩ ኾነው መጡ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015067.mp3
|
وَجَاء أَهْلُ الْمَدِينَةِ يَسْتَبْشِرُونَ |
68 |
(ሉጥም) አለ «እነዚህ እንግዶቼ ናቸውና አታጋልጡኝ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015068.mp3
|
قَالَ إِنَّ هَؤُلاء ضَيْفِي فَلاَ تَفْضَحُونِ |
69 |
«አላህንም ፍሩ፤ አታሳፍሩኝም፡፡» |
/content/ayah/audio/hudhaify/015069.mp3
|
وَاتَّقُوا اللّهَ وَلاَ تُخْزُونِ |
70 |
«ከዓለማት (ማንንም እንዳታስተናግድ) አልከለከልንህምን» አሉት፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015070.mp3
|
قَالُوا أَوَلَمْ نَنْهَكَ عَنِ الْعَالَمِينَ |
71 |
(ሉጥም) «እነኝህ ሴቶች ልጆቼ ናቸው፡፡ ሠሪዎች ብትኾኑ (አግቧቸው)» አለ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015071.mp3
|
قَالَ هَؤُلاء بَنَاتِي إِن كُنتُمْ فَاعِلِينَ |
72 |
በዕድሜህ እንምላለን እነሱ በእርግጥ በስከራቸው ውስጥ ይዋልላሉ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015072.mp3
|
لَعَمْرُكَ إِنَّهُمْ لَفِي سَكْرَتِهِمْ يَعْمَهُونَ |
73 |
ጩኸቲቱም ፀሐይ የወጣችባቸው ሲኾኑ ያዘቻቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015073.mp3
|
فَأَخَذَتْهُمُ الصَّيْحَةُ مُشْرِقِينَ |
74 |
ላይዋንም ከታችዋ አደረግን፡፡ በእነሱም ላይ የሸክላ ደንጊያዎችን አዘነብንባቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015074.mp3
|
فَجَعَلْنَا عَالِيَهَا سَافِلَهَا وَأَمْطَرْنَا عَلَيْهِمْ حِجَارَةً مِّن سِجِّيلٍ |
75 |
በዚህ ውስጥ ለተመልካቾች በእርግጥ መገምገሚያዎች አሉበት፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015075.mp3
|
إِنَّ فِي ذَلِكَ لآيَاتٍ لِّلْمُتَوَسِّمِينَ |
76 |
እሷም (ከተማይቱ) በቀጥታ መንገድ ላይ ናት፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015076.mp3
|
وَإِنَّهَا لَبِسَبِيلٍ مُّقيمٍ |
77 |
በዚህ ውስጥ በእርግጥ ለምእምናን መገሰጫ አለ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015077.mp3
|
إِنَّ فِي ذَلِكَ لآيَةً لِّلْمُؤمِنِينَ |
78 |
እነሆ የአይከት ሰዎችም በእርግጥ በዳዮች ነበሩ፤ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015078.mp3
|
وَإِن كَانَ أَصْحَابُ الأَيْكَةِ لَظَالِمِينَ |
79 |
ከነሱም ተበቀልን ሁለቱም (የሉጥና የአይከት ሕዝቦች ከተሞች) በእርግጥ በግልጽ መንገድ ላይ ናቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015079.mp3
|
فَانتَقَمْنَا مِنْهُمْ وَإِنَّهُمَا لَبِإِمَامٍ مُّبِينٍ |
80 |
የሒጅርም ሰዎች መልክተኞቹን በእርግጥ አስተባበሉ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015080.mp3
|
وَلَقَدْ كَذَّبَ أَصْحَابُ الحِجْرِ الْمُرْسَلِينَ |
81 |
ተዓምራታችንንም ሰጠናቸው፡፡ ከእርሷም ዘንጊዎች ነበሩ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015081.mp3
|
وَآتَيْنَاهُمْ آيَاتِنَا فَكَانُواْ عَنْهَا مُعْرِضِينَ |
82 |
ከኮረብታዎችም ቤቶችን ጸጥተኞች ኾነው ይጠርቡ ነበር፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015082.mp3
|
وَكَانُواْ يَنْحِتُونَ مِنَ الْجِبَالِ بُيُوتًا آمِنِينَ |
83 |
ያነጉም ሲኾኑ ጩኸት ያዘቻቸው፤ (ወደሙ)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015083.mp3
|
فَأَخَذَتْهُمُ الصَّيْحَةُ مُصْبِحِينَ |
84 |
ይሠሩትም የነበሩት ሕንጻ ምንም አልጠቀማቸውም፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015084.mp3
|
فَمَا أَغْنَى عَنْهُم مَّا كَانُواْ يَكْسِبُونَ |
85 |
ሰማያትንና ምድርንም በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ በእውነት እንጂ (በላግጣ) አልፈጠርንም፡፡ ሰዓቲቱም በእርግጥ መጪ ናት፡፡ መልካምንም ይቅርታ አድርግላቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015085.mp3
|
وَمَا خَلَقْنَا السَّمَاوَاتِ وَالأَرْضَ وَمَا بَيْنَهُمَا إِلاَّ بِالْحَقِّ وَإِنَّ السَّاعَةَ لآتِيَةٌ فَاصْفَحِ الصَّفْحَ الْجَمِيلَ |
86 |
ጌታህ እርሱ (ያልነበረን) ፈጣሪው ዐዋቂው ነው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015086.mp3
|
إِنَّ رَبَّكَ هُوَ الْخَلاَّقُ الْعَلِيمُ |
87 |
ከሚደጋገሙ የኾኑን ሰባትንና ታላቁንም ቁርኣን (በሙሉ) በእርግጥ ሰጠንህ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015087.mp3
|
وَلَقَدْ آتَيْنَاكَ سَبْعًا مِّنَ الْمَثَانِي وَالْقُرْآنَ الْعَظِيمَ |
88 |
ከእነርሱ (ከከሓዲዎች) ብዙዎችን ወገኖች በእርሱ ወደ አጣቀምንበት ጸጋ ዓይኖችህን አትዘርጋ፡፡ በእነሱም ላይ (ባያምኑ) አትዘን፡፡ ክንፍህንም ለምእምናን አለዝብ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015088.mp3
|
لاَ تَمُدَّنَّ عَيْنَيْكَ إِلَى مَا مَتَّعْنَا بِهِ أَزْوَاجًا مِّنْهُمْ وَلاَ تَحْزَنْ عَلَيْهِمْ وَاخْفِضْ جَنَاحَكَ لِلْمُؤْمِنِينَ |
89 |
በልም «እኔ ግልጽ አስፈራሪው እኔ ነኝ፡፡» |
/content/ayah/audio/hudhaify/015089.mp3
|
وَقُلْ إِنِّي أَنَا النَّذِيرُ الْمُبِينُ |
90 |
(ሰዎችን ለማገድ የመካን በሮች) በተከፋፈሉት ላይ እንደ አወረድነው (በኾነ ቅጣት አሰፈራሪያችሁ ነኝ በል)፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015090.mp3
|
كَمَا أَنزَلْنَا عَلَى المُقْتَسِمِينَ |
91 |
(እነርሱም) እነዚያ ቁርኣንንን ክፍልፍሎች ያደረጉ ናቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015091.mp3
|
الَّذِينَ جَعَلُوا الْقُرْآنَ عِضِينَ |
92 |
በጌታህም እንምላለን፡፡ ሁላቸውንም እንጠይቃቸዋለን፤ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015092.mp3
|
فَوَرَبِّكَ لَنَسْأَلَنَّهُمْ أَجْمَعِيْنَ |
93 |
ይሠሩት ከነበሩት ነገር ሁሉ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015093.mp3
|
عَمَّا كَانُوا يَعْمَلُونَ |
94 |
የታዘዝክበትንም ነገር በይፋ ግለጽ፡፡ አጋሪዎችንም ተዋቸው፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015094.mp3
|
فَاصْدَعْ بِمَا تُؤْمَرُ وَأَعْرِضْ عَنِ الْمُشْرِكِينَ |
95 |
ተሳላቂዎችን ሁሉ እኛ በቅተንሃል፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015095.mp3
|
إِنَّا كَفَيْنَاكَ الْمُسْتَهْزِئِينَ |
96 |
(እነሱም) እነዚያ ከአላህ ጋር ሌላ አምላክን ያደረጉ ናቸው፡፡ በእርግጥም (ፍጻሜያቸውን) ወደፊት ያውቃሉ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015096.mp3
|
الَّذِينَ يَجْعَلُونَ مَعَ اللّهِ إِلـهًا آخَرَ فَسَوْفَ يَعْمَلُونَ |
97 |
አንተም በሚሉት ነገር ልብህ የሚጠብ መኾኑን በእርግጥ እናውቃለን፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015097.mp3
|
وَلَقَدْ نَعْلَمُ أَنَّكَ يَضِيقُ صَدْرُكَ بِمَا يَقُولُونَ |
98 |
ጌታህንም ከማመስገን ጋር አጥራው ከሰጋጆቹም ኹን፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015098.mp3
|
فَسَبِّحْ بِحَمْدِ رَبِّكَ وَكُن مِّنَ السَّاجِدِينَ |
99 |
እውነቱም (ሞት) እስኪመጣህ ድረስ ጌታህን ተገዛ፡፡ |
/content/ayah/audio/hudhaify/015099.mp3
|
وَاعْبُدْ رَبَّكَ حَتَّى يَأْتِيَكَ الْيَقِينُ |